>

የወለጋ ደም ጎርፍ ሆኖ እንዳይወስደን! (ፊልጶስ)

የወለጋ ደም ጎርፍ ሆኖ እንዳይወስደን!

ፊልጶስ

የደም  ጽዋው ሞልቶ፣ ……

የደም ፅዋው ሞልቶ፣—–ሞልቶ፣  ሞልቶ ፈሶ
ሰው መባል በሰው፣ ስዕብናችን አሶ፤
የጅምላው መቃብር ፣ ከጉድጓዱ ተርፎ
የሬሳችን ክምር ፣ ከተራራው ገዝፎ፤
ከ’ጥናፍ- እስከ-አጥናፍ፣ ደማችን  “’ረክሶ’’፤
ውቅያኖስ፣ ባህሩን፣ ወንዙን አደፍርሶ
እዩት ይ’ጣለላል፣ ጫካውን አልብሶ።——
ግን እኮ፣ ……። እንኳ’ ደም፣ ውኃ ፈሶ፣ አይቀርም
ይዘገያል እንጂ፣ በሰፈሩት ቁና፣ መሰፈር አይቀርም።

ከዓመታት በፊት የአፍሪካን ቀንድ በሚመለከት፤ ኬንያናይሮቢ ውስጥ የምሁራን ስብሰባ ነበር። በስብሰባው ውስጥ ከታደሙት የሱማሌው ተወካይ  ምሁር በተለይ ኢትዮጵያንና አገራቸውን በተመለከት እንዲህ ነበር ያሉት፤

የኢይትዮጵያ ህዝብ አገር ሲኖረው፤ መንግሥት ግን የለውም።  የሱማሌ ህዝብ ግን አገርም መንግሥትም የለውም።  “”

ታዲያ እኒህ የሱማሌ ምሁር  ዛሬ ላይ  በአገራችን ላይ ስለሚፈጸመው ቢጠየቁ   በተቃራኒው ኢትዮጵያዊያን  አገርም ሆነ መንግስት የላቸውም እኛ ግን አለን“” የሚሉ   ይመስለኛል።

ሱማሊያኖች እንዲህ እንደኛ መንግሥት አልባ በሆኑበት ዘመን እንኳን፤ እንደ እኛ  ዓይነት የዘር ማጥፋት ወንጀል አልተፈጸመም። የሰው ልጅ በማንነቱ በቁሙ እንደ ከብት አልታረደም። እናት መሃጸኗ በጩቤ እየተዘለዘለ  በማንነቱ ብቻ መወለድ የለበትም ተብሎ ፅንስ አልታረድም፤  ሥጋው እየተዘለዘለ አልተጠበሰመ።
በኛ አገር ግን ያውም እገዛችኋለሁ የሚል ኃይል ባለበት ከዘመነ ፍጥረት እስከ
 አሁኑ ሰዓት ድረስ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ የዘር ማጥፋት ወንጅል አማራ በተባለ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ላይ ይፈጸማል፤ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ በእግር ህዝብ ላይ ተጀምሯል።

 በሩዋንዳ በቱቲሲ ዜጎች ላይ ይተፈጸመው የዘረ ማጥፋት ወንጀል የተካሄደው ለስምንት ወር ብቻ ነበር።፡ በእኛ ግን ከወያኔ ዘመን በኋላ እንኳን  ይኽው አረተኛ  ዓመቱን  አስቆጥሯል።

እስቲ ሌላውን ለታሪክ እንተወውና ሰሞኑን በወለጋ   በኦሮሙማ ብልጽግና  አዝማችነትና የዳቦ ስምም በተሰጠው በኦነግሸኔ  በማንነታቸው ብቻ ተመርጠው የታረዱትን ወገኖቻችን ለማውገዝና በቃ ለማለት ሰው መሆን በቂ አይደለም ወይ??
ከአሁንስ በኋላ የምንጠብቀው ከወለጋ የሚፈሰው ደም ጎርፍ ሆኖ እስኪወስደን ነውን

በዚህ ከቀጠልን ነገከነገ ወዲያ ኦሮሙማ ብልጽግና በየአንዳንዳችን በር  የእርድ ሰይፋን ይዞ አይመጥምን?  ከአሁን በኋላስ ምን አየጠበቅን ነው?

