>

ኢትዮጲያ እየተገዛች ያለቺው  አቢይ በሚያዘው ድብቅ ኢ-መደበኛ ቡድን እንጂ ብልጽግና በሚባለው ፓርቲ አይደለም..!!!" (አቶ ፀጋ አራጌ ትኩዬ   የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባለስልጣን)

ኢትዮጲያ እየተገዛች ያለቺው  አቢይ በሚያዘው ድብቅ ኢ-መደበኛ ቡድን እንጂ ብልጽግና በሚባለው ፓርቲ አይደለም..!!!”

 አቶ ፀጋ አራጌ ትኩዬ   የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባለስልጣን -!!!
ኢትዮ 360

፠ በ48 ሰዓት መልስ እንዲሰጥበት ለብልጽግና ፓርቲ ቁጥጥር ኮሚሽን የተላከው ባለ ስድስት ገጽ የኮሚሽነሩ ደብዳቤ ይዘት

፠ 12ቱ የብአዴን ባለስልጣናት ከሀገር ለመሰደድ ብለው የተቀራመቱትን 60ሚሊዮን ብር ዘረፋን በተመለከተ፦

የኢትዮጲያ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ ፀጋ አራጌ ትኩዬ ኢትዮጲያ እየተገዛች ያለቺው አቢይ በህገ ወጥ መንገድ ባደራጀው ኢ-መደበኛ በሆነ አደገኛ ቡድን  ነው በማለት ለብልግና ፓርቲው  የቁጥጥር ኮሚሽን በ48 ሰዓት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጣቸው ካስገቡት ባለስድስት ገጽ ደብዳቤ ማወቅ ተችሏል።
ዛሬ ለኢትዮ 360 ሚዲያ እጅ ገብቶ ይፋ በተደረገው የአቶ ጸጋ አራጌ ትኩዬ ደብዳቤ መሰረት ባለስልጣኑ በሕዝብ የተመረጥኩ የሀገሪቱ ገዢ  ፓርቲ ነኝ ስለሚለው የብልጽግና ፓርቲ እጅግ የገለማ አሰራርና ገበናዊ ማንነትን በድፍረትና በጽናት በግልጽ ያጋለጡበትን ሁኔታን ማወቅ የተቻለ ሲሆን የባለስልጣኑ ቆራጥ እርምጃ ፈረንጆች Whistle blower  እያሉ የሚጠሩት አይነት በውስጥ ሆነው ያዩትን እውነታን ያጋለጡበት ድንቅ ምስክርነታዊ ተግባር በመፈጸም ላይ ያሉ አመራር ሆነው አይተናቸዋል።
በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ አስተዳደርነት ጀምሮ በባህርዳር የድርጅት ጉዳይ ኋላፊ፣የገጠር ልማት ቢሮ ኋላፊ፣በአዲስ አበባ የፌዴራሉ ብልጽግና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኋላፊ፣በአዲስ አበባ የአማራ ብልጽግና ድርጅት ጉዳይ ምክትል ኋላፊና ብሎም የሀገሪቱ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ብሎም የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን እያገለገሉ ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ብልጽግና ፓርቲ የአንድ ግለሰብ የግል ንብረት ሆኗል በማለት እኛ ከውጪ ሆነን ስናስተጋባ የቆየነውን እውነታን ባለስልጣኑ በተጠናከረ ማስረጃ አስደግፈው በይፋ በመግለጽ የመጀመሪያ ባለስልጣን ሆነዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የጠቅላላ ጉባኤ አካህዶ የማያውቅ በፓርቲው መተዳደሪያ ሕገ ደንብ መሰረት አመራር እየሰጠ ያለ ያለመሆኑን የገለጹት ባለስልጣን ፓርቲው ማካሄድ የሚገባውን ሁለት ጠቅላላ ጉባኤ ካለማካሄዱም በላይ ሶስተኛውንም ጉባኤ ላለማካሄድ አቢይ እርምጃ እየወሰደ ነው በማለት ለፓርቲው ቁጥጥር ኮሚሽን በጻፉት ባለስድስት ገጽ ደብዳቤ ላይ መረዳት ተችሏል።
