>

የሰሊጥ ፖለቲካ ወግ....!!!! (ሰማህኝ ፈንታው)

የሰሊጥ ፖለቲካ ወግ….!!!!

ሰማህኝ ፈንታው

*…… ባህርዳር ውስጥ አንድ ስም አይጠሩ ሆቴል አለ።ሆቴሉ ለብአዴኖች ወዳጅ ነው ብሎ ከማለት ሆቴሉ እራሱ ብአዴን ነው ማለት ማጋነን አይሆንም።ሆቴሉ ለምን “ሁለገብ ብአዴን ሆቴል” ተብሎ እንዳልተሰዬመ ብአዴናዊ ጥናትና ምርምር በብአዴናዊ ሙህር መደረግ አለበት የሚሉ ብዙዎች ናቸው።
ሆቴሉ ለብአዴኖች ሁሉ ነገራቸው ነው።ሲራቢ መመገቢያ፣መዝናኛ፣መሰብሰቢያ፣የአንግዳ መቀበያ፣ሲጣሉ እንደ ዛፍ ሰር መታረቂያ ነው…ኧረ አገልግሎቱ ብዙ ነው,,,በጎራና በጎጥ ተቧድነው በአዝማሪ ታጅበው የሚበሻሸቁበት ነው፣ቁማር የሚጫዎቱበት…ከሁሉም በላይ ሚስጥራቸውን የሚጠብቅ ሁኖል።ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ ለአክቲቪስቶቻቸው ብአዴናው ዜና  ማነፍነፊያና ማሰራጫ ሁኗል።
ይገርማችኋል ትላንት እንደተለመደው ብአዴኖች በሆቴሉ ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል።
ከተቀመጡት ብአዴኖች ውስጥ ፀጋ አራጌን በአይኔ ብፈልገው አጣሁት።ገና አንድ ጃንቦ እንኳ ወረድ ሳላደርግ አቶ ፀጋ አራጌ ኮቱን ከግራ ትካሻው ላይ ጣል አድርጎ ሲገባ አየሁት።የዕለቱ የአየር ፀባይ ቀዝቀዝ ያለ ነው።ፀጋን ነገር ሙቆት ካልሆነ በቀር ኮት አስወልቆ ትካሻ ላይ የሚያሚስደርግ የአየር ፀባይ አልነበረም።
ፀጋ የኮበሌነት ዘመኑን እና የሰፈሩን ተራራ እያስታወሰ ይመስላል ቀጭን ፉጭት እያፏጨ እነ አገኘሁ ተሻገር፣አብርሐም አለኸኝ እና ጓድኞቻቸው በትልቅ ሞሶብ ክብ ሰርተው ወደ ሚመገቡበት ተጠጋ።ፀጋ የብአዴኖችን ፕሮቶኮል ባልጠበቀ ሁኔታ እንደነገሩ ሰላምታ ከሰጠ በኋላ በአገኘሁና አብርሐም መሐል ገብቶ ተቀመጠ።
የፀጋን ወደ ማዱ መቀላቀል ያየችው አስተናጋጅ በአቶ ፀጋ ጀርባ ጠጋ ብላ ድምጿን ዝቅ አድርጋ”ምን ይጨመር ጋሽ ፀጋ” አለች።
ፀጋ ድምፁን ከፍ አድርጎ “የሰሊጥ ፍትፍት ጨምሪልን”
በፀጋ ትዕዛዝ አስተናጋጇ ግራ ትጋባ እንጂ የብአዴኖቹ ጓድኞቹ ሽሙጥ እንደሆነ ገብቷቸዋል።
ጋሽ “ሰሊጥ ፍትፍት …” ብላ ሳትጨርስ እሽ እሱ ከሌላ “ሰሊጥ በሚሊዮን ተፈርሾ ጨምሪል።”
ፀጋ ይህን ሲናገር ጥግ ጥግ ይዘው ተቀምጠው የነበሩት ወሬ ቃራሚ አክቲቪስቶች በአንድነት በሳቅ አውካኩ።አገኘሁ ፀጋን አሽሙሩን እንዲያቆም በልምምጥ በሚመስል ተመለከተው።ምግቡ ለርሃብ ማስታገሻ ሳይሆን ለደንቡ ከመጠጥ በፊት የሚቀማመስ ሰለነበር ሌላ ጭማሬ ሳያስፈልጋቸው ማዱ ተነሳ።
