>

ስለወጊያው አንዳንድ ጨዋታዎች፣ ከላስታዎች! (ጦቢያን በታሪክ - ቴሌግራም)

ስለወጊያው አንዳንድ ጨዋታዎች፣ ከላስታዎች!

 

ጦቢያን በታሪክ 

 

የምታገኙት ሰው በብዛት መጫወት የሚፈልገው ስለ ጦርነቱ አስከፊነት እና እነሱ ስላሳለፉት ጊዜ ነው። አንዳንዱ በባሕል መሠረት “ግዳዩን ማቅረብ ይፈልጋል” ማለትም የሠራውን ጀብዱ ማውራት ይፈልጋል፣ አብዛኛው ግን ከመመጻደቅ ይልቅ ያየውን ያወራል። እቺን በቀልድ እና ጨዋታ፣ በአስቂኝ ክስተቶች መልክ ይነግራል።

1/ ላሊበላ የአንድ ትምህርት ቤት ጥበቃ አልሰሙም ወታደር እንደሸሸ። ሀገር ሁሉ ሕዝቡም ለቆ ወጥቶ ብቻቸውን ትት ቤቱ ጋ ሁነው tdf እየገባ ነበር። አንድ ልጅ በሳቸው ሲያልፍ እረ ማንነው የገባዉ ይሉታል ተንኮሉ “ፋኖ” አላቸው። ሰውየው ጠመንጃቸውን እያቀባበሉ በሰልፍ የሚገቡት እሳቸው ጋ ደርሰው እስኪያዋሯቸው ቸኩለዋል አሉ። ደስ ብሏቸው። ከዛ ሲደርሱ እሳቸው ጋ “እንኳን ደኅና ገባችሁ እነዛ መናጢዎች መስላችሁኝ እኮ!” አሏቸው። “ማንነው መናጢ?” አለ አለቃ ቢጤ። ህውሃት ነዋ። ሲሉ እኛ እኮ ነን አሏቸው። ክው ብለው “እንዲች?!” ብለው ጠመንጃቸውን ወረወሩት። 😂

እነሱ ሳቁ፣ ጠብቅ አሉና ትተዋቸው ሄዱ

2/ ለአንድ የቤተ አማኑኤል አባት 10ሺህ ብር የሰጠ የtdf ተዋጊ “ይሄ ሁሉ?” ሲባል “አሃ አማኔል አይደል?” ብሎ ነው የሄደው አሉ።

3/ ስልክ ለመደወል ሰው ጋራ ጋራውን እየሄደ ነበር ኔትወርክ የሚያገኘው እና ሽምሻ ሲሄዱ tdf ይፈትሻል ሰዉን። መታወቂያ ያያሉ። አንዱ መታወቂያው አልታደሰም ነበረ እና ወታደሩ “አልታደሰም እኮ” ቢለው “እና መንግሥት የለ የት ላሳድሰው” ይለዋል። ወታደሩ በሳቅ ፍርፍር ብሎ ስቆ በሉ ሂዱ እሺ ብሎ አሳለፋቸው። እንዲህ በጣም ብዙ ወሬ ነው ያለው።

4/ አንድ ዱላ የያዘ ሚሊሺያ ሦስት tdfኦችን በማታ ያገኛል። እንዲህ ብሎኛል “ብረት ገፊ እና ጂም የሠለጠነ ወደል ካጋጠመሽ አንገቱን ብትይው ፍንግል ይላል፣ እኔም ሁለቱን አጋድሜ ሦሰተኛውን አንገቱን ፍለጋ ብሰነዝር እየተገለባበጠ አቃተኝ። ጀግና ነው፣ ክርብትብት ይላል። ታድያ አራቴ ሰንዝሬ ቢያቅተኝ ይሄ ነገር አልሆነም አልኩ እና ልሮጥ ስል እግሬን ጠልፎኝ በፊቴ ተደፋሁ። እንደምንም አድርጌ ሳይዘኝ ይሻለይ ዘልዬ እየዋኘሁ አመለጥኩ። ፊቴ ተገሽልጦ ሃኪም የለ ምን የለ ሽንቴን ሸናሁ እና ተቀባሁት። መደኃኒት ነው። አምስት ቀን ቤቴ ተኛሁ። ተሻለኝ።”

እንዲሁ ከሩቅ ከመበጥረቅ ሕዝብ ያሳለፈውን ሲያወራ ጆሮ መሰጠቱ ይሻላል መሰል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ላሊበላ የደረሰውን የእህል እጦት ገታ ለማድረግ እርዳታ እየተከፋፈለ ነው እና እሱን እዩ። አከፋፈሉ ግን ሕዝብ እያጣላ ነው ብለዋል (ለያንዳንዱ አባወራ ሳይሆን በቡድን በቡደን ተከፍሎ ሰዉ በተወካይ ነው የሚሰጠው እና የሆነ ያልገባኝ ሰዉን ግን ያማረረው ነገር አለ።)

ቪድዮ: የUSAID እርዳታ እህል ሲከፋፈል

 

ጦቢያን በታሪክ በቴሌግራም እንዲከተሉ እንመክራለን። ብዙ ይማራሉ  ያውቃሉም – ይደሰታሉም።

https://t.me/EthiopiaInHistory

 

Filed in: Amharic