የፀረ ሙስና ኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌ ትኩዬ ለብልጽግና ፓርቲ ቁጥጥር ኮሚሽን በላኩት ባለስድስት ገጽ ደብዳቤያቸው ኮሚሽኑ በ48ሰዓታት ውስጥ ምላሽ እማይሰጣቸው ከሆነ ወደ የኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽን በመሄድ የፓርቲውን ኢ-ህጋዊነትና ከፓርቲው መተዳደሪያ ሕገ ደንብ መሰረት እየተጔዘ ያለ ፓርቲ ሳይሆን በምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትና መመስረቻ መስፈርትን በማያሟላ መልኩ ያለ ፓርቲ በመሆኑ ቦርዱ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ እንደሚጠይቁ የገለጹ ደፋር ቆራጥና ጽኑ -በመሆን የመጀመሪያው የአማራ ባለስልጣን ሆነው ብቅ ያሉ ሰው ናቸው ማለት ይቻላል።
ቀደምት ለህወሃት ዛሬ ለኦህዴድ ታማኝ አገልጋይ ባሪያ ጃንደረባ ነው በምንለው ጃንደረባው  ጸረ አማራ ብአዴን ውስጥ እንዲህ አይነት ሀሞተ ኮስታራ፣ለሕዝብና ለሀገር የሚቆም ጀግና አመራር አለ ወይ በሚያስብል ሁኔታ ኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌ የብልጽግናን ፓርቲን ውስጠ ገመናን በተለይም የአቢይ አህመድና የደመቀ መኮንን የማን አለብኝነታዊ የሆነን አምባገነንነትን ቁልጭ አድርገው አሳይተው – ችግሩንም ለማረቅ በጽናት እንደሚታገሉ አሳውቀዋል።
 
፠ 12ቱ የብአዴን ባለስልጣናት ከሀገር ለመሰደድ ብለው የተቀራመቱትን 60ሚሊዮን ብር ዘረፋን በተመለከተ፦
በኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌ ባለስድስት ገጽ ደብዳቤ ውስጥ ከሰፈረው ቁም ነገር ውስጥ አንዱ የብልጽግና ፓርቲ የገንዘብ መዝረፊያና መባከኛ ሁኔታን ከገለጹበት ማስረጃ ውስጥ ፓርቲው ለምርጫው ብሎ ከበጀተው ገንዘብ ውስጥ 60 ሚሊዮን ብር የብ አዴን 12 ከፈተኛ አመራሮች ተከፋፍለውታል በማለት በድፍኑ ካሰፈሩ በኋላ ከ100ሚሊዮን ብር በላይ ደግሞ ያለአግባብ እንዲባክን ተደርጔል በማለት በፓርቲው ውስጥ የሰፈነውን አይን ያወጣ ዘረፋን አስቀምጠዋል።
ይህንን የኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌን የብአዴን ባለስልጣናት 60ሚሊዮን ብር ተከፋፍለዋል ብለው በድፍኑ ያስቀመጡትን መረጃ ለማጣራት ጥረት ያደረገው የኢትዮ 360 ሚዲያው ጋዜጠኛ ሀብታሙ አያሌው 60ሚሊዮኑን ብር የብአዴን ባለስልጣናት መቼ፣እንዴትና  እነማን እንደተከፋፈሉት ለማወቅ ባደረገው ጥረት የ12ቱን የብአዴን ባለስልጣናትን ስምና የተከፋፈሉትን የገንዘብ መጠን አግኝቶ ለማሳወቅ በቻለው መሰረት የሚከተሉት 12 የብአዴን ባለስልጣናት 60ሚሊዮን ብር መከፋፈላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
👉 60 ሚሊዮኑን የተቀራመቱት 12ቱ የብአዴን ባለስልጣናት ዝርዝር
👉 1ኛ – አገኘሁ ተሻገር -9 ሚሊዮን ብር
👉 2ኛ- አብርሃም አለልኝ – 8 ሚሊዮን ብር
