>

ቋሚ ሲኖዶስ እና የከተማ አስተዳደሩ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል....!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ቋሚ ሲኖዶስ እና የከተማ አስተዳደሩ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል….!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

ብዙ የተባለለት ስብሰባው እና መልእክቴ… !!!

“…አርፍጄ ነው የደረስኩት። ከራየን ወንዝ ማዶ የተነሣችው ጠያራ በቶሎ ቦሌ ዓለምአቀፍ ሮጲላ ጣቢያ ልታደርሰኝ አልቻለችም። ለዚያ ነው የዘገየሁት። ሃሳቤን ብቻ ይዤ ስለሆነ የሄድኩት ሻንጣ ፍተሻው ጋርም አልቆምኩም። በቀጥታ ወደ ቤተ ክህነት ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው ያመራሁት። በቦሌም በባሌም ያንገራገረኝም ያስቸገረኝም የለም። አሁን ጥጌን ይዤ ስብሰባውን እየተከታተልኩ ነው። የጸጥታ ኃላፊው ዶር ቀንአ ያደታ ብቻ አስር ጊዜ ወደ እኔ ዞር እያሉ እየገላመጡ ቢያዩኝም እኔ እቴ ደንታም አልሰጠኝ።
“…ከንቲባ አዳነች አቢቤም ታላቋን ቤተ ክርስቲያን በሚመጥን መልኩ ቀርባለች። መነኮሳት ፊት፣ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ፣ ያውም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፊት፣ ቅዱስ ፓትርያርኩም ፊት ሲቀረብ እንዴት ተሁኖ እንደሚቀረብ በተግባር ስላሳየችኝ ደስ ብሎኛል። ቀረብ ብዬ አመሰግናለሁ ልላት ፈለግኩና የለም የለም ነገር እንዳላበላሽ ኋላ ይደርሳል ብዬ ጥጌን ይዤ ቀልቤን ወደ ስብሰባው አድርጌ ጮጋ ብዬ ተቀምጫለሁ።
“…ስለ ስብሰባው ከማውጋታችን በፊት ግን ከስብሰባው በኋላ ምን እናድርግ? የሚል አንዲት ጦማር ትኖረኛለች። ጠብቁኝ። ከንቲባ አዳነች አቢቤን በዐቢይ ደመቀ አማካኝነት በአዲስ አበባ ከተማ ከታቀደላት ክፉ ሴራ ቢያንስ እንዴት እንድትባንን ማድረግ ይቻላል በሚል የማቀርበው ሃሳብም ይኖረኛል። እነ ዐቢይ አሕመድ ፋኖን ለመምታት ሲሉ ለጥምቀት በጎንደር ሊበሏት አስበው በጎንደር የከሸፈውን ዕቅድ አዳነች አቢቤን በአዲስ አበባ በመብላት በአዲስ አበባ ህዝብ እና በአጠቃላይ በኦርቶዶክሳውያኑ ላይ ሊያደርሱ ላቀዱት ጭፍጨፋስ እኛ ኦርቶዶክሳውያን እንዴት ነው በጥበብ ማለፍ የምንችለው? የእነ ዐቢይ አሕመድን አጋንንታዊ የክፋት እቅድስ እንዴት ማክሸፍ ይኖርብናል? በሚል የራሴን ቀኝ ትከሻዬን የሸከከኝን ምልከታም አቀርብላችኋለሁ። ጠብቁኝ።
“…አጀንዳ አንቀይርም። አጀንዳ እንሰጣለን እንጂ ከእንግዲህ በኋላ አንቀበልም። የትግራይ ቤተ ክህነትን ጉዳይ እዚያው እነ ስታሊንና አሉላ ይንጫጩበት። ኢግኖር ማድረግ ነው። በስንት ጉዳይ ጮጋ ብሎ ከርሞ ለዚህ አጀንዳ ሲል ተንጦልጡሎ የመጣውን ዳንኤል ክብረትንም አንሰማውም። ትግሬን ለመስደብ፣ ለመቃወም ብቻ ፈቃድ ያገኘ ይመስል ኦሮሞን ባላየ ባልሰማ ጮጋ እያለ አስሬ ህወሓት ሕወሓት የሚለውንም ዝብዘባውን አንሰማም። ትኩረት ለመሳብ የሚላላጠውን በሙሉ በዝምታ ራቁት ማስቀረት ነው። ብቻውን በትግርኛም በአማርኛም ይንጫጫ። ፃፃፃፅጺፂቓቑቔቖኻዅኽ ይበል ምን አገባኝ። ኢግኖር መግጨት ነው። በዚህ ጉዳይ የምን ማስታወቂያ መሥራት ነው። እኔን በውስጥ መስመር የሚወተውቱኝ የወያኔ መንጋ መዓት ብትመለከቱ ለጉድ ነው። አልመልስላቸውም። “…ልንገነጠል ነው? ምን እንደሚውጣችሁ እናያለን ሲሉኝ ለአንዳንዶቹ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ። ታዲያ እኔ ምን ላድርግህ ነው የምላቸው። እነሱ የሚፈልጉት አጀንዳ ይዘን ዋይዋይ እንድንልላቸው ነው። ወፍ የለም።
