>

"ጆሮ ከቀንድ በፊት ቢበቅልም ... ቀንድ ሲዋጋ፣ ጆሮ እንደተንጠለጠለ ይኖራል" (አቶ ፀጋ አራጌ )

“ጆሮ ከቀንድ በፊት ቢበቅልም … ቀንድ ሲዋጋ፣ ጆሮ እንደተንጠለጠለ ይኖራል”
አቶ ፀጋ አራጌ 

ከ10 አመት በፊት በኢህአዴግ የማዕከላዊ ስብሰባ ላይ አቶ በረከት ስምዖንን ሞገተው አሉ። አማራ የሚወከለው በእኛ በአዳዲስ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንጂ፣ እንደነ በረከት ስምዖን ባሉ አማራን በማይወክሉ አመራሮች አይደለም። ነባሩ የብአዴን አመራር የህወሃት ተላላኪ ነው። በደምም ቢሆን ለእነሱ ይቀርባሉ … በማለት ይጋፈጣቸዋል። በዚህ ጊዜ እነ በረከት እሳት ሆኑ፣ እነ ታደሰ ካሳ አጓሩ፣ እነ ከበደ ጫኔ ተነጫነጩ።
ታደሰ ካሳ እጁን አውጥቶ በትጥቅ ትግሉ ባልነበሩ፣ እኛ ትናንት በመለመልናቸው የብአዴን አዳዲስ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ልንሰደብ አይገባም። አሁኑኑ ድርጅታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል አለ አሉ። በረከት ስምኦንም ይህንኑ ደገመው።
አቶ ፀጋ አራጌም በድጋሜ እጁን አውጥቶ በአንድ ተረት ሸነቆጣቸው።
“ቀንድ ከጆሮ በሗላ ቢበቅልም ሹል ነው። ረጅምም ነው። ይዋጋል። ጆሮ ግን ከቀንድ በፊት ቢበቅልም፣ እንደተንጠለጠለ ይኖራል” በማለት። እኛ አዳዲሶቹ እንዋጋለን ለማለት ነው።
ሰዎቹ አሁንም አበዱ።
በሗላ አቶ በረከት በማጠቃለያ ሰዓት መልሶ አቶ ፀጋን ለማሸማቀቅ እንዲህ አለ አሉ።
“እከ ተሳስቷል። በአወስትራሊያ ቀንድ ካላቸው ላሞች ይልቅ፣ ቀንድ የሌላቸው ብዙ ወተት ይሰጣሉ። ስለዚህ የእከ ተረት ሳይንሳዊ አይደለም” በሚል ሊያሸማቅቀው ሞከረ።(አቶ በረከት እከ ያለው አቶ ፀጋን ነው። ወቅቱ የቤቶች ድራማ የተጀመረበት ስለሆነ ) …
የሆነው ሆኖ በወቅቱ ውስጣዊ ትግል እነ ፀጋ አሸንፈው ነበር። እነ ደመቀ መኮንን ተመልሰው እነ በረከትን ባይሆኑ ኖሮ።
ወደድንም ጠላንም ግን በብአዴን ካምኘም ሆነ በመላው የአማራ ፖለቲካ የአቶ ፀጋ የሰሞኑ ዱላ አንድ ውጤት ያስገኛል። የደፈረሰው ይጠራል። የአማራ ተቆርቋሪና የአማራ ባንዳ ይለያል።
በውጤቱም ወይ ብአዴን ከአራጁ ኦነግ ይነጠላል፤ ወይ ከአራጁ ኦነግ ጋር ይሞሸራል።
Filed in: Amharic