👉 3ኛ- ደሳለኝ በላይ-   የፓርቲ ዘርፍ ኋላፊ – 8 ሚሊዮን ብር
👉 4ኛ – ጎሹ እንዳለማው የብልጽግና ኋላፊ 8 ሚሊዮን ብር
👉 5ኛ ጌትነት የብልጽግና ፋይናንስ ኋላፊ – 8 ሚሊዮን ብር
👉 6ኛ – ፍስሀ ደሳለኝ   4.9 ሚሊዮን ብር
👉 7ኛ – አማኑኤል  የወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ ኋላፊ     4.9 ሚሊዮን ብር
👉 8ኛ – የብልጽግና አደረጃጀት  ዘርፍ ኋላፊ – 4.9 ሚሊዮን ብር
👉 9ኛ – ጥላሁን የብልጽግና አደረጃጀት ምክትል ኋላፊ 1.5 ሚሊዮን ብር
👉 10ኛ – ፍቃዱ ዳምጤ የብልጽግና ኦዴትና ቁጥጥር ዘርፍ ኋላፊ    1.5 ሚሊዮን ብር
👉 11ኛ – ባህሩ የብልጽግና አደረጃጀት ምክትል ኋላፊ 1.5 ሚሊዮን ብር
👉 12ኛ – ደሳለኝ  የፖለቲካ ዘርፍ ኋላፊ  1.3 ሚሊዮን ብር
እንደ የመረጃ ምንጫችን 12ቱ የብአዴን ባለስልጣናት የወያኔ ወረራ ተጠናክሮ አስጊ በመሰለበት ወቅት ነገር አለሙ ያበቃለት ነው በሚል ውሳኔ ቤተሰቦቻቸውን ማሸሻ ብለው የተቀራመቱት መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን ይህ ማለት አቢይ አህመድ በአማራ ላይ እንደፈለገ የጭፍጨፋ እርምጃ ሲፈጽም እነዚህ እና  እነዚህን መሰል የብአዴን ባለስልጣናት የፈጸሙት ይህን  እና ይህንን መሰል የዘረፋ ተግባር አፋቸውን ለጉሙው እንደፈለግክ አድርግ እንዲሉ የሚያደርጋቸው አፍ መያዣ ስለመሆኑ አስረግጦ መግለጽ ይቻላል።
ስለብልጽግና ፓርቲ ከብልጽግና አመራር ይልቅ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጠለቅ ያለ መረጃ ሳይኖራቸው አይቀርም
“በፓርቲያችን ብልጽግና ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የህግ ጥሰትና የአሰራር መዛነፍ እንዲስተካከል ስለመጠየቅ” በሚል ርዕስ ለፓርቲው የቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በቀጥታ፣ በግልባጭ ለፓርቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ደብዳቤያቸውን ያስገቡት አቶ ጸጋ አራጌ ትኩዬ  መሆናቸውን ለኢትዮ 360 የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
አቶ ጸጋ አራጌ ለኦዲት ኮሚሽን ያቀረቡት ደብዳቤ የተለያዩ የህግ ጥሰቶችን የሚያነሳ መሆኑንም ተመልክቷል። በተለይም የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ በደንቡ የተሰጠው ስልጣንና ተግባር አካሉ ሳያውቀው ሙሉ ለሙሉ መጣሱን አመልክተዋል። ማዕካላዊ ኮሚቴው ማንም አካል በማያውቀው መንገድ ሁለት መደበኛ ስብሰባ አልፎበት ሶስተኛው መደበኛ ስብሰባን ለማሳለፍ በመንደርደር ላይ መሆኑንም አሳውቀዋል።
