>

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች…!!

እስካሁን ድርድር አላደረግንም።

(አራት ነጥብ)

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች!!

 
ይሄ መንግስት ዘረኛ እንዳልሆነ ብቃት ያለው ማንንም ሰው አምባሳደር አድርጎ ሾሞ አሳይቷል….!!! 
* አሜሪካ ወዳጅ አገር ነው፤
* ለጋራ ጥቅማችን በጋራ እንሰራለን፤
* ኤርትራ ወንድም ህዝብ ነው፤
* ለጋራ ጥቅም ሲባል ልክ እንደሌላው አገር ከኤርትራም ጋር አብረን እንሰራለን፤
* የአባይ ወንዝን በተመለከተ በጋራ ተጠቃሚነት መሰረት መጠቀማችንን እንቀጥላለን፤
*  ግብጽም ሱዳንም ኢትዮጵያም ከወንዙ የመጠቀም መብት አላቸው፤
* እንዳያችሁት ውሃው ሀይል አመንጭቶ መሄዱን ቀጥሏል፤ ወደፊትም ይቀጥላል፤
*  የአምባሳደሮች ምደባ ቅጥር ሳይሆን ሹመት ነው፤
* ሹመቱ ግን የራሱ መመዘኛዎች አሉት፤
*  ባለፉት 30 አመታት ተደርጎ የማይታወቅ አይነት ሹመት ነው የተሰጠው፤
*  ይሄ መንግስት ዘረኛ እንዳልሆነ ብቃትያለው ማንንም ሰው አምባሳደር አድርጎ ሾሞ አሳይቷል፤
* ሳውዲ አረቢያ እንደ መንግስት ሪፎርም እየሰሩ ነው፤
*  ከዚህ ቀደም በሌሎች ዜጎች ሲሰሩ የነበሩትን ስራዎች በራሳቸው ዜጎች ማሰራት ይፈልጋሉ፤ መብታቸው ነው፤
* ዜጎቻችንን በተመለከተ ከሳውዲ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰራን ነው፤
*  ዜጎቻችንን ስንመልስ በጥናት በመለየት ነው፤ ይሄንን ካላደረግን አደገኛ ነው የሚሆንብን፤ ምክንያቱም የሰለጠኑ ገዳዮችም አሉ ይባላልና፤
Filed in: Amharic