>

"ኦነግ ሸኔ ዐማራ መሆኔን አያውቅም፤ ለይቶ የሚያውቀን የሚያሳርደን የአካባቢው አመራር ነው.....!!!" (ከወለጋ የተፈናቀሉ የ60 ዓመት እናት አቤቱታ)

“ኦነግ ሸኔ ዐማራ መሆኔን አያውቅም፤ ለይቶ የሚያውቀን የሚያሳርደን የአካባቢው አመራር ነው…..!!!”
(ከወለጋ የተፈናቀሉ የ60 ዓመት እናት አቤቱታ)
*…. በማጅራቴ ታርጄ የተረፍኩ ሰው ነኝ”
(ከወለጋ የተፈናቀሉ የ6 ልጆች አባት እማኝነት)

*…. አማራን አርደው ደሙን ከጠጡ በኋላ “እፎይ” ይላሉ፤ ሥጋውን ይበሉታል፤ የሰው ሥጋ ምን ምን ይላችኋል? ስንላቸው ጨው ጨው ይለናል ይላሉ
 
*…. ዐማራው በችርቻሮ ሳይሆን በጅምላ መታረድ ዕጣ ፈንታው ከሆነ 4 ዓመት ሞላው…!!!
1. “እናንተ አጎዛ ለብሳችሁ ነው የመጣችሁት፣ የምትኖሩበት መሬትም ሆነ ያፈራችሁት ንብረት የኦሮሞ ነው” ይሉናል።
2. የገደለን ኦነግ ሸኔ አይደለም፤ ኦነግ ሸኔ እኔ ዐማራ መሆኔን ያውቃል? የሚገድለን ጎረቤታችን ማንነታችንን የሚያውቀው ነው።
3. ለአቤቱታ ሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ሄደን ነበር፤ “ውጡልን” ተብለን ተገፍትረን ነው የወጣነው፤ “ወደ መጣችሁበት ሂዱ” ነው የተባልነው።
4. ተፈናቅለን ስንወጣ ሹፌሩን አስቁመው “አንተ የጫንከው በግ ነው? አውርድ” እያሉ ዐማራውን አጋድመው አርደውታል፤ ማረድ የተለመደ በመሆኑ ዐማራን “በግ” እስከ ማለት ደርሰዋል።
5. የወረዳው አመራር በስልክ ሲያወራ በጆሮዬ ሰምቻለሁ፤ “እኛ ግዳጃችንን ጨርሰናል፤ እናንተ በጫካ ያሉትን ጨርሱ፤ ወደ እኛ ጋር አትምጡ፤ ተመለሱ” ብሎ ሲናገር ሰምቻለሁ።
6. አማራን አርደው ደሙን ከጠጡ በኋላ “እፎይ” ይላሉ፤ ሥጋውን ይበሉታል፤ የሰው ሥጋ ምን ምን ይላችኋል? ስንላቸው ጨው ጨው ይለናል ይላሉ።
7. “ኦሮምኛ አትችልም? መሬቱን ወደህ ቋንቋውን ጠልተህ” እያሉ ስብሰባ ላይ ሳይቀር ይደበድቡናል፤ በዚህ ምክንያት ዐማራ ስብሰባ አይቀመጥም።
8. ሰፈርተኛው ሳይቀር ውኃ ልንቀዳ ስንሄድ ይሰድቡናል፡ “አትቀዱም” ብለው ይከለክሉናል።
9. የዐማራ ልጅ ጨካኝ አይደለም፡ የኦሮሞ ልጆችን ሳይቀር ከራሱ ልጆች ጋር አቅፎ መጥቷል።
10. የዐማራ ክልል መንግሥት ይድረስልን፡ ሕዝቡ ታግቶ ተራውን እየጠበቀ ነው ያለው፡ “ጸሎት አርጊልኝ፣ ከነልጄ ተከብቤያለሁ” ብላኛለች አንዷ ከዛው። እባካችሁ ድረሱልን፣ ዘራችን አለቀ።”
አንዲት እናት ከወለጋ ተፈናቅለው ከመጡ በኋላ የሰጡት ምስክርነት!
✍ “በማጅራቴ ታርጄ የተረፍኩ ሰው ነኝ”
(ከወለጋ የተፈናቀሉ የ6 ልጆች አባት እማኝነት)
 1. “መጀመሪያ ብር ነው የጠየቀኝ፣ ነፍሴን ለማዳን ወይፈን ሸጬ ያስቀመጥኩትን ገንዘብ ሠጠሁት፤ ቀጥሎ ‘ክላሽ አምጣ’ አለኝ፤ ‘ማርያምን የለኝም’ ስለው !ማርያም ምንድን ነው?’ አለኝ።
2. “በሰደፍ ማጅራቴን መታኝ። ሰደፉ ሲሰበርበት በመጥረቢያ ደንደስ መታኝ። ወደቅሁ፤ በወደቅሁበት በማጅራቴ አረደኝ። በቆሰለው ማጅራቴ ውስጥ የቆንጨራውን ጫፍ አስገብቶ ደሜን እጁ ላይ እንዲሞላ ካደረገ በኋላ ጠጥቶታል።”
3. እኔንም ልጄንም ሳንሞት የተውን በሬዎቹን ሲያዩ ነው፤ እኔም ልጄም በሕይወት አለን። ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ መቆምና ዕቃ ማንሳት ባልችልም አለሁ።”
ዐማራው በችርቻሮ ሳይሆን በጅምላ መታረድ ዕጣ ፈንታው ከሆነ 4 ዓመት ሞላው…!!!
አሁን ባለው ሁኔታ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በተለይ ኦሮሚያ ብሎ መለስ ዜናዊ በፈጠረው ምድር ውስጥ የሚገኘው ነገደ ዐማራ ዕጣ ፈንታው እንደምታዩት እንደምትመለከቱት መሆን ብቻ ነው። ዐማራው በችርቻሮ ሳይሆን በጅምላ መታረድ ዕጣ ፈንታው ከሆነ 4 ዓመት ሞላው።
ዐማራው በሀገረ መንግሥቱ ውስጥ ወኪል ስለ ሌለው ጥቃት ሲደርስበት እንኳ ድምጽ የሚሆነው የለም። ብአዴን ደግሞ ያው የታወቀ ነው። የብአዴን መሪዎች በአብዛኛው ሃይማኖታቸውን ቀይረው ወይ የደመቀ መኮንን እስልምና አሊያም የዐቢይ አሕመድን ፕሮወሄ እምነት አምነው ተቀብለው የተጠመቁ ስለሆኑ ደንታም የላቸው። የሚታረደውን ወገናቸውን ሲያዩ የሚረኩ ሁላ ነው የሚመስለው።
ወዲህ ዞር ስትል ደግሞ ለዐቢይ መንግሥት ህልውና ሉባንጃ እያጤሰ፣ ወይራና ቀበርቾ እየታጠነ የሚያሽቃብጥለትም ዐማራ ነኝ የሚለው ነው። ዐቢይን መቃወም #NOMORE እያለ ባንዲራ ለብሶ እዬዬ ሲል ሲያሽቃብጥ የሚውለውም በአብዛኛው ዐማራው ነው። ገንዘቡን ፎጭ አድርጎ ለዐቢይ መንግሥት ካድሬና ኮስሞቲክስ የሚያዋጣውም እርሱው ነው።
“…ነፍስ ይማር  ‼
Filed in: Amharic