“…ቅዱስ ሲኖዶሱም ጮጋ ነው ማለት ያለበት። የትግራይ ህዝብ ራሱ የማያውቀውንእና ከውጭ ያለው ትግሬ ብቻ የሚሰማውን ጫጫታ ማስተጋባት የለበትም። የትግሬ ጉዳይ ከኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጉዳይ ጋር አንድ አይነት አይደለም። የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጉዳይ ለመነጋገር መንገዱ ዝግም ሩቅም አልነበረም። በእግርም፣ በታክሲም፣ በፈረስም የሚደረስበት ነገር ነበር። የሃሳቡ አንቀሳቃሾችም ተፈልገው የሚገኙ፣ ለውይይትም ሩቅ አልነበሩም። የትግሬው ግን ወቅቱ አይፈቅድም። አሁን መጀመርታ ቀለብና መድኃኒት የሚያገኙበት መንገድ ሰፋ እንዲል መጣር ማገዝ ነው እንጂ የብሽሽቅ ጊዜም አይደለም። ደግሞም በትግራይ ላሉት አባቶች ልናዝንላቸው እንጂ ልናዝንባቸው አይገባም። ጆሮ ግንዳቸው ላይ ምን ተደቅኖ እንደሚቀባጥሩ እናውቃለን? እህዕ።
“…እንናበብ። እናቅድ፣ በአንድነት እንነሣ፣ ቃላችን፣ መፎክራችን፣ ድምጻችን አንድ ይሁን። ያቀድነውን እንተግብር። አጀንዳ ሰጪ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ አንሁን። እንደ መስኖ ውኃ ወሄም፣ መኔም፣ ብልፄም፣ ከአቅሟ ሂዊም አይንዱን፣ በቀደዱልን ቦይ አንፍሰስ። ረጋ ብለን እናስብ። ሜዳውን በአግባቡ እንጠቀምበት፣ አሰላለፋችንን እናስተካክል። መከላከሉ ጥሩ ነው ነገር ግን ነጥቡ ጎሉ ላይ ነውና ለውጤት እንሥራ። ራቅ ራቅ ብላችሁ የቆማችሁ ባለ ማዕተብ ኦርቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ልጆች የሆናችሁ በሙሉ ቀረብ ቀረብ በሉኘ ቲፎዞ ሰብሰብ ሲል ነው የሚያምረው። የሚያስደነግጠውም። በፌስቡክ ፔጃችሁ ላይ ክፉ የሚያናግሯችሁ፣ በብዕር ስም፣ በእስላም ስም፣ በጴንጤ ስም እየተሳደቡ ፔጃችሁን ሊያቆሽሹ፣ ሃሳብ ሊሰርቁ፣ ከአጀንዳው ሊያስወጡ፣ ሊረብሹ የሚመጡትን በብሎክባን ሰይፍ አስወግዱ። ቅሰፉአቸው። ቤታችሁን አጽዱ። አባቴ ይሙት አዛኜን ነው የምላችሁ የኢትዮጵያውን የፌስቡክ መንፈስማ እንለውጠዋለን። ድልም እንነሣበታለን። ከመንገደኛ ጋር ፌስቡክ ላይ ወገባችሁን ይዛችሁ አትሰዳደቡ። ተሳዳቢን ከፔጃችሁ አስወግዱት። ምንአባቱ ያመጣል? ምንም። ምንም አባቱ አያመጣም። አከተመ።
•… አሁን ወደ ጋራ መግለጫ አዳራሹ እንግባ።

ቋሚ ሲኖዶስ እና የከተማ አስተዳደሩ የጋራ መግለጫ አወጡ

በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስና የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባለት  የጋራ ውይይት ላይ ቤተክርስቲያን ያቀረበቻቸው ጥያቄዎች ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ተቀባይነት አግኝተዋል ።
   ችግሩንም በመሰረቱና በማያዳግም መልኩ መፍታት እንደሚገባም ታምኖበታል።ስለሆነም ችግሮቹን በማያዳግም ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መልኩ መፍታት ይቻል ዘንድ ቋሚ ሲኖዶስና የከተማ አስተሩ መግባባት ላይ የደረሱ ሲሆን በቤተክርስቲያን የቀረቡ ዝርዘር ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጠበት እንደሚሔድና ጎን ለጎንም ቤተክርስቲያን እና የከተማ አስተዳደሩ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። የጋራ መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
Filed in: Amharic