>

እነ ደመቀ መኮንን የተሸከመ እነ ወ/ሮ አዳነችና ሺመለስ ቢቀልዱበት አያስገርምም....!!!! (ግርማ ካሳ)

እነ ደመቀ መኮንን የተሸከመ እነ ወ/ሮ አዳነችና ሺመለስ ቢቀልዱበት አያስገርምም….!!!!

ግርማ  ካሳ

ከአንድ ሁለት አመት በፊት፣  በፊት የብልጽግና  አመራሮች ስብሰባ ላይ ነበሩ፡፡ በወቅቱ፣ በቅርቡ የብልጽግና ብልሹና ሕገ ወጥ ተግባራት በመቃወም፣ ለድርጅቱ ጽ/ቤት ደብዳቤ የጻፉት፣ አቶ ፀጋ አራጌ፣ ብድግ ብለው አስተያየት ይሰጣሉ፡፡”የአማራ ህዝብ አመራሮች ከፍርሀት  ከቆፈን እና ከሌብነት ተላቀን ህዝባችን ልንታደገው ይገባል። የሌሎች ተላላኪ በመሆን ህዝባችን እያስጨረስነው ነው። ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪ ስራ እየሰራን ነው። ልንታረም ይገባናል” የሚል እውነት ያዘለ ትክክለኛ አባባል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ከሰላሳ አመት በፊት አሁን ያለው የሕገ መንግስት ሲረቅ በዚያ ነበር፡፡ አንድ አርቃቂ ነበር፡፡ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ልዩ ጥቅም ይጠበቅ ሲባል። የጎሳ አወቃቀር ሲሸነሸን አቶ ደመቀ እዚያው ነበር፡፡ አንዱ  ሰዉዬው የመለስ ዜናዊ የትምህርትሚኒስቴር ሆኖ ሲሰራ ነበር፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስተር እያሉ ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ነበር፡፡  በመጨረሻ ሰዓት፣ እነ አቶ ተስፋዬ ጌታችውና ዶር አምባቸው መኮንን (ነፍሳቸውን ይማር) አንገት ለአንገት ከወያኔ ጋር ሲያያዙ፣ እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ውስጥ ውስጡን ሲታገሉ፣ እርሱ በመጨረሻ ሰዓት ላይ ፍሬቻ ሳያበራ ታጠፈ፡፡  ጠቅላይ ሚኒስተር ሲመረጥ፣  እርሱ እንዲመረጥ ወያኔዎች ይፈለጉ ስለነበረ፣ የድል ቀን አርበኛ ሆኖ፣ ራሱን ከምርጫው አገለለና ዶር አብይ አህመድ እንዲመረጥ አደርገ፡፡  ወያኔዎችን  ከዳቸው፡፡ ለዚህ ውለታውም ኦህዴዶች  በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት እንዲቀጥል አደረጉት፡፡ይህ ሰው ለ30 አመት በስልጣን ላይ የተቀመጠ ሰው ነው፡፡ ስመንግስት ደምቄ አባ መቻል ቀበል አደረጉና  ፀጋ የተናገረው የራሱን አቋም እንጅ የድርጅታችን አመለካከት አለመሆኑን በከፍታ አስምረንበት ልናልፍ የተገባ ነው በማለት ፀጋን “በከፍታ” እንደገሰፁት  360 ዛሬ ዘግቧል።አቶ ፀጋ ለብልፅግና ፓርቲ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የ 48 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ሰጥተዋል ብሏል 360።
ከአንድ ሁለት አመት በፊት፣  በፊት የብልጽግና  አመራሮች ስብሰባ ላይ ነበሩ፡፡ በወቅቱ፣ በቅርቡ የብልጽግና ብልሹና ሕገ ወጥ ተግባራት በመቃወም፣ ለድርጅቱ ጽ/ቤት ደብዳቤ የጻፉት፣ አቶ ፀጋ አራጌ፣ ብድግ ብለው አስተያየት ይሰጣሉ፡፡
