በነውረኛነቱ ፋሽስት ወያኔን የሚያስንቀው የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ
አቻምየለህ ታምሩ
የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ ዛሬ ይፋ ባደረገው “የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች” ዝርዝር ሰብሳቢውንና ምክትል ሰብሳቢዋን ኦሮሞ ሲያደርግ ለይስሙላ እንኳን አንድም የአማራ ነገድ ተወላጅ አልተካተተም። በኮሚሽነርነት የተሾሙት የአስራ አንዱ ሰዎች “ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብነት” የሚከተለውን ይመስላል፤
1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ – ሰብሳቢ – [ኦሮሞ]
2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ – ምክትል ሰብሳቢ -[ኦሮሞ]
3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ – [ኦሮሞ +]
4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ -[አፋር]
5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን – [ትግሬ]
6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ – [ደቡብ]
7. አቶ ዘገየ አስፋው – [ኦሮሞ]
8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም – [ደቡብ]
9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር – [ሶማሌ]
10. አቶ ሙሉጌታ አጎ – [ደቡብ]
11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ – [ሲዳማ]
የአፓርታይዱ አገዛዝ ሌላው ነውር የይስሙላው ፓርላማ ከዘረዘራቸው 42 እጩዎች ውስጥ የስም ዝርዝራቸው የሌለውን ብሌን ገብረመድህንን፣ ሙሉጌታ አጎንና አምባዬ ኦጋቶን ኮሚሽነሮች አድርጎ መሾሙ ነው። የይስሙላው ፓርላማም የስም ዝርዝራቸው ከ42ቱ እጪዎች ውስጥ ያልነበሩትን እነዚህን ሰዎች ተቀብሎ ሾመታቸውን አጽድቋል።
አንድም አማራ እንኳን ለይስሙላ ያልተካተተበት አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ የተቋቋመው አማራን ለመታገል በተፈጠረው ብአዴን በሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት ፍቃድና ይሁንታ ጭምር ነው።
የግርጌ ማስታወሻ
********
ከታች የተያያዘውን ዝርዝር ተመልከቱት በህዝብ ድምፅ ተጠቁመው በመስፈርቱ መሰረት ተለይተዋል ብለው ይፋ ካደረጉት የ42 ሰውች ስም ዝርዝር ውስጥ የሌሉ ሦስት ሰዎችን አካትተው ኮሚሽን ብለው አምጥተዋል። ብሔር መዘርዘሩ ስርዓቱ ነውረኛ በሆነ መንገድ የፖለቲካ ጫወታውን ሁሉ የዘር በማድረጉ እንጂ ደመቀ መኮንን ወይም በለጠ ሞላ፣ አገኘሁ ተሻገር ወይም መልዓኩ አለበል አማራ በመሆናቸው ለአማራ ህዝብ እዳ እንጂ እድል አይደሉም። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነሩ አራርሳ መርዳሳ ኦሮሞ ነው የጉጂ አባገዳዎችን የረሸነው እሱ መሆኑን ስታውቅ ነገሩ ግልፅ ይሆንልሃል። የአብይ አህመድ አፓርታይዳዊ ሥርዓት ምን ያህል ነውረኛ እንደሆነ ከሚያሳዩ ነጥቦች አንዱ ይህ ሳይጀመር የከሸፈው ኮሚሽን ነው።