>

የሸዋን ኦሮሞ ያለኮሽታ እያጸዱት ነው....!!! ዘመድኩን በቀለ

የሸዋን ኦሮሞ ያለኮሽታ እያጸዱት ነው….!!!

ዘመድኩን በቀለ

“…በሰሜን ሸዋ ሰላሌ እና በምዕራብ ሸዋ እንዲሰፍር የተደረገው ኢ-መደበኛው የዐቢይ ሽመልስ ኦነግ የዲሞግራፊ ለውጡን በቶሎ እንዲያሳልጥ እየተደረገ ነው ተብሏል። መረጃው ነገርየው ገዝፎ አድጎ ቤተሱብን መብላት ከጀመረ የመንግሥት አካል ነው። ህዝቡ ልክ እንደወለጋው በሁለቱም ነው የሚገደለው። በመንግሥት ተብዬውም። በኢ-መደበኛው የኦነግ ጦርም። ነገሩ እንዲህ ነው።
“…የሽመልስ አብዲሳና የዐቢይ አሕመድ ጦር የሆነው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ይመጣና ጫካውን እያሳየ በጫከው ከሰፈረው ጦር ጋር እንደመግጠም ለጫካው ሸኔ ስንቅ አቀብላችኋል። አውርታችኋል በማለት በአደባባይ መቀጣጫ ብሎ ይረሽናል። ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ ጣቢያ ይናፍቅህሃል። የሚገደሉት ሰዎች ስም ዝርዝር ቀደም ብሎ ስለሚታወቅ የሰዎቹን መብት የመጠበቅ ምናምን አይሠራም። በቃ መንግሥት በሃላል በሕጋዊ መንገድ ይረሽንሃል።
“… ቀጥሎ መንግሥት የሚገድለውን ገድሎ ከሄደ በኋላ ኢ-መደበኛው የዐቢይ እና የሽመልስም ጦር ደግሞ በተራው ምሽቱን መጥቶ የሚገደሉትን ስም ዝርዝር ይዞ ይመጣና የፈለገውን መርጦ ሰብስቦ ይረሽናል። ኦነግ ደግሞ የሚረሽናቸው በተራው ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ እያለ ነው ተብሏል።
“…የሚገርመው ነገር ደግሞ ጫካ ላለው ቡድን መንግሥት ስንቅ እና ትጥቅ የሚቀርብበት መንገድ ነው። ስንቁ የሚቀርበው እህሉ ከገበሬው ተዘርፎ፣ ከነጋዴው ተገፍፎ ሲሆን ገንዘብ ሲያሻቸው ደግሞ ከባንክ ዘረፋ ውጪ የጫካው የእነ ዐቢይ አሕመድ ቡድን አዲስ ዘዴ እንዳዘጋጀላቸው ነው የሚነገረው። “ኦነግ የመንግሥት ሠራተኛ ልጆችን እያደነ አፍኖ እንዲወስድ ይደረጋል። ከዚያ ሽማግሌ ይላካል። በአንድ ልጅ፣ ወይም ሚስት እስከ 300 ሺብር ይጠይቃሉ። ግለሰቦች ላይ ተሞክሮ ስላላዋጣ ነው የመንግሥት ሠራተኞች ላይ የተተገበረው ይላሉ።  የመንግሥት ሠራተኞቹም ብሩን ከየት እንደሚያመጡት ባይታወቅም የተጠየቁትን ከፍለው ያስለቅቃሉ። ከመንግሥት ካዝና ማለት ነው።
“…ኦርቶዶክስ የሚባል እምነት የሚከተል ኦሮሞ ይታረዳል። የኦሮሞ ሃይማኖቱ ዋቄፈና ነው። ወደፊት የዋቄፈና እምነት የሃይማኖት ሥርዓት እስኪያዘጋጅ ድረስ ማዕተባችሁን ከወዲሁ በጥስ። እምቢ ካልክ አንገትህ ይበጠሳል በማለት አብዛኛውን የሸዋ ኦርቶዶክስ ኦሮሞ ዐቢይ አሕመድ እና ሽመልስ አብዲሳ የመከራ ቀንበር በላያቸው ላይ በመጫን እንዲህ አድርገዋቸዋል።
“ለምሳሌ ብቻ የሌሎቹን አቆይተን በአሁኑ ወቅት በደገም ወረዳ ኢላሙ ሚካኤል ቀበሌ ጎጥ1 ብቻ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እንመልከት። ቤቶቻቸውን በእሳት ካወደሙባቸው እንጀምር።
• የረጋሳ ግዛው ቤተሰብ ሰባት ቤት(7)
• የግርማ ማሙዬ አምስት ቤት(5)
• የተሾመ ደፋሩ ሁለት ቤት (2)
• የሰግጥ ፈዬ ሁለት ቤት (2)
• የሙላቱ አባቡ ሁለት ቤት (2)ከነ እናቱ
• የአስጨናቂ ዘመድኩን አራት ቤት(4)
• የግርማ ብርሃኑ ሁለት ቤት (2)
