>

'ዋናው ትግል ገና አልተጀመረም...!!! "  አቶ ፀጋ አራጌ

‘ዋናው ትግል ገና አልተጀመረም…!!! “

 አቶ ፀጋ አራጌ
ንሥር  ብሮድካስት
*…. የብልጽግና ከፍተኛ አመራር አቶ ፀጋ አራጌ ፓርቲያቸውን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰሱት
ከዚህ በፊት ለብልፅግና ፓርቲ የውስጥ ኦዲት ክፍል በፓርቲው ያሉ የህግ ጥሰቶችን በመጥቀስ ቅሬታ ያቀረቡት ከፍተኛ አመራሩ አቶ ፀጋ አራጌ የካቲት 2/2014 በይፋ ብልጽግና ፓርቲን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰውታል።
   አቶ ፀጋ አራጌ አክለውም “እኔ እውነትን ፍለጋ እየናወዝኩ ነው። ከዚህ በኋላ የማውቀውን እውነት ሁሉ ለህዝቡ መረጃ ለመስጠት ራሴን አዘጋጅቻለሁ!!” ሲሉ ተናግረዋል።
ፀጋ አራጌ ትኩየ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በጽሑፋቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
<<የተከበራችሁ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሰሞኑን እኔ ያቀረብኩትን ቅሬታ መሠረት ተደርጎ በርካታ ነገሮች ሲንሸራሸሩ ተመልክቻለሁ። እኔ ያለኝን ቅሬታ በህግና በአሠራር መሠረት አቅርቤ መልስ እየተጠባበቅኩ ነው። እስከዚህ ጊዜ ድረስ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም በጉዳዩ ላይ ምንም የሰጠኝ መልስ የለም። ቅሬታ የቀረበበትም አካል ግን በጀመረው ህገ ወጥ መንገድ ስራውን ቀጥሏል።
የእኔ አቅም ለሚመለከተው አካል ማሣወቅና ፍትህ መጠየቅ ነው። ከዚያም ካለፈ ለፈጣሪ መተው የገረመኝ ነገር ግን የአማራ ብልፅግና የሠጠው መግለጫ ነው። ለሱ የቀረበ ቅሬታ በሌለበት ሁኔታ መልስ ሠጥቷል። የሠጠው መልስ እርባና ቢስ ስለሆነ ለዚህ መልስ አልሠጥም። ዋናው ትግል ገና አልተጀመረም። እሱ ሲጀመር ምን መልስ እንደሚሠጥ እናየዋለን።
ሌላው የምታሣዝኑኝ በላኪዎቻችሁ ትእዛዝ በሚከፈላችሁ ገንዘብ ህሌናችሁን ሽጣችሁ በማታውቁት አጀንዳ ገብታችሁ እኔን የምትሣደቡ ወገኖቸ ናችሁ። እርግጠኛ የምሆነው ግን እውነቱን ስታውቁትና ሲገባችሁ ትቆጫላችሁ። እኔ አውነትን ፍለጋ እየናወዝኩ ነው ከዚህ በኋላ የማውቀውን እውነት ሁሉ ለህዝቡ መረጃ ለመስጠት እራሴን አዘጋጅቻለሁ ብለዋል።
በእኔ ላይ የመንግስትንና የፓርቲን ገንዘብ እያወጣችሁ የምታሠድቡ ወንድሞቼና እህቶቼ የምነግራችሁ ነገር ስራችሁ ካልሆነ በስተቀር የቀጠራችሁት ፀሃፊ አያድናችሁም፤ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ።
የእኔን የእውነትና የፍትሕ ፍለጋ ቅን ልቦና በትክክል ተረድታችሁ ላበረታታችሁኝ ወገኖች በፈጣሪ ስም አመሠግናለሁ ሲሉ የሀሳብ ደጋፊዎቻቸውም አመስግነዋል አቶ ፀጋ አራጌ፡፡
Filed in: Amharic