>

አስገዳጅ ስምምነት እስከለለ ድረስ ኢትዮጵያ በምትወስንልን ደምወዝ ሄደን ግድቡን የምንጠብቀው እኛ ግብፃውያኖች እንሆናለን ! (ሱሌይማን አብደላ)

አስገዳጅ ስምምነት እስከለለ ድረስ
ኢትዮጵያ በምትወስንልን ደምወዝ ሄደን ግድቡን የምንጠብቀው እኛ ግብፃውያኖች እንሆናለን !
ሱሌይማን አብደላ

ኢትዮጵያውያን በብዙ ችግርና ፈተና ውስጥ አልፈው፣ በአፍሪካ ትልቁን የኤሌትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ሰርተው በዘመናዊ መንገድ የሀይል ማመንጫ ቁልፍን ሲጫኑት
አየናቸው።
በግድቡ የኤሌክትሪክ ማመንጨት
ግብፅና ሱዳን ምንም አልተረበሹም። አብይ አሕመድ ሁላችንም ተጠቃሚወች ነን እያለ ሲያረጋጋን ነው ነበር። አዎ በርግጥም ልክ ነው በናይል ወንዝ ሁሉም ተጠቃሚ ነው ። ለግብፅ ብቻ ጉዳት ቢኖርም።
አሁን ላይ እኛ (ግብፆች ) በኢትዮጵያ የእጅ መዳፍ ውስጥ እንገኛለን። ምክኒያቱም
መስጠት የሚችል መከልከል ይችላልና ።  ከእሁድቱ የግብፅ ውጭ ጉዳይ  ሚ/ር
መ/ቤት መግለጫ በኋላ እኛ ግብፃውያን የምንጠብቀው ነገር ቢኖር ከህዳሴ ግድብ ውጭ ኢትዮጵያ የምትሰራቸውን ግድቦች ስትጨርስ የሚያወጣውን መግለጫ ብቻ ነው ።
 እሁድለት ከኢትዮጵያዊው ሙሀመድ አልአሩሲ ጋር በነበረን ውይይት ላይ ከእስራኤል ጋ በተያያዘ ለጠየኩት ጥያቄ በምላሹ የከፋ ነበር።
 በአጋጣሚ የተገኘን እድል በግዜው ካልተጠቀምክበት ሁለተኛ አታገኘውም ።
የትራምፕ አስተዳደር በመጨረሻው ሳአት ለግብፅ የሰጠው ዕድል አሁን ላይ የለም ።
ወይም ተመልሶ አይመጣም። የነገ ዋስትናችንን ለማስጠበቅ አስገድጅ ስምምነት እስከከሌለን ድረስ ኢትዮጵያ በምትወስንልን ደምወዝ ሄደን ግድቡን የምንጠብቀው እኛ ግብፃውያኖች እንሆናለን። ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ ኢማድ አልብሔሪ !
በነገራችን ላይ አስገዳጅ ስምምነት የሚሉት ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድቡ ውጭ በወንዙ ላይ ሌላ ፕሮጀክት እንዳትሰራ የሚያግድ ስምምነት ማለት ነው። እንጅ ለግድቡ አይደለም። ግድቡ አሁን ራሱ ዘበኛ ራሱ አጥቂ ራሱን ተከላካይ ግድብ ሆኗል። ማንም ነኪ የለውም። ከጉባ ተራራ ግርጌ ላይ ሆኖ ካይሮን የዝቅዝቅ እያየ ያስጨንቃታል። ካርቱምን ተጠቀሚብኝ
በጨለማ ውስጥ እየኖርሽ ድንብርሽ ላይ ካለሁት የብረሀን ቱርፋት ተካፈይ።
አለዛ አትወላውሊ፣ ከተነሳሁ መጀመሪያ አንቺ ነሽ የጅራፌ መለማመጃ የምትሆኒው እያለ ያፌዝባቸዋል። እነሱም ባፋቸው ይሰድቡትና ያሙት ይሆናል እንጅ ቀርበው አይነኩትም።
Filed in: Amharic