>

በ ቄለም ወለጋ   ከ160 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ኃላፊዎች እና ነዋሪዎች ተወስደው እስካሁን ደብዛቸው ጠፍቷል....!!!! DW

በ ቄለም ወለጋ   ከ160 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ኃላፊዎች እና ነዋሪዎች ተወስደው እስካሁን ደብዛቸው ጠፍቷል….!!!!

DW

 

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ በጅምላ አንድ ቦታ ተገድለዋል የተባሉት 87 ሰዎችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ደብዛ መጥፋት እስካሁን ከመረጃ ውጭ በውል አለመረጋገጡን አንድ   የአከባቢው ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬሌ ነግረዋል
የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ኬንቦን ቀና እንዳሉት የጊዳሚ ወረዳን ከሁለት ወራት በላይ ተቆጣጥረውት የነበሩ «የኦሮሞ ነጻነት ጦር » ታጣቂዎችን ማስለቀቅ ቢቻልም በአጎራባች ወረዳዎች አሁንም ታጣቂዎቹ እየተንቀሳቀሱባቸው ስለሆነ አስከሬንም ሆነ የጅምላ መቃብር ማግኘት አልተቻለም። ይሁንና ከቄለም ወለጋው ዞን ጊዳሚ ወረዳ እና ከአጎራባች የምዕረብ ወለጋ ዞን ወረዳዎች ከ160 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ኃላፊዎች እና ነዋሪዎች ተወስደው እስካሁን ደብዛቸው መጥፋቱ ግን በውል የየተረጋገጠ መሆኑን አመልክተዋል።
ኃላፊው «ቄለም ወለጋ ካሉዋት 12 ወረዳዎች አንደኛው ጊዳሚ ወረዳ በአሸባሪው ሸኔ እጅ ነበር። ከ2 ወራት ጊዜ በኋላ መንግሥት አሁን ወረዳዋን ወደ ቁጥጥሩ መልሷታል። ኦነግ ሸኔ ወረዳዋን በተቆጣጠረበት ከሁለት ወራት ባለፈ ጊዜያት በርካታ ሰዎችን በተለይም የመንግሥት ሠራተኞችን ለይቶ በመያዝ አሰቃይቷል። ባገኘነው ተጨባጭ መረጃ 16 የወረዳ አስተዳደር ኃላፊዎች፣ 11 የመንግሥት ሠራተኞች፣ 47 የሚሊሻ አባላት፣ 2 ፖሊሶች፣ 5 የቀበሌ ኃላፊዎች፣ ከማኅበረሰቡ 20 ወንድ እና 4 ሴቶች አጠቃላይ ከጊዳሚ ወረዳ 105 ሰዎች እና እንደ ቆንዳላ እና ቤጊ ካሉ ከአጎራባች ወረዳዎች 63 ሰዎች ባጠቃላይም ታፍነው የተወሰዱት 168 ሰዎች  መገደላቸውን ነው ያገኘን መረጃ የሚያሳየው፡፡» በማለትም ዘርዝረዋል።
ባለፈው ሳምንት በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ታጣቂዎቹ ብሔርን መሰረት አድርገው ባደረሱት  ጥቃት 168 ሰዎች በጂምላ መገደላቸው ተዘግቧል። የግድያው መፈጸም እንደተሰማም «መንግሥት ዜጎችን መከላከል አልቻለም» እንዲሁም «ታጣቂዎች ብሔርን መሰረት አድርገው እያደረሱ ያለው ጥቃት እየተባባሰ ነው » በሚል ከፍተኛ ውግዘት አስከትሏል።
በተደጋጋሚ ወለጋ ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ስለመኖራቸው እሱን ተከትሎም በርካቶች ስለመፈናቀላቸው እየተነገረ ነው። ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት ምን መደረግ ይኖርበታል ትላላችሁ? ሃሳባችሁን አካፍሉን።
ምንጭ #DW_Amharic
Filed in: Amharic