በሳውዲ ጉዳይ
እንደ ተወካዮቻችን ሳውዲዎች አልበደሉንም‼
ነቢዩ ሲራክ
* ስለ ስደተኛው እናብራለን ‼

ኩሩው ዜጋ ተንቋል። ከክቡሩ የሰው ልጅ የተፈጠረ መሆኑን የዘነጉት ሳውዲዎች ብቻ አይደሉም። ለመብቱ መከበር ቆምን የሚሉ የኢትዮጵታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲን ሰውነቱን ረስተውታል ፣ ዘንግተውታል ብቻ ሳይሆን ጨክነውበታል 🙁 ለስደተኛው ዜጋ መብት የተቋቋሙት ተቋማቱ ሀገር ወዳድ ፣ ወገን አጉራሽ ደጋፊ ዜጋውን ዶላር አያመጣም ብለው ዘንግተውታል …
አዎ እውነት እላችኋለሁ ሳውዲዎች እንደ እኛ ሹሞች አልከፉብንም ። እናም ለምን ስደተኛው ተዘነጋ ብለን ከዚህ በኋላ ደረቅ የተደበቀውን እውነቱን እንናገራለን ። ልዩነት ካለን ከማንኛውም አካል ጋር በአጋርነት በመጓዝ ስለ ስደተኛው መገፋት ድምጽ ከሚያሰሙት ጎን ሆነን የተገፊ ወገኖቻችን በደል መከራና ስቃይ ለአለም እናደርሳለን ።
አዎ ዝም አንልም ‼
የካቲት 3 ቀን 2014 ዓም