>

''----መስማማት ካቃታችሁ በቃ ይገደል!---''' (ፊልጶስ)

”—-መስማማት ካቃታችሁ በቃ ይገደል!—”

ፊልጶስ


ከወለጋ፣ አዲስ አበባ፤ ከአዲስ አበባ  ደብረብርሃን፤  ከደብረብርሃን  አዲስ አበባ፤ ከአዲስ አበባ አርሲ፤ ከአርሲ  መርሲ——- ይቀጥላል።

እቃ ወይም ኮንትሮባንድ እየተጓጓዘ አንዳይመስልን፤ ወይም   የሰላም ተጓዥ፤ አንዳይመስለን።  ትላንት ቤት ንብራት፣ ቤተሰብ  የነበራቸው፣ አሁን ግን የሌላቸው፤  ሰርትው፣ ጥርውግረው ለመንግሥት ግብር እየከፈሉ የሚያድሩ፤ ከመታረድና ከመታገት የተረፋ  ሰላማዊ ዜጋ  ናቸው፤  የሰው ልጅ ናቸው። ግን  አሁን እንደ ሰውም  ሆነ እንደ ዜጋ የሚቆጥራቸውም ሆነ የሚያቸው የለም።   አንድም የሃይማኖት ተቋም ወይም ስብዕና ያለው አካል ሊረዳቸው ቀርቶ መንፈሳዊ መፅናናን እንዲያገኙ  ሊያናግራቸው የፈቀደ የለም።

ትላንት እንደ እኛ ሁሉም ነገር ነበራቸው። አሁን ግን አገር እንኳን የላቸውም። 

ጣሊያን አገር በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኝ የአንድ መቃብር ቦታ መግቢያ በር ላይትላንት እኛም እንደ እናንተ ነበርን።“. የሚል መልዕክት በትልቁ ተፅፎ ይታያል። የወለጋ ተፈናቃዮችም ሆኑ በአገራችን የሚታረዱትና የሚሳደዱት ትላንት እንደ እኔ እንደ አንችና እንደ አንተ ነበሩ።  ‘ርግጣኛ መሆን የሚቻለው በዚህ ከቀጠልን  የግዜ ጉዳይ እንጅ ነገ ቢቀር ከነገ ወዲያ ሁላችንም በየተራ  የወለጋ ተሳዳጅና ተፈናቃዮች እድልም በእኛ ላይ ይፈፀማል።

አገርና መንግሥት ስሌላቸው ለምን ገዥዎቻችን የተባበሩት መንግሥታት ፈቃደኛ ከሆነ ለእነሱ አያስረክቧቸውምወይም በአንድ  ስብሰባ ላይ አንድ አባት ሲናገሩ የሰማሁት  አይፈፀምባቸውምእኒህ አባት በአንድ ስብሰባ ላይ ለታዳሚ የተናገሩት  የሚከተለው ነው፤

ድሮ በደርግ ዘመን በአዲስ አበባ በአንዱ የቀበሌ  አዳራሽ ውስጥ ነው። ስብሰባው  እንድ ዳንኤል (እውነተኛ ስሙ አይደለምስለተባለ ወጣት፤ በወቅቱ  በየቀበሌው የሚኖሩ ወጣቶች ተደራጅተው የማርክስዚም ሌኒንዝም የፓለቲካ ንቃተትምህርት ይሰጣቸው  ነበር። ዕድሜው የደረስ  ወጣት ደግሞ  የማርክስዚምሌኒንዝም የፓለቲካ ንቃተ ትምህርት መከታተል ግዴታ አለበት። ዳንኤል ግን በተደጋጋሚ በዚህ የንቃት ትምህርት አልተገኘምና ክስ ቀርቦበት የቀበሌው ኗሪ ህዝብ ተስብስቦምን ዓይነት ርምጃ  የወሰድበትበሚል መውያየት  ተጀመረና፤ ተሰብሳቢው እየተነሳ  በቅጣቱ ላይ ሃስቡን መስጠት ጀመረ።

አንደኛው ተሰብሳብዳንኤል  ጥሩ ልጅ ስለሆነ ምህረት ይደረግለት።ሁለተኛው ድግሞምህረትማ አየደረግለትም አብዮቱን እየተፈታተነ ስለሆነ ሌላው ቢቀር በእስር ይቀጣ።”   ሶስተኛው ቀጥለእሱን አስሮ ማን ይቀልባል?

