ኦነግ-ሸኔ አደባባይ – ባሕርዳር ላይ! (ብአዴን ለይቶለት ጨርቁን ጣለ!!)
ይነጋል በላቸው
አንድ መስከረም ከመጥባቱ በፊት ስንት ሽህ ጉድ መስማታችንን እንደምንቀጥል እግዜር ይወቀው፡፡ የሀገራችን ነገር ከቀን ቀን በሚባል ደረጃ ከድጡ ወደ ማጡ እየተዘፈቀ እጅጉን እያስደመመንና እያስጨነቀንም ይገኛል፡፡
ወደዋናው መነሻየ ከማምራቴ በፊት አንድ አስደንጋጭ መረጃ ላካፍላችሁ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ርዕሳነ መምህራንና የሥራ ኃላፊዎች በዝርያ ከኦሮሞ መሆናቸው ቀደም ሲል የሰማነውና እንግዳ ያልሆነ ክስተት ነው፤ መምህራንም የሚቀጠሩት ከዚያው ከኦሮሞ ጎሣ ሆኖ ቦታ ካለ ነው ሌላው የሚቀጠረው ይባላል፡፡ የዚህን መረጃ እውነትነት ለማረጋገጥ ትንሽ የዳሰሳ ጥናት ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም ከሚታየው አጠቃላይ የኦሮሙማ አገዛዝና ከሚስተዋለው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ኦነግ/ኦህዲ ወለድ ቀውስ አኳያ ግን ነገሩ ከግምት ባለፈ ሃቅ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡ አንዳንድ የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታዎች ለይምሰል ያህል በሌሎች ጎሣዎች አባላት ቢያዙም ዋናዎቹ ተቆጣጣሪዎች በየትም ሥፍራ ኦሮሞዎች መሆናቸው የአደባባይ መሥጢር ነው፡፡ ትናንትና ማታ ታዲያ አንድ ወዳጄ በአንድ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ውስጥ ስላጋጠመው ነገር እንደሚከተለው አጫወተኝ፡፡ እንደኔ ብዙም አትንጨርጨሩ፤ ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ ገና ብዙ ጉድ ማየታችን አይቀርም፡፡
“ የአዲስ አበባ ነገር እያከተመላት ነው ወንድሜ፡፡ በሁሉም ሥፍራ የሚሰማውና የሚደረገው ነገር ራስ ያዞራል፡፡ ደጃች ወንድራድ ትምህርት ቤት ውስጥ ሰሞኑን እንዲህ ተደረገ፡፡ ቦታው ኮተቤ የቀድሞው መምህራን ኮሌጅ የአሁኑ ኮተቤ ኮዘሞፖሊታን ዩንቨርስቲ አጠገብ ይገኛል፡፡ አንድ ተማሪ ሊመዘገብ ወደዚያ ትምህርት ቤት ይሄዳል፡፡ የተላከው ሚሌኒየም ከሚባል በዚያው አካባቢ ከሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሊመዘገብ ሲል ዳይሬክተሩ ልጁን ኦሮምኛ ይችል አይችል እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ ልጁም እንደማይችል ይናገራል፡፡ ዳይሬክተሩም በመናደድ ለምን እንዳቻለ ይጠይቀውና ሊመዘገብ እንደማይችል ነግሮ ከግቢው ያስወጣዋል፡፡ የልጁ ቤተሰቦች አንድ ኦሮምኛ የሚችል ወዳጃቸውን ወደ ትምህርት ቤቱ ልከው ዳይሬክተሩን በኦሮምኛ እንዲያግባባላቸው ይጠይቁታል፡፡ ሰውዬውም ሄዶ ዲኒክተሩን ያናግረዋል፡፡ ዲኒክተሩ ግን ‘እርግጥ አንተ ኦሮምኛ ትችላለህ፤ ግን አንተ እንጂ ልጁ አይችልም፡፡ ስለዚህ ህጋችን ነውና ሊመዘገብ አይችልም‘ በማለት አሳፍሮ ይመልሰዋል፡፡ ይህን ጉድ ታሪክም ይመዝግበው፤ ሕዝብም እንዲያውቀው ይደረግ፡፡ ኦሮሙማ አዲስ አበባ ላይ ጉድ እያፈላ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ይሠሩትን አጥተው እሽቅንድር አድርጓቸዋል፡፡ ለጤና ያድርግላቸው፡፡