 ለኛ አይነቶቹ  ነው አልበርተን አነስታየን፤
ዓለም የምትጠፋው ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ቁጭ ብለው በሚመለከቱ ነው። ´´’ ያለው። አዎ ኢትዮጵያ  እየጠፋች  ያለችውና ልጆቿ እንደ  አውሬ እየታደኑ እንዲገደሉ አሳልፈን የሰጠናቸው  እኛ ቁጭ ብለን የምንመለከተው ነን።

ከጽንስ እስከ ሽማግሌ  በወያኔም ሆነ በኦነጋዊ ብልጽግና ከአፋር እስከ ወለጋ  ወገኖቻችን በማንነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው  የሚታረዱት  ´ ዝምታ ወይም ከፌስ ቡክ ጫጫታ ያላለፈ  የመሆኑን ሃቅ መቀበል አለብን።

ኢትዮጵያም አንደ አገር እንዳትቀጥልና ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉት   ደግሞ በማንነታቸው እንዲጠፋ መወሰኑን   የኦሮሙማው ብልጽግና ገዥ ኃይል   እየወሰደ ያለውን ርምጃ  ግራ ለገባችሁም ሆነ  ለግንዛቤ ያህል  በዚህ ሰዓት ያለውን አራት  ፀሃይ የሞቀውን ሃቅ ብቻ ልጥቀስ፤1/ በቃላት ሊገለጽ የማይችል   መሰዋአትነት የተከፈለበት ጦርነት እንዲገታ ተደርጎ፤ ነገር ግን ወያኔ ግዜ ተሰቶት  አራሱን በበለጠ እንዲያደራጅና ሁለተኛ ዙር ጥቃት በተለይም በጎንደር፣ በወሎና በአፋር እንዲያካሄድ  የተደረገበት።

በአሁኑ ሰዓት በአፋር ከሶስት መቶ በላይ ወገኖቻችን መፈናቀል ብቻ አይደለም፤ ወያኔ ከጅቡቲ  አዲስ እበባን መንገድ ለመቆጣጠር እንደተቃረበ ተረጋግጧል። ታዲያ ይህ ሁሉ የሚሆነው ድል አድርገናል ወያኔንም ዳግም እንዳይነሳ አደርገነዋል በተባለ ሳምንታት ውስጥ ነው። የአፋር ፋኖዎች ብቻቸውን እንዲጋደሉ ተውስኖባቸዋል። የዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት በኢትዮጵያዊነታቸው ሰለማይደረደሩ ነው።

2/ በጭንቅ ወቅት ራሱን አስታጥቆ  የወያኔን ወደ አዲስ አበባ መግባት በመከላከል ደረጃና እሰከ ትግራይ ድንበር ወያኔን በማባረር  ከፍተኛ መሰዋአትነተ የከፈለውን ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረገው ደፋቀና፤  ዓላማው ወያኔን ሰተት አድርጎ በተለይም ወልቃይትን  ለማስወረርና ከሱዳን ጋር እንዲገናኙ፤ ከዚያም እርቅ ሲባል ወያኔ የያዘውን ቦታ ይዞ የመደራደር መብት አለው በማለት ኢትዮጵያዊኑን ከጨዋታ ውጭ ማድረግ ነው።

3/ የኦሮሙማ ብልጽግና  የዳቦ ስም የሰጠውን ኦነግ ሸኔን  ከአራት ኪሎ በሚሰጠው መመሪያ እንዲደራጅና  በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋቱን በነጻነት አንዲያካሄድ የተደረገበት። ከዚህ ላይ የኦሮሙማን  ብልጽግና እንደ መንግሥት ለምትቆጥሩ ስለ ኦነግ ሸኔ  ከመሰረቱ ጀምሮ አስከ ዚህ ሰዓት ድረስ ማን አንደሚመራው  የኦሮሚያ ክልል ፀጥታና ደህንነት ሀላፊ የነበሩት በብ/ ከማል ገልቹ !በራሳቸው ሰው የተነገረው አውነታ አንዲህ ይላል፤

አብዛኛዉ የኦነግ ሰራዊት የኦዴፖ ነዉ። ትጥቁም የኦዴፖ ነዉ። ኦዴፖ ደብዳቤ ፅፎ ኦነግ ወረራ እንዲካሂድ ይፈቅዳል። ኦዴፖ ወደ ደቡብ እና ስሜን እንዲዘምት ደብዳቤ ፈቅዷል። እኔ ይህን በመተቸቴ ተባርሬያለሁ።ኦነግ እንዲረብሽ የሚፈቅድለት ኦዴፖ ነዉ። ኦነግ ማለት ኦዴፖ ነዉ። ሁለቱም በስህተት መንገድ ላይ ናቸዉ።

