>
5:09 pm - Wednesday March 2, 5374

"አዲስ አበባ አትገቡም ሸኖ ላይ አድራችሁ ነገ ወደ አሩሲ ትሄዳላችሁ"  (ፖሊስ - ለተፈናቃዮች)

“አዲስ አበባ አትገቡም ሸኖ ላይ አድራችሁ ነገ ወደ አሩሲ ትሄዳላችሁ” 
ፖሊስ
“የአዲስ አበባ ሕዝብ እንዳረገ ያርገን እንጂ ወደ አሩሲ መሄድ አንፈልግም
ተፈናቃዮች

ስንታየሁ ቸኮል
በከንቲባ አዳነች አበቤ የሚመራዉ ስዉሩ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ  ዜጎችን ማንገላታት ስራዬ ብለዉ ይዘውታል።
ከአዲስ አበባ በግዳጅ ወደ ደብረ ብርሃን የተወሰዱ አማሮች  አዲስ አበባ አትገቡም ሸኖ ላይ አድራችሁ ነገ ወደ አሩሲ ትሄዳላችሁ ተብለዋል።
ከአዲስ አበባ፤ ጃን ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን በግዳጅ የተወሰዱ የወለጋ ተፈናቃይ አማሮች በደብረ ብርሃን ተቀባይ አጥተው ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ መሆኑ ገልፀው ነበር። ይሄን መረጃ በምፅፍበት ሰዓት  በፖሊስ ፓትሮል ተከበዉ   ሜዳ ላይ ወድቀዉ የወገን ያለህ ሕይዎታይችን አደጋ ላይ ነው ድረስልን ብለዋል።
ከአዲስ አበባ ከንቲባ ቢሮ በደረሰ ትዕዛዝ ደብረ ብርሃን ድረስ አጅቦ አስገድዶ የወሰዳቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ወደ አሩሲ እንደሚወስዳቸውም ነግሯቸዉ አዲስ አበባ ሳትገቡ በለሊት አሩሲ ትሄዳላችሁ ተብለዉ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቷል። ተፈናቃዮቹ የአዲስ አበባ ነዋሪ እንዳረገ ያድርገን እኛ አሩሲ አንሄድም በማለት በቁጣ እየገለፁ ይገኛሉ።
ከ338 ተፈናቃዮች መካከል 20ዎቹ የሚያጠቡ አራስ እናቶች ናቸው። ሌሎች 20ዎች ደግሞ ከአንድ አመት በታች የሆኑ ጨቅላ ሕፃናት ናቸው። እንዲሁም 95ቱ ከአንድ አመት እስከ ሦስት ዓመት እድሜ ያላቸው ሕፃናት ናቸው።
እነኝህ በመንግሥት ባለሥልጣናት ከሚደገፈው ኦነግ/ሸኔ ጅምላ ጭፍጨፋ የተረፉ አማሮች አሁንም ድረሱልን እያሉ ነው። “የአዲስ አበባ ሕዝብ እንዳረገ ያርገን እንጂ ወደ አሩሲ መሄድ አንፈልግም” ብለዋል።
Filed in: Amharic