>

ወለጋ እሩቅ ለመሰላቸዉ የቁራ ፖለቲካ አራማጆች....!!! (ሸንቁጥ አየለ)

ወለጋ እሩቅ ለመሰላቸዉ የቁራ ፖለቲካ አራማጆች….!!!

ሸንቁጥ አየለ

ኢትዮጵያን እጅ ስታደርግ ብቻ ትድናለህ::ላንተ እንደሚመስልህ መደበቂያ ቀበሌም ወይም መሸሻ ሰፈር የለህም::
ወለጋ እሩቅ የመሰላቸዉ የብአዴን ፖለቲከኞች የአብን ፖለቲከኞች: እና አንዳንድ ተቃዋሚ መሰል የአማራ ፖለቲከኞች ህዝብ በኦሮሚያ እየተጨፈጨፈ ዝም በሉ “አማራ በኦሮሚያ ተጨፈጨፈ ካላችሁ ሌሎች ይበልጥ ይገደላሉ” የሚል ምክር ሲያዘንቡ ነበር::
እነሱ ይሄን ቢሉም የኦነግ ግፍ ግን አጣዬን ከማቃጠል አልቆመም::ዛሬ ደግሞ ጎሃ ጺዮን ደርሶ የአማራን ህዝብ ከመፍጀት:የአማራን ተጓዦች ከማረድ አልቆመም::
የአማራ ክልል የሚባል ወያኔ ቆርጦ የሰተህ አጥር ቤት ዉስጥ ታጥረህ ብትፎክር :ብታጓራ ቁም ነገር የለህም::ማንም አይፈራህም::ከቶም አትድንም::
ደጋግመን እንደጻፍነዉ መላዉ ኢትዮጵያን እጅህ ሳታደርግ አትድንም::
መላዉ ኢትዮጵያን ነጻ ሳታወጣ እና የምኒሊክን ቤተመንግስት ሳትቆጣጠር ከቶም መሸሻ የለህም::
የቁራ ፖለቲካ አማራ ወጣት መሃከል ተነዝቶ “እኔ ስለ ኢትዮጵያ አያገባኝም” ስለ አማራ ብቻ ነዉ የሚያገባኝ የሚል ስነልቦና እንዲረጭ የብ አዴን ቅጥረኞች በሀሰተኛ ብሄረተኝነት ስም ብዙ ሰርተዋል::
የአማራ ሀገሩ ወያኔ የሰጠዉ ቁራጭ መሬት ብቻ የሆነ እንዲመስለዉ ብዙ የስነልቦና ጨዋታዎች ተሰርተዋል::
በመሆኑ 51% የአማራ ማህበረሰብ እራሱን መጤ እንደሆነ እንዲቆጥራ በጠባቂነት እጅና እግሩን አሳስሮ እንዲቀመጥ ሆኗል::ሞት እና እርድ እየመጣለት የአማራ ክልል ከሚባለዉ አካባቢ የሆነ ሀይል መጥቶ የሚያድነዉ እየመሰለዉ እግርና እጁን አጣጥፎ የሚጠብቀዉ እርሱ እራሱን እንደ መጤ እና ሀገር እንደሌለዉ አይቶ ነዉ::
በሌላ በኩል ደግሞ አማራ ክልል ላይ ፖለቲካ እንሰራለን የሚሉ የአማራ ቅብ ፖለቲከኞች እራሳቸዉን በቆራጣ ክልል አጥረዉ እስክስታ እየመቱ ቆመዋል::
ከግራ እና ከቀኝ ቆራጣ ራዕይ ህዝቡን ልቦናዉን ሸብቦ እንዲይዘዉ ተደርጓል::
ግን ደጋግመዉ ነግረዉሃል::በዬትኛዉም የኢትዮጵያ ክፍል ብትኖር የአማራን ዘር ሳናጠፋ አርፈን አንቀመጥብም ብለዉሃል::ጥርት እና ቅልብጭ ባለ ቋንቋም እንዲህ ነግረዉሃል::ይሄን ሊንክ ተከትለህ የጠላቶችህን ንግግር ለአንድ ደቂቃ ስማዉ:: https://fb.watch/bcMQzngbTi/
በመሆኑም ኢትዮጵያን ከጠላቶችህ እጅ ፈልቅቀህ ካላወጣህ ፈጽሞ አትድንም::
ከኦህዴድ/ኦነግ ጋር ተስማምታችሁ የአማራን ህዝብ ለአካባቢያዊ ጥቅማችሁ እና ለጎጣዊ ጥቅማችሁ የለወጣችሁ:የአማራ ፖለቲከኛ ነን ብላችሁ ምግባራችሁን ግን በክፍለሀገር የቀየዳችሁም: የኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን እርድ በፍጥነት ወደ እናንተም ይመጣል::እናተ ግን ዛሬ ዉስኪ ስለጨበጣችሁ ጮማ ላይ ስላላችሁ አይሰማችሁም::
ዛሬ አባይ በረሃ ደርሶ የሚቆም ከመሰለህ ጉዳዩ አይቆምም::ትግልህን ወደ መሃል ሀገር አድረገዉ::ወደ መላዉ ኢትዮጵያ ላይ አድርገዉ::መላዉ ኢትዮጵያን እጅህ የምታደርግበትን እና የምኒሊክን ቤተመንግስት የምትቆጣጠርበትን  ራዕይ አንግበህ እስክትነሳ በዬትኛዉም አካባቢ ብትሸሸግ ከቶም አትድንም::ኢትዮጵያን እጅ ስታደርግ ብቻ ትድናለህ::
ዋናዉ የትግል መሳሪያ ገንዘብ:ሰራዊት ወይም ደግሞ ወኔ አይደለም::ራዕይ ነዉ::አሁን ያለዉ ትግል የተሰበረ ራዕይ ላይ የቆመ ነዉ::ኢትዮጵያን እጅ ለማድረግ የማይሰራ ራዕይ::የምኒሊክን ቤተመንግስት ለመቆጣጠር ከመንቀሳቀስ ይልቅ በዬአካባቢ ታጥሮ እስክስታ መምታት ላይ እና መፎከር ላይ ያተኮረ ትግል::ስለፎከርክ የሚፈራህ የለም::
ስለገደልክም ድል አታደርግም::በራዕይ ተንቀሳቅሰህ ግን በዉስን ሀይል ሀገርን እጅህ ማድረግ ትችላለህ::ያኔም ህዝብህን ታድናለህ:: መዳኛዉ መንገድ አንድ ብቻ ነዉ::ኢትዮጵያን እጅ ማድረግ::
Filed in: Amharic