>
5:21 pm - Saturday July 20, 2058

መድረሻ ያጡ የወለጋ 300 ተፈናቃይ አማሮች ወደ አዋሽ መልካሳ ተወስደዋል....!!! (ጌጥዬ ያለው)

መድረሻ ያጡ የወለጋ 300 ተፈናቃይ አማሮች ወደ አዋሽ መልካሳ ተወስደዋል….!!!
ጌጥዬ ያለው

ከወለጋ ተፈናቅለው ከመጡ በኋላ አዲስ አበባ እንዳያርፉ የተከለከሉት አማሮች ዛሬ ሐሙስ የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በግዳጅ ወደ ኦሮሚያ መስተዳድር፤ ምስራቅ ሸዋ ዞን፤ አዋሽ መልካሳ (አዋሽ ጎርጎ) ከተማ ተወስደዋል። ተፈናቃዮቹ በግዳጅ ከተወሰዱበት አሩሲ ዞን፤ አቦምሳ ተባረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ጉዞ ጀምረው ነበር።
ነገር ግን ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን፤ ከዚያም መልሶ በአዲስ አበባ በኩል ወደ አቦምሳ የወሰዳቸው የአዲስ አበባ ሙሉ ፓትሮል ፖሊስ ከልክሏቸዋል። በደብረ ብርሃን እና በአቦምሳ ተፈናቃዮቹን የሚረከበው አካል ያጣው ይኸው ፖሊስ አሁንም አስገድዶ ወደ አዋሽ መልካሳ ከተማ ወስዷቸዋል። 338 ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ሰዓት በከተማው የዶሮ ማርቢያ ክፍል ተሰጥቷቸው ገብተዋል።
 ነገር ግን የከተማው የመንግሥት አመራሮች ስለመፍቀድ አለመፍቀዳቸው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የታወቀ ነገር የለም።
ፖሊሶችና የከተማዋ አመራሮች በጉዳዩ ላይ እየመከሩ ነው።
Filed in: Amharic