>

ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ና በሆሳዕና የቆመለት ሀውልት የሚናገረው ውሉ የጠፋበት መልዕክት!! (ዮሴፍ የየሱስወርቅ) 

ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ና በሆሳዕና የቆመለት ሀውልት የየሚናገረው ውሉ የጠፋበት መልዕክት!!
ዮሴፍ የየሱስወርቅ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዋጊ ጀት አብራሪው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ  የውጊያ ላይ ጀግንነት የጀመረው በኢትዮጵያና በሶማሊያ በተደረገው ጦርነት በደርግ መንግስት ጊዜ ነው::
በመቀጠልም በመጀመሪያው የኢትዮጵያና የተገንጣይ ሻዕቢያ ጊዜም ጀግናው በዛብህ በሻቢያ ጦር ተመትቶ ተማርኮ ነበር::
ወያኔና ሻዕቢያ በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግስት ሲመሰርቱ የጦር ምርኮኞችን ሲለዋወጡ ኮሎኔል በዛብህወደ እናት አገሩ ኢትዮጵያ ተመለሰ::
የአንዳንድ ሰው የህይወት ውጣ ውረድ መንገድ እጅግ የሚገርም ነውና ኢትዮጵያና ኤርትራ በባደመ ምክንያት በገቡት ጦርነት ውስጥ ኮሎኔል በዛብህ በተዋጊ ጀቱ በግዳጅ ላይ እያለ ተመትቶ በድጋሚ የኤርትራ ምርኮኛ ሆነ::
ወያኔና ሻዕቢያ ወንበዴ በነበሩበት ጊዜ ተማርኮ በምርኮ ልውውጥ ነፃነቱን የተቀዳጀው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ
የኢትዮጵያና የኤርትራ አገሮች ባካሄዱት ጦርነት ተማርኮ በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት የጀግናውን ነፃነት ወይም ሞቶም ከሆነ ተገቢውን እረፍት አላጎናፀፈውም::
ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ  የታዋቂው ፖለቲከኛ የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ  ታናሽ ወንድም ነው::
ፕሮፌሰር በየነ ለወንድማቸው በተሰራው ሃውልት ላይ ያደረጉትን ንግግር ካዳመጥኩ በኃላ የወንድማቸውን ደብዛ መጥፋት በተመለከተ ምንም ሳይነግሩን በማለፋቸው ምክንያታቸውን ለመረዳት ስልክ ደወልኩላቸውና አገኘኃቸው::
ቃል በቃል ባይሆንም ውይይታችን ይሄን ይመስል ነበር!!
 እኔ (*) ጤና ይስጥልኝ ፕሮፌስር በየነ?
እሳቸው(**) ነኝ ማን ልበል!?
* እኔ :-
ዮሴፍ የየሱስወርቅ እባላለሁ ከአሜሪካ ነው የምደውለው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል መኮንን ነኝ
በወንድሞ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ሃውልት ምርቃት ላይ ያደረጉትን ንግግር አዳምጬ ምንአልባት ስለወንድሞ ያለበት ሁኔታ እኛ ከምናወቀው የተለየ የሚያቁት ካለ ብዬ ለመጠየቅ ነበር?!
**እሳቸው:-
የኤርትራ መንግስት ፈቃደኛ አልሆነም ብዙ ሞክረናል ምንም የተለየ ነገር አላገኘንም
እኔ* :-
በሃውልት ምርቃቱ ላይ ያገኙትን መድረክ ተጠቅመው ለምን የኤርትራ መንግስትን የወድምዎን መጨረሻ ለእስርሶም ሆነ ለኢትዮጵያውያን እንዲያሳውቅ ተማፅእኖ አላቀረቡም? የኢትዮጵያ መንግስትም ከኤርትራ ጋር የፈፀመው የሰላም ስምምነት እንዴት የወንድሞትን ነፃነት እንዳላጎናፀፈ ሊጠይቁበት አይገባም ነበር?
እሳቸው**:-
እናንተ ጋዜጠኞች ስትባሉ …
እኔ* አላስጨረስኳቸው አግባብ ባይሆንም አቋረጥኳቸው!!
