“በመጨረሻም “ቆሻሻዎቻችን” የዶሮ እርባታ አዳራሽ ውስጥ ከዶሮ ኩስ ጋር ታሽገዋል…!!!”
ዘመድኩን በቀለ
*…. ” ከአሩሲ አቦምሳ አባረዋቸው አዋሽ መልካሳ ወደ ሶደሬ መሔጃ መንገድ ላይ የዶሮ እርባታ አዳራሽ ውስጥ አፍስሰው ቆልፈውባቸዋል! ከዶሮ ኩስ ጋር አስቀምጠዋቸዋል። ቆሻሾች ናችሁ ሲሉ ቆሻሻ፣ እዳሪ፣ የዶሩ ኩስ ላይ ጥለዋቸዋል። በዶሮ ኩስ ሽታ እንዲሰቃዩ ፈርደውባቸዋል….!!!
“…አደባባዩ የትም አይሄድም። ለአደባባዩ ቤተ ክህነቱ በቂው ነው። ወንጌላዊ ነኝ የሚል ከአደባባዩ፣ ከመሬቱ በላይ ሰው ግድ ይበለው። እስቲ ሁለት መስመር ይጻፉልህ። በእሱ ላይ ግርር ብላችሁ አታላዝኑ። በዐቢይ አሕመድ የፓርላማ ውሎው ሆን ብሎ እብድ እብድ መጫዋትም ላይ ጊዜአችሁን በከንቱ አታባክኑ። በአዝማሪት ጂጂ ፎቶም ላይ ተተክላችሁም አትቅሩ። በዩክሬንና ሩሲያ ጉዳይም ላይ ከጣሪያ በላይ አትጩሁ። መጨረሻችሁ አይታወቅምና በዳንኤል ክብረት በፓርላማ ውስጥ መተኛትም አታላግጡ። ይልቅስ በጥቂቱም ቢሆን ባልደራስን ሁኑ። እስክንድር ነጋን ምሰሉ። ስለህዝባችሁ ጥቂትም ቢሆን የሰናፍጭ ቅንጣት ታክልም ግድ ይስጣችሁ።
“…ሰካራም !! እኔ የምለው ከዚህ በላይ ምን ትሆኑ? ከዚህ በላይ ምን ይድረስባችሁ? እንዴት ሰው ዘሩ እየጠፋ፣ እየተንገላታ እንዲህ ድባቴ ውስጥ ይወድቃል? እንደ ኩርድ ሃገር አልባ ከመሆን በላይ ምን ይምጣላችሁ? እንደ ቱትሲ እየታደናችሁ እንደ ዱር እንስሳ እየታደናችሁ በማንም መንገደኛ ወጠጤ ከመገደል በላይ ምን ይምጣላችሁ? ምን አይነት ተፈጠሮ ነው? ኧረ ንቁ። አዚማችሁን ከላያችሁ ላይ በጠበልም በደንገልም ለማላቀቅ ሞክሩ። በሃገሩ ላይ ማረፊያ አጥቶ እንደ ገበቴ ውኃ ከወዲያ ወዲህ ሲዋልል የምታየው ወገንህ ሳያዝንህ ስለ ዩክሬንና ሩሲያ ትጨነቅልኛለህ አይደል? መጀመሪያ ራስህን አድን። ለመፍትሄ ተነሥ። ተንቀሳቀስ።
“…ደግሞ ብአዴን ከዳን ብለህ አታላዝን። ሲጀመር ብአዴን ሲፈጠር ጀምሮ ታማኝህ ሆኖ ያውቃል እንዴ? ዐብን ከዳን ብለህም ኢኚኚ አትበል። የራስህን የማይከዳህ ዐብን ፍጠር። ጊዜ የለህም። አንተ አሁንም ቀልድ ላይ ነህ። ቧልት ላይ ነህ። ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ነህ። ህወሓት በራያ በኩል ድጋሚ ልትወርህ ነው። አንተ አሁንም ከቀበሌ ሊቀመንበር ጋር ድብብቆሽ ትጫወታለህ። በኦሮሚያ የሚኖሩ ዐማሮች ማረፊያ እንዳጣች ነፍስ ከወዲህ ወዲያ ይባክናሉ። አንተ ግን የአዝማሪ ጂጂ ፎቶ ይዘህ ከሳች፣ ጠቆረች፣ አረጀች እያልክ ትንደቀደቃለህ። ምን አይነቱ ጉድ ነህ በማርያም?
“…የጂጂ እህት እኮ የዐቢይ አህመድ ሚንስትር ዴኤታ ናት። ሶፊያ ሽባባውም የዐቢይ አሕመድ መንግሥት አስመላኪ ናት። ማኅሌት ሽባባውም የህወሓቱ ዛዲግ አብርሃ ሚስት ናት። አቶ ሽባባውም የዶክተር ብርሃኑ ነጋው ኢዜማ ካዳሚ ናቸው። በልበል ከጂጂ ፎቶ ላይ አይንህን ንቀልና በራስህ ጉዳይ ላይ አይንህን ትከል። ቸክልም። መቼም አንተ የሚዠልጥህን እንጂ የሚመክርህን አትሰማ። ጉድ እኮ ነው። ሆሆይ…
“…ሰው እንዴት በዚህ መጠን ሽንታም ይሆናል? አልሞትም ለማለት እንዴት ፈቃድ ይጠይቃል? ለማንኛውም “ቆሻሻዎቻችን” ከአሩሲ አቦምሳ አባረዋቸው አዋሽ መልካሳ ወደ ሶደሬ መሔጃ መንገድ ላይ የዶሮ እርባታ አዳራሽ ውስጥ አፍስሰው ቆልፈውባቸዋል። ከዶሮ ኩስ ጋር አስቀምጠዋቸዋል። ቆሻሾች ናችሁ ሲሉ ቆሻሻ፣ እዳሪ፣ የዶሩ ኩስ ላይ ጥለዋቸዋል። በዶሮ ኩስ ሽታ እንዲሰቃዩ ፈርደውባቸዋል። አንተ ድራፍትህን እየለጋህ ስለ ጂጂ ማርጀት ተቀደድ። መስቀል አደባባይ የኛ ነው በል። ድሮስ የማነው? አዲስ አጀንዳ አታላምጥ። መጀመሪያ ወገንህን ታደግ። የሰው ልጅ ከአደባባይ በላይ ነው።
ሻሎም ! ሰላም !