በአንጻሩ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አብይ አህመድ የፓርቲውን ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነውን የፓርቲ ተቋም የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባን በማጠፍና በመተው በህግም፣ በአሰራርም ሆነ በሞራል የማይመለከታቸውን ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን በመሰብሰብ የፓርቲውን የፖለቲካና የትግል መድረክ ሆን ብለው የማቀጨጭ አቅጣጫ ተከትለዋል ይላሉ። ይሄም የፓርቲውን ቁመና በእጅጉ ጎድቶታል በማለት አቶ ጸጋ አራጌ ይከሳሉ።
የፓርቲው ጉባኤ በሁለት አመት ተኩል መካሄድ እንዳለበት በህግ ቢቀመጥም ማዕከላዊ ኮሚቴው በማያውቀው ሁኔታ ለሶስት አመት ተኩል እንዲራዘም ተደርጓል ይላሉ። በአሁን ሰአት ደግሞ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለማንኛውም አካል ውክልና ባልሰጠበት ሁኔታ ህገወጥ አዘጋጅ ኮሚቴ በማን እንደተቋቋመ የማይታወቅ የጉባኤ ዝግጅትን እየመራ ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ አካል የማያውቀውን ሰነድ ቀጥሎ ላሉ የመዋቅር አባላት እያወረደ በማደናገር ላይ ነው ሲሉም ይከሳሉ።
በፓርቲው ውስጥ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እየቀረ በጸረ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እየተተካ ነው ይላሉ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ጸጋ አራጌ። ሁሉም ነገር በግለሰብ የግል ፍላጎትና በተናጠላዊ እንቅስቃሴ እየተሰራ በመሆኑ ፓርቲው የግለሰብ ተንቀሳቃሽ ንብረት እስኪመስል ድረስ ተቋማዊ ህልውናውን እስከማጣት ሊደርስ የሚያስችል የህልውና አደጋ ተደቅኖበታል ብለዋል ለኢትዮ 360 በደረሰው መረጃ ላይ።
የብልጽና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በተቋማዊ ስርአት አሰራር ስንጠይቃቸው ሁሉም በፓርቲ ደረጃ የሚሰራውን ስራ እንደማያውቁና መረጃ እንደ፡ሌላቸው ይነግሩናል ይላሉ። ለአንድ ትልቅ ፓርቲ ከዚህ በላይ የሚያሳፍር ነገር ከቶውንም ሊኖር አይችልም ሲሉም በአግራሞት ይናገራሉ።
ስለብልጽግና ፓርቲ ከብልጽግና አመራር ይልቅ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጠለቅ ያለ መረጃ ሳይኖራቸው አይቀርም በማለትም ይገልጻሉ። ይህም በፓርቲው አመራሮች ዘንድ የመገለል ስሜት ፈጥሯል በማለት ፓርቲያቸውን ይከሳሉ።
የፓርቲው የውስጥ ጉዳይ አመራርም ይሁን አባላት ለምን የሚል ጥያቄ ካነሱ የመፈረጅና የማሸማቀቅ ስራ ይሰራባቸዋል። በዚህም ምክንያት በፓርቲው ውስጥ የመተማመንና የተግባቦት ፖለቲካ ከማራመድ ይልቅ የስጋትና የጥርጣሬ ፖለቲካ ምህዳር በፓርቲው ውስጥ ተፈጥሯል ይላሉ።
ሃገሪቱ ባልተገመተ ሁኔታ በጦርነቱ ምክንያት የህልውና አደጋ ውስጥ በወደቀችበት ሁኔታ ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ አካል በዚህ ትልቅ አጀንዳ ላይ አለመወያየቱ ትዝብትን፣ግርምትን ከመፍጠሩም በላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አብይ አህመድ ለአካሉ ያላቸውን ፖለቲካዊ ንቀትና ሞራላዊ ድፍረት የምንረዳበት ግልጽ ሁኔታ ነው በማለት ያስቀምጡታል። በመሆኑም የህወሃት ወራሪ ሃይል የወረራ መነሻና መድረሻ ሄደት ራሱን ችሎ በማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲገመገም የቁጥጥርና የኢንስፔክሽን ኮሚሽኑ ትእዛዝ ይስጥበት ብለዋል።
የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ አቶ ጸጋ አራጌ የቁጥጥርና የኢንስፔክሽን ኮሚሽኑ በ48 ሰአታት ውስጥ የጽሁፍ ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ ፓርቲዎችን ለማስተዳደር ስልጣን ለተሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማቅረብ የሚገደዱ መሆኑን በደብዳቤያቸው ላይ አሳውቀዋል።
 መቌጫዊ መልእክት
የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ስለጦነቱ ጉዳይ ላይ እንኴን ተሰብስቦ እንደማያውቅና አጠቃላይ በፓርቲው መተዳደሪያ ሕገ ደንብ መሰረት ማእከላዊ ኮሚቴውና ስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ በሚወስነው ውሳኔ እየተመራ ያለመሆኑን እና አቢይ አህመድና ደመቀ መኮንን ብቻ የሚዘውሩት ኢ-መደበኛ በሆነ አደረጃጀት የተደራጀ አደገኛ ቡድን – ማለትም የብልጽግና ጠቅላላ ጉባኤ የማየውቀው፣የብልጽግና ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀውና ከሁለቱ አመራሮች ከአቢይና ደመቀ በስተቀር የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የማያውቀው ኢ-መደበኛ ቡድን ሀገሪቱን እያሽከረከሩ ስለመሆናቸው የኮሚሽነር ፀጋ አራጌ ባለስድስት ገጽ ደብዳቤ ያስረዳል።
በፓርቲው መተዳደሪያ ሕገ ደንብ ላይ የሰፈረውን የደንብ አሰራር፣የገንዘብና ፋይናንስ አያያዝ፣የኦዲትና ቁጥጥር አሰራር በሙሉ በመጣስ ስልጣን ያላግባብ የመጠቀምና ብሎም በስልጣን የመባለግ ተግባሮች በፓርቲው ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት – ማለትም በአቢይ አህመድና በደመቀ መኮንን የሚፈጸም መሆኑን በመግለጽ ይህ ተግባራዊ ድርጊት ፍጹማዊ አምባገነንነት እና ህገ ወጥነት ስለሆነ በአስቸኴይ ሊቆም ይገባል በማለት ከብልጽግና ውስጥ ደፍረው በመውጣት የአቢይን ኢ-መደበኛ አመራርን ተቃውመው ለማስቆም የተነሱ ብቸኛውና የመጀመሪያው የአማራ ባለስጣን ናቸው ብሎ የኮሚሽነር ፀጋ አራጌን እርምጃ መግለጽ ይቻለል።
የኮሚሽነሩ የ48ሰዓት ጊዜ ገደብ ወይ ተጠናቌል አሊያም ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። ይህንን አጋላጭ ድንዳቤያቸውን እና አቌማቸውን ተከትሎ በእነ አቢያና ግብረ አበሮቹና ብሎም በራሳቸው በኮሚሽነር ፀጋ አራጌ በኩል የተወሰዱ እርምጃዎችን በቀጣይ እንደማቀርብ እየገለጽኩ መጣጥፌን ስደመድም የመላው  አማራ ሕዝብ ዓይን እና ትኩረት በኮሚሽነሩ ላይ ይሁን የሚለውን መልእክት በማስተላለፍ ነው!!
(  መረጃውን ለሕዝብ ጆሮ በማድረስ በኩል ይፋ ላደረጉት ለኢትዮ 360 ሚዲያ  – ምስጋናችን ይድረስ
Ethio 360 Media  )
Filed in: Amharic