• የዳኛቸው ተሃለው አራት ቤት (4) ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።
“…ከወደሙት ቤቶች በተጨማሪ በሕጋዊ መልኩ ከዚህ ቀደም በመንግሥት ዕውቅና ሕጋዊ አግባብ በመንግሥት ፈቃድ ታጥቀው ሃገር ይጠብቁባቸው ዘንድ የነበሩ እና አሁን ኢ-መደበኛው የዐቢይ ሽመልስ ጦር ገፍፎ እንዲታጠቀው መደረጉም ተገልጿል።
• የሊቀመንበሩ አቶ ታደሰው ፈዬ አንድ ጎማ ክላሽ
• የአዝመራ ታደሰ አንድ ሳንጃ ክላሽ
• የአቶ ጆቦ ቶላ አንድ ss መሳሪያ
• የአቶ ጆቢር አበበ አንድ ss መሳሪያ
• የአቶ ግርማ ማሙዬ አንድ ሰሌን ክላሽ እና አንድ pps • የአቶ ሀይሉ አንበርብር አንድ እስፓርታ ክላሽ
• የአቶ ግርማ በቀለ አንድ ሰሌን ክላሽ ፣
• የአቶ አስጨናቂ አንድ ሰሌን ክላሽ
• የአቶ ቦጋለ ቶላ አንድ ሰሌን ክላሽ
• የአቶ ጨበር ጌታነህ አንድ ዶጅ ክላሽ
• የአቶ ተካ ከተማ ሳንጃ ክላሽ
• የአቶ አሳመረ ለማ አንድ አባት ጦር
• የአቶ ቦጋለ ሀይሌ አንድ ሳንጃ ክላሽ ነጥቀው መውሰዳቸው ተነግሯል።
“…በጥሬ ገንዘብ።
• ከአቶ ደለለኝ አባቡ ወፍጮ ቤት 500,000 ብር
• ከአቶ ወረቱ ጋቲ 150,000 ብር
• ከአቶ ግርማ እንዳለ 50,000 ብር ተወስዷል።
“…በዐቢይ ሽመልስ የጫካ ኢ-መደበኛ ቡድን የታገቱ ሴቶች ስምዝርዝር
1~ የአቶ ሀብታሙ ቸሩ ባለቤት (ወ/ሮ ኮኮብ)
2~ የአቶ ጆቢር አበበ ባለቤት
3~ የአቶ ተሾመ ደፋሩ ባለቤት (ወ/ሮ ጠጋ አየለ)
“…አሁን ከደገም ወደ ቁርቁራ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የቆመ ሲሆን ሌላው ቀርቶ የቁርቁራ ቅዳሜ ገበያ ራሱ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል። ማንም ከቤቱ፣ ከመንደሩ መውጣት አይችልም። በችርቻሮ መግደሉ ቀርቶ በጅምላ ፍጅት የሚያልቁበትን ቀን ከመጠበቅ በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው ነው የሚናገሩት። የጫካው ቡድን ከህዝቡ በሚዘርፈው እህልና ከብት ሳይቸግረው የሚኖር ሲሆን ለምሳሌ በቀደም ዕለት እንኳ በዐውድማ ካቃጠለው የጤፍ ክምር ባሻገር ከአቶ ጥበቡ ዱፌራ ሰላሳ ኩንታል ጤፍ ሙሉ በሙሉ ለኢ-መደበኛው የዐብይ ሽመልስ ጦር ስንቅ ይሆነው ዘንድ የተጫነለት ሲሆን ማንኛውም አይደለም ስልክ ማውራት ስልክ በእጁ ይዞ ከተገኘ እርምጃ ይወሰድበታል።
“…መረጃውን የሰጡኝ አካላት ዜናውን ዓለም ሁሉ እንዲያውቀው ነው እንጂ ከፈጣሪ በቀር የሆነ ኃይል ይደርስልናል ብለው ተስፋም እንደማያደርጉም አክለው ገልጠዋል።
“…አፋር አደጋ ውስጥ ነው። አፋር ዋናው የጅቡቲ መንገድ ተያዘ ማለት የኢትየጵያ ገቢ ወጪ ንግድ እንዳበቃለት ቁርጡ ይታወቃል። ወደ ዐማራ ክልል ለመሄድ መንገዱ በቀን ብርሃን ይዘጋል። ወለጋ ምዕራብ ሸዋ በኦነግ ኃይል ቁጥጥር ሥር ነው። ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሃገረ መንግሥት ታሪኳ እንደ ዐቢይ አሕመድ አይነት የከፋ መንግሥት ገጥሟት እንደማያውቅ የሚናገሩ አሉ። ብዙ ደካማ መንግሥታት አሉ። ይኖራሉም። እንደ ብልጽግና ግን ከአንድ ተራ የመንደር ዕድር ከፍ ያለ ቁመና የሌለው መንግሥት በታሪክ ታይቶ የሚያውቅም አይመስለኝም።
“…ሻሎም !   ሰላም !
Filed in: Amharic