“የአማራ ህዝብ አመራሮች ከፍርሀት  ከቆፈን እና ከሌብነት ተላቀን ህዝባችን ልንታደገው ይገባል። የሌሎች ተላላኪ በመሆን ህዝባችን እያስጨረስነው ነው። ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪ ስራ እየሰራን ነው። ልንታረም ይገባናል” የሚል እውነት ያዘለ ትክክለኛ አባባል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ከሰላሳ አመት በፊት አሁን ያለው የሕገ መንግስት ሲረቅ በዚያ ነበር፡፡ አንድ አርቃቂ ነበር፡፡ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ልዩ ጥቅም ይጠበቅ ሲባል። የጎሳ አወቃቀር ሲሸነሸን አቶ ደመቀ እዚያው ነበር፡፡ አንዱ  ሰዉዬው የመለስ ዜናዊ የትምህርትሚኒስቴር ሆኖ ሲሰራ ነበር፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስተር እያሉ ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ነበር፡፡  በመጨረሻ ሰዓት፣ እነ አቶ ተስፋዬ ጌታችውና ዶር አምባቸው መኮንን (ነፍሳቸውን ይማር) አንገት ለአንገት ከወያኔ ጋር ሲያያዙ፣ እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ውስጥ ውስጡን ሲታገሉ፣ እርሱ በመጨረሻ ሰዓት ላይ ፍሬቻ ሳያበራ ታጠፈ፡፡  ጠቅላይ ሚኒስተር ሲመረጥ፣  እርሱ እንዲመረጥ ወያኔዎች ይፈለጉ ስለነበረ፣ የድል ቀን አርበኛ ሆኖ፣ ራሱን ከምርጫው አገለለና ዶር አብይ አህመድ እንዲመረጥ አደርገ፡፡  ወያኔዎችን  ከዳቸው፡፡ ለዚህ ውለታውም ኦህዴዶች  በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት እንዲቀጥል አደረጉት፡፡ይህ ሰው ለ30 አመት በስልጣን ላይ የተቀመጠ ሰው ነው፡፡
ወደ ብልጽግና ስብሰባ ስመለስ፣ አቶ  ፀጋ አራጌ የሰጡትን ትክክለና  አስተያየት ተከትሎ፣  አቶ ደመቀ  ማይክ በመያዝ አስተያየት ሰጠ፡፡  “አቶ ጸጋ የተናገረው የራሱን እንጂ   የአማራ ብልጽግና አቋምን የሚያንጸባርቅ አለመሆኑን በትልቁ አስምረንበት ልናልፍ ይገባል”  የሚል፡፡
አቶ ጸጋ የአማራ ብልግዎች በፍርሃት ቆፈን ተይዘናል፣ ሌቦች ነን፣ ተላላኪ(የኦህዴድ) ነን፣ ህዝባችንን እያስጨረስን ነው፣ ታሪክ ይቀር የማይለው አሳፋሪ ስራ እየሰራን ነው፣ ልንታረም ይገባል ነው ያሉት፡፡
አቶ ደመቀ ይሄንን አባባል ውድቅ አድርጎ ፣ ደፋሮችና ቆራጦች ነን፣ ሌቦች ለትቅም የምንሰራ አይደለንም፣ የሕዝባንችን ሰላም፣ መረጋጋት፣ እድገትና ብልጽኛን አምጥተናል፣ ለህዝቡ ትልቅ ስራ በመስራታችን ሃዉልት ሊሰራልን ይገባል  የሚል እምነት ስላለው ነው መሰለኝ፣ አቲ ጸጋን ተቃውሞ ነው አስተያየት የሰጠው፡፡
እንግዲህ ወገኖች እነ አቶ ደመቀ መኮንን እንደ ሙጃ በላያችን ላይ አድርገን፣ እነዚህን እንኩቶዎች ተሸክመን፣ ለሕዝብ የማያስቡ ከሃዲዎችን እንዲመሩን አድርገን አስቀምጠን፣ ታዲያ እነ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ቢንቁን፣ እነ ሺመለስ አብዲሳ ቢቀልዱን ያስገርማል ????
አሁንም ህዝብ ከነ አቶ ጸጋ አራጌ ጎኢን በመቆም፣ በስሙ እየቀለኡ ያሉት እነ አቶ ደመቀ መኮንን ታግሎ ማስወገድ መጀመር አለበት፡፡
Filed in: Amharic