>

ሐገር በዜጎች ሰቆቃ ትታመሳለች፤ የውስጣችን አሮብን ስለ ሩሲያና ዩክሬን እናማስላለን...!!! (ምኒልክ ሳልሳዊ)

ሐገር በዜጎች ሰቆቃ ትታመሳለች፤ የውስጣችን አሮብን ስለ ሩሲያና ዩክሬን እናማስላለን…!!!
ምኒልክ ሳልሳዊ

*… ለብልጽግና ካድሬ ሩሲያ ቅርቡና ብርቁ ነች…!!!
 
 ፑቲን ለሃገሩ ያለውን ግዴታ እየተወጣ ነው። ከሐገር አጀንዳ ይልቅ ተራ የሩቅ እለታዊ ወሬና አጀንዳ የሚበልጥባቸው የብልጽግና ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ በየፖለቲካ ድርጅት ውስጥ የተለጠፉ በርካቶች ናቸው።
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ በርካቶችን እየጎዳ በትግራይ በአማራና በአፋር በከፍተኛ ፍጥነት ንፁሃን እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ ፤ በወለጋ፣ በጉጂ፣ በሸዋ ከፍተኛ የሆነ ጦር ያሰማራው ኦነግ በዜጎች ላይ አሰቃቂ ግፍ እየፈጸመ ባለበት ወቅትና የተፈናቀሉ ዚጎች እየተንከራተቱ ባለበት፣ በምስራቅና በደቡብ ምስራቅ የተከሰተው ድርቅ፣ ዜጎች በኑሮ ውድነት ናላቸው ዞሮ እየተዋከቡ ባሉበት ወቅት ላይና በተወጠሩ በርካታ ችግሮችን ታቅፈን በቆምንበት ወቅት ላይ ይህንን ችግር መንግስት እንዲፈታ ጫና ማድረግ የሚገባው ሁሉ ስለ ሩሲያና ዩክሬይን ጦርነት ሊተርክ ያሞጠሙጣል።
ለብልጽግና ካድሬ ሩሲያ ቅርቡና ብርቁ ነች ። የውስጥ ችግራችንን በሚገባ ለመፍታት ሁላችንም መረባረብ እያለብን ባለበት ወቅት ቸልተኝነት እንደ ካሁን ቀደሙ ዋጋ ያስከፍለናል። ይህ አጀንዳ የሚጠቀምበት አካልም ቢሆን ዘልቆ ለማይሄድበትና መፍትሄ ለማይሰጠው ጉዳይ መማሰኑ ያሳዝናል። በውስጣችን መፍትሄ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ እንደ ዜጋ መነጋገር የሚገባን በርካታ ችግሮች እያሉ ለፖለቲከኞች እየተውን የዜጎችን ሰቆቃ ማራዘማችን አሳፋሪ ነው።
Filed in: Amharic