ለዓለፋት ሶስት ዓመታት በወለጋ የሚሰማው ሰቆቃ ከገዥዎቻችን ይልቅ እኛን የሰው ልጆችን የበለጠ ተጠያቂ የሚያደርግ ነው። በጉጅ ህዝብም ተመሳሳይ የዘር ማጥፋት በኦሮሙማ እየተፈጸመ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች እየወጡ ነው።
የሚገርመው ´ የሚካሄደው የዘር ማጥፋት ሁሉ  ኦነግሸኔ ከወያኔ ጋር አብሮ  ኦሮሞን ከእማራ ለማጣላት የሚደረግ ነው።´  የሚል ውሃ የማይቋጥር ማዘናጊያ ይደሰኮራል።  እውነት ከሆነ ሰላሳ ሶስት ዙር የሰለጠነው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ምን ሲሰራ እየዋለ  ነው??  ´  ኦነግሸኔ የማሰልጠኛ ካምፕ የሚሰጠውና መኪና ከነ ጦር መሳሪያ የሚያስታጥቀው ማን ነው?  “ዶሮን ሲያታልሏት—–” ´ማለት ከዚህ ላይ ነው።

4/ የሃይማኖት ብጥብጥ ለመፍጠርና አገር ለማመስ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማዳከምና  የተረኝነትን አገዛዝ ለማጠናከር በኦሮሙማ ብልጽግና በተሾሙት፤  በእነ አዳነች አበቤ የሚፈጸመው ግፍና ማን አለብኝነት፤  ብሎም  አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርና ´ፊኒፊኒ ኬኛ´ ´  ለማረጋገጥ  የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ተጠሪነቱን  በቀጥታ  በአዳነች አበቤ ስር ለማድረግ እየተከሂደበት ያለበት መንገድ  የሚያመለክተው ነገ የወለጋውን የዘር ፍጅት አዲስ አበባ ላይ ለመፈጸም መሆኑ ነብይ አያስፍለግም።

ጥያቄው ታዲያ አሁን ምን እናድርግ ? የሚለው ይሆናል።

በርግጥም አገራችን የጎሰኞች መጫዎቻ ለመሆን የበቃችውና አገር አልባ ለመሆን የደረስነው፤ ወደድንም ጠላንም ሃቁ፤ የኛ ተደራጅቶና አምርሮ ያለመታገል፣ ያለያም ቁጭ ብሎ የመመልከት ውጤት መሆኑን  መቀበለ አለብን።
መጸሃፍ ´ጥበብ ቤትን ሰራች፤ ስንፍና ግን አፈረሰችው።´ ይላል።

እናም  ከትላንንቱ ግብዝነታችን ተምረን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ  ከተደራጅንና ከታገልን የጎጠኞች መንደር የማይፈራርስበትና ኢትዮጵያን የማንተደግበት  ምክንያት የለም። ነገር ግን ሊሎቹ ላይ ጣትን በመቀሰር ወይም በማሳበብ የሚካሂድ  ትግል እንደሌለ ተገንዝበን፤ ትግላችን ከራሳችን እንጀምር። እንደሚባለውሌሎች ታግለው ነጻ እንዲወጥ የሚጠብቅ ሰው፤ እሱ ራሱን ባሪያ አድርጓልና መቼም ቢሆን ነጻ አይወጥም።´”

ስለዚህ ´´ ብለን ትግላችን ከራሳችን እንጀምር።
የወያኔን ወረራ  ለመቀልበስ፣ የወለጋን እልቂት ለምታደግ፣ የኦሮሙማን ብልጽግና ተረኝነትንና ዘረኝነትን ለማሰውገድ፤  እንደ ግለሰበም ሆነ  እንደ ቡድን ምን አደርኩ´ በለን  ራሳችን እንጠይቅ። ተደራጅተን ለማደራጀት ብሎም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት በወሬ ሳይሆን በተገባር የተደራጁትን በመደገፍና በማገዝ ወገናችንና አገራችን እንታደግ።