ማዱን ያነሳችው አስተናጋጅ የሚጠጣ ይፈልጉ እንደሆን ስጠይቃቸው የእነ አገኘሁ ቡድን “ውስኪ” አዘዙ።አቶ ፀጋ ያለ ድሮው ለብቻው “ቮልካ” አዘዘ።መጠጣት ተጀምሯል ቤቱ ሞቅ ሞቅ እያለ ነው።አብርሐም አለኸኝ “አቶ ፀጋ ያለድሮህ ምነው ቮልካ አዘዝህ,,,ውስኪ ያዝና እንመሳሰል እንጂ” አለ።
አመስግናሉ አቶ አብርሃም እኔ የፈለግሁትን ነው የምጠጣው ከእንግዲህ መጠጥም ሀሳብ በየግል ምርጫችን ቢሆን ነው የሚሻለው።ታውቃለህ ውስኪ ያሳስታል ጓድ ውስኪ ጠጥተው አይደል እንዴ አረቄን እጠጣለሁ ለማለት “ሽጉጤን እጠጣለሁ”ብለው የነበረው።ሌላው ቮልካን የመረጡሁበት ምክኒያት ምን መሠለህ ካንፓኒው ቮልካን ሲያመርተው ከሰሊጥና ከብድር ነፃ አድርጎ ነው።አይመስልህም ልጅ አብርሃም? ብሎ ጠየቀው።
የእነ አገኘሁ ቡድን ላብ ላብ አላቸው።ደግነቱ ይህን ሁሉ ጭንቀት የገባው ይመስል የቤቱ አድማቂ አዝማሪ መጀመሪያ በኅዘን ቅላፄ ማሲንቆውን ሲከረክር ከቆዬ በኋላ ቤቱ በትካዜ ሲዋጥበት የማሲንቆውን የዜማ ቅላፄ ወደ ደስታ ቅላፄ ቀይሮ እየከረከረ:
ኧረ አበባ አበባ!
ኧረ አበባ አበባ!
እያለ ሲያዜም…ከቤቱ ከወደ አንደኛው ጥግ ሰሊጥ የተሸከመ ሰው ካርቶን በባነር አሰርቶ የያዘ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ” አማራ እየሞተ እሸሸ ገዳሜ ይቁም፣የአማራ ደም በየቦታው እየፈሰሰ በውስኪ መራጨት ይብቃ❗“እያ አስተጋባ።
አገኘሁ ተሻገር ለሆቴሉ ጋርድ የሚጨኸውን ሰውዬ እንዲያስወጣው በምልክት አሳዬው።ከመቅፅበት ይጮኸ የነበረውን ሰው ሁለት ጋርዶች ማንቁርቱን ይዞው አስወጡት።
የቤቱ ጨዋታ ቀጠለ…አስማሪ ማሲንቆውን እየከረከረ
“አሽበል!!አሽበል ገዳዎ” ይላል የእናገኘሁ ቡድን “አሃው ገዳዎ!” እያለ ይቀበላል።
አሽበል አሽበል ገዳዎ!
አሃው ገዳዎ!
አሸበል ያልሞተበት የለም
አሃው ገዳዎ
አሸበል ያልጎተተ እሬሳ
አሃው ገዳዎ
አሸበል ጨዋታነው እንጂ
አሃው ገዳዎ
አሸበል ሁሉን የሚያስረሳ..አዝማሪው ግጥሙን እየደጋገመ ወደ አገኘሁ ሲመለከት አቶ አገኘሁ ቀጥልበት በሚል ይመስል አንገቱን ነቀነቀለት።
አቶ አብርሃም ተቀበል አለ።አዝማሪው ግጥሙን ለመቀበል ወደ አብርሃም ተጠጋ።
ስንጠጣ ነበረ ውሃ በአንድ ኮዳ
በጣም ያሳዝናል ያመኑት ሲከዳ…
ይቀጥላል…
Filed in: Amharic