የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አረፉ….!!!
*…. አቡነ አንቶኒዮስ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩትና በመንሥት አስገዳጅነት ከመንበራቸው ተገፍተው በቁም እስር ሲማቅቁ የኖሩትና በቅርብ ቀን በ92 አመታቸው በዛሬው እለት እለት መሞታቸው ተነግሯል። ነፍስ ይማር።
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አንድ አካልና አንድ አምሳል ናቸው። በኤርትራ ቤተ ክርስቲያን የሚደርሰው ግፍ በኛ እንደ ደረሰ እንቆጥረዋለን። በነገራችን ላይ ኤርትራ ለረጅም ዘመን በጣሊያን ቅኝ አገዛዝ ስር ሆና ፋሺስት ጣሊያን እንኳን ከእናት ቤተ ክርስቲያን እንድትነጠል አላደረገም። ነገር ግን በፈረንጆች 1993 በግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሼኑዳ ፈቃድ ተጠይቆ የኤርትራ ቤተ ክርስቲያን እንድትገነጠል ሆናለች። በተጨማሪም ታሪካዊው ደብረ ቢዘን ገዳም ከእናት ቤተ ክርስቲያን ሳይለይ ለአንድ ሺ አመት ሲኖር በጣሊያን ቅኝ ግዢ ዘመንም ቢሆን በእናት ቤተ ክርስቲያን ሲተዳደር ኖሯል። የዘመኑ የክስረት ፖለቲካ ግን ይህንን እትብት ቆርጧል። ይህ ሁሉ ግን ያልፋል።
ለማንኛውም የአባታችንን የአቡነ አንቶንዮስ ነፍስ ይማርልን። በረከታቸው ይደርብን። ቸሩ ፈጣሪ ነፍሳቸውን በቀኙ ያውልልን። አምላካችን መልካም ፈቃዱ ሆኖ ቤተክርስቲያኖቻችንን አንድ ያድርግልን።