ሽመልስ አብዲሣ ሰሞኑን ወደባሕር ዳር አቅንቶ ነበር፡፡ የተቀበለውም ጀዝባው – ይቅርታ – ዘገምተኛው የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ይልቃል አስረስ ነው፡፡ ዋናው ፕሬዝደንት ሽመልስ ወይንም አቢይ በመሆናቸው ነው ይህን ገልቱ ምክትል ያልኩት፡፡ ብአዴን የኦሮሙማ ደንገጡር ነው፤ የራሱ እስትንፋስ የሌለው በኦነግ/ኦህዲድ ሣምባ የሚተነፍስ የዞምቤዎች ስብስብ ነው ብአዴን፡፡ የዚህን ቡድን መጨረሻ ለማየት እግ በጣም ጓጉቻለሁ፡፡
ሽመልስ አንደኛ አያፍርም፡፡ እኔ እሱን ብሆን በትዕዛዜ የማስፈጀውን ሕዝብ ይመራሉ ወይም ይወክላሉ ወደሚባሉ ሰዎች ዘንድ አልሄድም፤ እንደሰው የማስብ ከሆነ ያሳፍረኛላ፡፡ ሁለተኛ ሽመልስ አማራን ብቻ ሣይሆን የአማራውን አመራር እጅግ ይንቃል፡፡ በድብቅ ስብሰባው አማራንና አማርኛን እንዴት ከጨዋታ ሜዳ እያስወጣ እንዳለ ለኦሮሞ ልሂቃን ያስረዳበት ድብቅ ቪዲዮ ተተርጉሞ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ያንን ንግግር ደግሞ ብአዴኖች አልሰሙትም ማለት አይቻልም፡፡ እንደዚያ ያለ ስብዕና ያለው ሽመልስ ባሕር ዳር መሄዱ ታዲያ ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ አማራም በቁሙ ሞቷል ያሰኛል፡፡ ምንም ዓይነት ጎጂ ነገር ማድረግ ከህግም ከሞራልም አንጻር ባይመከርም ቢያንስ ጠላታችንና ዕልቂት ያወጀብን ግለሰብ ደጃችንን አይርገጥ ማለት ያባት በነበር፡፡ ይህን ታሪክ መጪው ትውልድ እንዴት እንደሚያፍርበት መገመት አይከብድም፡፡ ብአዴኖች ጥቁር ውሻ ይውለዱ፤ ሲሞቱም ፈጣሪ ነፍሳቸውን አይማረው፡፡ ወንጀለኞች ናቸው፡፡
ሌላው የሚያስቀው የታሪክ ምፀት ደግሞ ለዚሁ ሽመልስ “እንኳን ፈጀኸን፤ እንኳም በየቦታው የሚገኝን አማራ አሳረድክልን” በሚል ይመስላል በስሙ መንገድ ሊሰየምለት እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ በእውነት እንዲህ ሊደረግ ከሆነ ብአዴን ጨርቁን ጥሎ ለይቶለት አብዷል ማለት ነውና ብልህ አማሮች ልትመካከሩበት ይገባል፡፡ ይህ ነገር ለአማራ ስድብ ነው፡፡ ከዚያም ማን ያውቃል – ነገ ደግሞ “ኦነግ-ሸኔ አደባባይ” የሚል የማስታወሻ አደባባይ ጎንደር ውስጥ ወይንም እዚያው ባሕር ዳር ላይ ተሰይሞ ልንሰማ እንችል ይሆናል – ጆሮ አይሰማው የለም መቼም፡፡ ሆዳምነት እስከዚህ እንደሚያዋርድ አላውቅም ነበር፡፡ በዚህ መልኩ ጎዳናና አደባባይ በገዳዮችና አስገዳዮች ስም መሰየም በርግጥ ትልቅ ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ወዴት እየሄድን ነው ግን? በዚህ ሰሞነኛ ጉዳይ ብዙ አማሮች በሀፍረት ተሸማቀው አንገታቸውን እንደሚደፉ እልጠራጠርም፡፡ ለነገሩ ብአዴን ውስጥ እውተኛ አማራ ወይንም ትክክለኛው የአማራ ሥነ ልቦና ያለው ሰው አንድም የለም፡፡ ሁሉም ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ጭንቅላታቸውን ሆቸው ውስጥ የደበቁ አጋሰሶች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ደግሞ በሙስና የበሰበሱና የጠነቡ፣ በንጉሣቸው በአቢይም ይሄው ሙሰኝነታቸው በቀይ ካርድነት ተይዞ የገዛ ነውራቸው “ሆስቴጅ” የሆኑ ናቸው፡፡ ያሳዝናል፡፡