 ሊላው ደግሞበገንዘብ ይቀጣ።ብሎ ሲል፤ ሌላው ”  የቅጣቱን ገንዘብ የሚከፍሉት ወላጆች ናቸው፣ በዚህ የኑሮ ውድነት የት አምጥተው ሊከፍሉት ነው?”  

ብዙ የቅጣት ዕይንቶች ቢቀርቡም  በዳንኤል   ቅጣት ላይ መስማማት  ስላልተቻለ ተሰብሳቢው ማጉረምረም ሲጀምር፤ አንድ በሰል ያለ ሰውየ ጉረሮን  ሞርዶ ተሰብሳቢውን ጸጥ ካደረገ በኋላ

 ” ያላችሁትን ሁሉ በደንብ ተከታትያለሁ።  በተሰጠው የቅጣት ሃሳብ ሁሉ በእንዱ እንኳ መስማማት ካቃታችሁ በቃ  ዳንኤል  ”ይገደል!” አለና ተቀመጠ።

እንግዲህ ለእኛዎቹ ከርታታ ዜጎች ገዥዎቻችን  ምን እንደምታደርጓቸው መስማማት ካቃታችሁ፤ የደርጉ ዘመን የቀበሌ ተሰብሳቢ እንዳአሉት   እነዚህ የወለጋ ተፋናቃዮችይገደሉ ከመገደል ተርፈው የመጡ አይደሉ? ምን አልባትም እኮ እነሱ   በአሁኑ ሰዓት እንደ ከብት  ታርደውን እንደ አውሬ ታድነው  በተገደሉት ወገኖቻቸው ይቀኑ ይሆናል?  

ርግጥ እኛ ኢትዮጵያዊ ነን የምንል ከሚታረዱትም ሆነ ከሚንከራተቱ በባሰ በቁማችን ሞተናል።  ሰው በመሆናቸው ብቻ፣ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ፣  የምድርን ፍዳ ሁሉ ሲከፍሉ እያየን  የምንኖር፤ ባለሃብትም ሆነ ባለዝና ነን ብለን ልንመፃደቅ እንችላለን። በእውነቱ የጓድ መንግሥቱን /ማርያም አባባል ልዋስና፤ወደድንም ጠላንም በቁማችን ሞተናል።ሞታችብ ደግሞ በየሰዓቱ፣  በየደቂቃውና  በየቀኑ ነው።

በተለይም ላለፋት አራት ዓመታት ሳያቋርጥ የዘር ማጽዳት  ዘመቻ ሲካሄድ፤ እንዴት እንድም የሃይማኖት ተቋም፣  ድርጅት ወይም ዜጋ ወይም የሰባአዊ መብት ታጋይ ነኝ የሚል ማስቆም ያቅተዋልማስቆም አይደልም ገዥዎቻችንን ቁጭ አድርጎምን እየተደርገነው‘? ” ብሎ  መጠየቅና፤  በዚች አገር ላይ  የሚካሄደውን የዘር ማፅዳት ሊላው ቢቀር ለዓለም ህብረተሰብ ማሳወቅ ይሳናል? በእውንቱ ኢትዮጵያኖች እንደዚህ ረክሰናልእንዲህስ አንሰናል? ነፍሳቸውን ይማረውና ጸጋየ /መድህን  ”እናታለም ጠኑበተሰኘው ተውኔቱ ውስጥአሁንስ አንሰን! አንሰንአይጥ አከልን።የሚል መነባንብ አለ። ግን ያኔው ዘመን የተሻለ ነበር ማለት ነው፤ አይጦች ርስርስ አይበላሉም።