እኔ ጋዜጠኛ አይደለሁም  እንደ ኮሎኔል በዛብህ የኢትዮጵያ አየር ኃይል መኮንንነበርኩ ስለ ጀግንነቱ እርሶውን አልጠይቆትም ራሴ በሚገባ አውቃለሁ
እርሶ በወንድምነትዎ እስከአሁን ያደረጉት ሙከራ ካለ( የወንድማቸውንመጨረሻ ለማወቅ) እጅግ በጣም አነስተኛ እንደሆነ ይሰማኛል::
ከለውጡ በሃላ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተነሱት ፎቶ በኢንተርኔት ላይ ሲዘዋወር ያየሁ ይመስለኛል ለመሆኑ ያንን አጋጣሚ ተጠቅመው ጠይቀውታል?
እሳቸው:-**
እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር በ1991 ከመለስ ዜናዊ ጋር የሽግግር መንግስት ምስረታ ተብሎ እንጂ ከዛ በሃላ ኢሳያስ አፈወርቂን አግኝቼው አላቅም::
*እኔ
የእስርሶን ቃል እንደወረደ እወስደዋለሁ ግን እኮ እርሶዎ ራሶ ምክትል ሚንስትር ነዎት የወንድምዎትን ያለበት ሁኔታ ለማወቅ ብዙ መንገዶች አልዎት’
ለምሳሌ:. ጠቅላይ ሚኒስትሩን በየጊዜው ሲያገኙት ሊጠይቁት ይገባ ነበር::  በተለይም የመንግስት አካል ሆነው የምክትል ሚንስትርነትን ሹመት ሲቀበሉ ራስዎትን የችግሩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሄውም አካል አድገዋልና የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ስምምነት እንዴት ተራውን የምርኮኞች ልውውጥ እንኳን ለማስፈፀም የማይበቃ መሆኑ እርሶንም ያስጠይቆታል አልኳቸው!!!
እሳቸውም:-
በሆሳዕና የቆመለት ሃውልት በሃድያ ህዝብ በግሉ ያሰራው እንደሆነ በኤርትራ መንግስት በኩል በእሳቸውም ሆነ በመንግስት የተደረገው “ጥረት” ምንም ለውጥ እንዳላመጣ የተቻላቸውን እንደጣሩና ከዚህ የበለጠ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ነገሩኝ!!
እኔም  የግሌ የሆነውን እምነት ይኸውም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የኤርትራ መንግስት የወንድማቸውን  ያለበት ሁኔታ በማያሻማ ቋንቋ ባልገለፀበት ሁኔታ  የኢትዮጵያ መንግስትም እያሳየ ባለው ዳተኝነት ላይ የእርሳቸው የአብይ አህመድ ተሿሚ ሚኒስትር ሆነው ስልጣን መቀበላቸው  እጅግ የሚያስተዛዝብ መሆኑን ግልጬላቸው በተለይ  የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ገድልና ጀግንነት በተወለደበት ቦታ ብቻ እንዲወሰን  የተደረገበትን ሁኔታ ቢቻል መቃወም አለዚያም በሃውልት ምርቃቱ ላይ የተገኘውን አጋጣሚም ተጠቅሞው የኢትዮጵያንና የኤርትራን መንግስታት የጀግናው ወንድማቸውን መጨረሻ ማሳወቅ እንደሚገባቸው  መልዕክት አለማስተላለፋቸው እጅግ የሚያስቆጭና አሳዛኝ ድርጊት እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ::
የሆሳዕናው የበዛብህ ጴጥሮስ ሃውልት መልዕክት አልባ ነው!!
እንድ ቀን ጀግናውን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን በመዲናዋ ሃውልት የምታቆምለትና በእናት የጦር ክፍሉ አየር ኃይል በስሙ የሚሰየም የተዋጊ ጄት ስኳድሮን የምትሰይምለት ኢትዮጵያ መምጣቷ አይቀርም!!!
ኮሎኔል በዛብህ:-
ጌታዬባለህበት ( በሰማይም ሆነ በምድር)የከበረ ወታደራዊ ሰላምታ ይድረስህ!!!
ኢትዮጵያ የውሸታሞች አገር ሆና መቀጠል የለባትም!!!
አበቃሁ!!!
Filed in: Amharic