ሰበር ዜና
ከአዲስ አበባና ከደብረ ብርሃን የተባረሩ የአማራ ተፈናቃዮች በግዳጅ ከተወሰዱበት ከአሩሲም ተባረሩ!
ባልደራስ
ከወለጋ ተፈናቅለው፤ አዲስ አበባ የሰነበቱ አማሮች በግዳጅ ወደ ደብረ ብርሃን ከተወሰዱ በኋላ ተቀባይ አጥተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው በድጋሜ በግዳጅ ወደ አሩሲ፤ አቦምሳ ወረዳ ተግዘው ነበር። በአሁኑ ሰዓት በወረዳው መርሲ ከተማ ቀበሌ 02 ሜዳ ላይ ተጥለው ይገኛሉ።
ነገር ግን ወረዳው “በጀት የለንም። ከፌዴራል መንግሥትም መመሪያ አልመጣልንምና አንቀበልም” በማለቱ በዚያም ለማረፍ ተከልክለዋል።
ወደ አዲስ አበባ እንዳይመለሱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ያስታወሱት ተፈናቃዮቹ “ቀኑ ጨልሞብን፤ መድረሻው ጠፍቶናል” ብለዋል።
ከዚህ በኋላ ወደ የት እንደ ሚሄዱ የሚታወቅ ነገር የለም።
↵ ፎቶ አዲስ አበባ ሳሉ ያነሳነው