ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
በኦሮሚያ መስተዳድር፤ ሰሜን ሸዋ ዞን፤ ወረጃርሶ ወረዳ፤ ጎሐ ፅዮን አቅራቢያ፣ ጎልጀ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ፣ የካቲት 15 ለ16 አጥቢያ ንፁሃን አማሮችና የክልሉ የፀጥታ አባላት ተገድለዋል። በከተማዋ የአማሮች መኖሪያ ቤትም እየተመረጠ በእሳት ጋይቷል።
ከግድያው የተረፉ የዓይን ምስክሮች እንደገለፁት፣ አማራን ለይቶ በማጥቃቱ እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ተዋናይ ኦነግ/ሸኔ ቢሆንም፣ አማሮችን በመለየቱና ገዳዮችን በማስታጠቅ በኩል የሚሳተፉት የክልሉ ባለሥልጣናትም ጭምር ናቸው።
እነኝህ ሓላፊዎች የአካባቢው ተወላጅ ሳይሆኑ፣ ከሌላ ቦታ የመጡ የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውን ኗሪዎች አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ሰዓት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ወረዳው የገባ ቢሆንም፣ በእነኝህ ባለሥልጣናት መንገድ መሪነት አማሮች የሚገደሉበትን አካባቢ ትቶ አንፃራዊ ሰላም ወዳለበት ቀበሌ ዘምቷል።