የህዳሴው ግድብ ተገደበ ተባለ። አዎ! ለኢትዮጵያዊ ከዚህ የበለጠ የሚያስደሰተው ነገር የለም።  በተመሳሳይ ለኢትዮጵያዊ የአንድ ዜጋ መገደል  የበለጠ የሚያሳዝነን ሊኖር ባለተገባ ነበር። አሁንማ መታረዱንም ሆነ መሳደዱን  ተለማምደነው የኢትዮጵያዊነታችን  መለያ አድርገነው በተገቢው መንገድ መዘገብና ዜና መሆኑ ቀርቷል።

 ግድያውንም ሆነ መፈናቀሉንና መሳደዱን እንቅልፍ ነስቶን ወሬያችንም ሆነ  ትግላችን በአገራችን ላይ በተሰነዘረው ሰይፍ ላይ በሆነ ነበር።   ይሁን እንጅ በተለይ በዚህ ሰሞን  የዮክሪንና የሩሲያ ጉዳይ በልጦብናል። በየቀኑ ግን ዮኪሪን ከሚሞተውና ከሚፈናቀለው  በመቶ እጅ በበለጠ በአገራችን ላይ  የሰው ልጅ ይገደላል።  ይፈናቀላል። ታዲያየራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለችሆኖ፤ በማያገባን ገብተን በየዩቲየቡና ድህረገፁ የጦርነትና የዓለም ፓለቲካ ተንታኝ  በመሆን  ” የሰው ሊጥእናቦካለን።

 ለመሆኑ ግድብ ተግንብቶ መብራት እንዲኖረን የምንፈልገው፣ መንገድ እንዲሰራ የምናፈልገው በአጠቃላይ ብልጽግና የምንፈልገው ለማን ነውዜጎች  የመኖር መብት ከሌላቸውናአገራቸው፣ አገራችሁ አይደለምከተባሉ እኮ፤ ነገከነገ ወዲያ ያፈርሱታል። ምክንያቱም የኔ የሚሉትን  ማንነታቸውንና መብታቸውን አይደለም ህይወታቸውን  በጉልበተኞችና በጎሰኞች ተነጥቀዋል፤ እየተነጠቁም ነው።  ዛሬ ደካማ ሆነው በገዛ አገራቸው ምጻተኛና ተቅበዝባዥ ቢሆኑም፤   በአገራቸው አገር አልባ እንደተድረጉና በማንነታቸው መታረዳቸው የማይቆም ከሆነ፤  ነገከነገ ወዲያ  ራሳቸውን አደራጅተው ለራሳቸው መብት እንደሚፋለሙ የሚያጠያይቅ እየደልም። 

እያልን ያለነውና ሌት ተቀን የምንቃትተው ግን ይህ ለማንም አይበጅም፤ ተያይዘን እናልቃለን ነው። 

የሰው ልጅ በማንኛውም መንገድ ቢሆን መገደሉና መሳደዱ መቆም አለበት። አሁንም   መንግሥት ነኝ የሚለው  አካል ሃላፊነቱን ወስዶ ነገ ዛሬ ሳይል የዜጎቹን መብት ያስከብር

 ለእያንዳዱ ዜጋ መታረድም ሆነ መፈናቀል፤ ተፈናቅሎም ደግሞ መጠለያ በማሳጣት ማከራትት ኃላፊነቱ የገዥዎቻችን  መሆኑን ለአንዳፍታም አትዘንጉት። ኢትዮጵያዊንም፣ ሃይማኖት አለን የምትሉ ተቋማትም  ለዜጎቻችን ድምጽና ኃይል በመሆን የዜግነታችን ድርሻ እንወጣ። ገዥዎቻችን ፊት ለፊት  ”በቃእንበላቸው።  

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

 

Filed in: Amharic