>

ይህ ሁሉ መንግስታዊ  ሸፍጥና ሴራ አፋርን ቀብድ አስይዞ ለመደራደር ይሆን....??? (ምኒልክ ሳልሳዊ)

ይህ ሁሉ መንግስታዊ  ሸፍጥና ሴራ አፋርን ቀብድ አስይዞ ለመደራደር ይሆን….???
ምኒልክ ሳልሳዊ

ሰርዶ ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወደብ ጋር በሚያገናኘዉ አዉራ መንገድ ላይ የምትገኝ የፍተሻ ኬላ ናት። የመንግስት ዝምታ እያነጋገረ ነው። ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም የሚወስደው መንገድ በዛሬው እለት ከጧቱ 2 ሰአት ጀምሮ ተዘግቷል ።
ሆን ተብሎ በአፋርና አማራ ህዝብ ላይ የሚደረግ ቁማር እየተመለከትን ነው። የድል ጭፈራ ላይ የነበሩ የመንግስት አክቲቪስቶችም የተሰጣቸውን እንዳይነጠቁ በመፍራት ዝም ብለዋል፤ መንግስት መተንፈስ ሲጀምር ለሆያሆዬ ይመጣሉ።
አፋርን ቀብድ አስይዞ ለመደራደር ታስቦ ነው ? አፋርም እንደ ወሎ መውደም አለበት ? የፌዴራል መንግስቱ ዝምታ ምንድነው ? እስከመቼ ነው ? ካሁን ቀደም በመጀመሪያው ምዕራፍ አፋር የደረሰበት ውድመት እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን በድጋሚ የሁለተኛ ምዕራፍ ውድመት እየደረሰበት ነው። ወይንስ ኬንያ ላይ ለሚያደርገው ድርድር ሕዝብን የሚያስገድድ ተግባር ሕወሓት እንዲፈፅም በሩን ክፍት ያደረገበት ምክንያት ሊኖር ይችል ይሆን ?
ሕወሓት በአፋር ክልል አዲስ በከፈተዉ ጥቃት የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 3 መቶ ሺሕ ደርሷል። የሕወሓት ታጣቂዎች በሚያወነጭፉት ከባድ መሳሪያ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፣ የተለያዩ ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በኢትዮ-ጀቡቲ አዉራ መንገድ ላይ ወደምትገኘዉ ሰርዶ የፍተሻ ኬላ መቃረቡ ታውቋል ።ሰርዶ ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወደብ ጋር በሚያገናኘዉ አዉራ መንገድ ላይ የምትገኝ የፍተሻ ኬላ ናት። የፌዴራል መንግስት ነኝ የሚለው አካል ዝምታም መርጧል።
ሕወሓት ወደፊት እየመጣ መንግስት ዜጎቹን መከላከል የማይችልበት ደረጃ የደረሰው ከምን በመነጨ የፖለቲካ ስካር እንደሆነ ሊገባን አልቻለም። መንግስት ጦርነቱ አልቋል በማለት ጄኔራሎችን መሸለም ብቻ ሳይሆን ቅድሚያ አስተዳድረዋለሁ ለሚለው ሕዝብ ደሕንነት ሊሰራ ይገባዋል። የክልሉ መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች ሲጮኹ ቢሰማም መንግስት መስሚያዬ ጥጥ ነው ብሏል። ይህ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ መንግስት ለሚፈናቀለው ህዝብና ለሚደርሰው ውድመት ኃላፊነቱን ይወስዳል። ለመከላከል ፈቃደኛ ባለመሆኑም ተጠያቂም ነው።
Filed in: Amharic