ስለዚህም፤

1/ ፋኖ  መነሻውም ሆነ መድረሻውን ኢትዮጵያዊንትና የኢትዮጵያን አንደነት ለማሰከበር ራሱን በበለጠ አድራጅቶ  ከአፋርና ከሌሎች ወገኖቹ ጋር አንድነት በመፍጠር በተለይም በወለጋና በሌሎቹም የአገራችን ቦታዎች የሚካሄደን የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከልና ማስቆም። ከዚህም በተጨማሪ  ፋኖ ዓለም  ዓቀፍ እውቅና እንዲኖረው ጥበብና ጥንቃቄ የተሞላበት የዲፕሎማሲ ስራ መስራት፤ አቋሙንና ትግሉን ለሚመለከታቸው ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች፤  ሌላው ቢቀር በደብዳኔ ማሳውቅ፤ ለምሳሌ ለተባበሩት መንግሥታት፣ ለአፍሪካ ህብረት፣ ለአውሮፓ ህብረ ወዘተ። ከዚህ ላይ ይህ ሲሆን ኦሮሙማ ብልጽግና ዝም ብሎ ያያል ማለት አይደለም። ግን  በእንድነት ተደራጅተን እስከቆምን እና ለመሰዋአትነት እስከተዘጋጀን ድረስ  የዘር ፍጅት ፈጽሚዎቹን ሆነ  ተላላኪውን የእማራ ብልጽግና ነኝ ባይ  በውድም ኮነ በግድ መስመር ማስያዝ የግድ ይላል።
2/ ´በቃ´ ወይም  “No Moor”   የተሰኘው እንቅስቃሴ እንደገና ራሱን መፈተሽና ለውጭ አገሮች  ጣልቃ ገብነትት  “በቃ”  እንዳለ ሁሉ የገንዛ ወገኖቹ በበገንዝ ወግኖች  መንግሥት ነኝ በሚል አካል የዘር ፍጅት ሲፈጸምበት፣ ከወያኔ ጋር አብሮ እንደገና ከጀርባው ሲወጋውና ለሌላ ዕልቂት ሲያዘጋጀው፤  “በቃማለት አለበትና እንቅስቃሴን በወያኔና በኦሮሙማ ብልጽግና ላይ ማዞር አለበት። ለዚህ ደግሞ ´ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው። 

3/  በተቃውሚ ስም  ተደራጅተው ነገር ግን ከኦሮሙማ ብልጽግና ጋር አብረው ለሚሰሩ፣  ወያኔም ሆነ ኦነግ ሸኔ ለሚፈጽመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ መሆናቸውን አውቀው በርግጥም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን መቆም ከፈለጉ ከተሰጣቸው የተላላኪንት ስልጣንም ሆነ ከይስሙላው ፓርላማ በመውጣት ማንነታቸውን ያስመስከሩ።  

4/ በወለጋም ሆነ  በአጠቃላይ በአገራችን ህዝብ ላይ ያለውን ጥቃትና የዘር ማጥፋት ለመከላከል ´”ራስን መከላከል”  የተፈጥሮን መብት መጠቀምና መደራጅት ያስፈልጋል። ራስን ለመከላከል መንግሥት በሌለበት አገር ከማንም ፍቃድ መጠየቅ አያስፈልግም።  ይህ እንዲተገበር   ትጥቅ ለሌለው ትጥቅና አስፈላጊውን ራስን የመከላከያ ቁሳቁስ ማቅረብና ወገንን መታደግ ከእያንዳድዱ ዜጋ የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን ነገ ለሁላችንም ለተደገሰው እልቂት መከላከያ ነው።

ማጠቃለያ፤  ትግሉ ውስብስብና ብዙ መሰዋአትነት የሚጠይቅ  ብቻ  ሳይሆን፤ የውስጥ ገዥዎቻችን ከምደረ-ገፅ መጥፋታችንን ከሚሹ አገሮች ጋር መጣመራቸው ነው።  በተለይም በአሁኑ ሰዓእት አፋርና አማራ ከያቅጣጨው  ጥቃት ተከፍቶበታል። መልዕክቱ ግልጽ ነው፤ ኢትዮጵያዊነትን ለመስበር  እነዚህ ሃይሎች ለወያኔም ሆነ ለኦሮሙማው  መመታት አለባቸው።  ጥቃቱ ግን ወደፊት ኢትዮጵያዊ ነኝ በሚል ዜጋም በደቡቡም ሆነ በሊሎቹ የአገራችን ክፍል እንደሚቀጥል ግልጽ ነው።   ስለዚህም  እንድነት መፍጠርና ትግሉን  በጋራ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከመሃል እስከ ዳር ማቀናጀት፤ የሁላችንም መዳኛ የሆነችውን ኢትዮጵያንና ወገንኖቻችንን ይታደግልናል፤ የገዥዎቻችን ዕድሜም ያጥራል። ስለዚህም ከወይኔ እልቂትም ሆነ  የወለጋው ደም ጎርፍ ሆኖ ሳይወስደን ´ ጅብ ከሚበላህ በለተህው ተቀደስ።´  እንድሚባለው፤ ትግል የሚጀምረው ራስን ከመከላከልና ነጻ ከማውጣት ነውና፤ ሁላችንም የትግሉ አካል እንሁን።


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

E-mail: Philip is we gmail.com

Filed in: Amharic