የፖለቲካ ድኩማኖች አለም አቀፍ ጦርነት በመቀስቀሱ ጮቤ እየረገጡ ነዉ…!!!
ሸንቁጥ አየለ
የአቢይ አሽቃባጭ የፖለቲካ ተንታኞች የሩሲያን ወረራ ጉዳይ የአማራ ህዝብ እልቂት ለማዳፈኛነት ሊጠቀሙበት እየተጯጯሁ ነዉ::እንሱ በጮሁ ቁጥር አብሮ የሚጮህ ብዙ ቁራዎችም አግኝተዋል::
መከራ እና ሰቆቃ ዉስጥ ስለ ወደቀዉ አማራ ትንፍሽ ሳይሉ የሰነበቱት ምናምንቴዎች አሁን ደርሶ የሰበአዊ መብት እና የወታደራዊ ሳይንስ ጠበብት በመሆን የተወለጋገደ ትንታኔ እያዘነቡ ነዉ::
ያዉ የተሰጠዉን አጀንዳ እየለቃቀመ ሲጮህ የሚዉለዉ ብዙሃንም የራሱ ዜጎች/ የራሱ ነገድ የዘር ፍጅት ታዉጆበት አይኑ ስር በአሬመኔዎች ሰይፍና ርሃብ እያለቀ ይሄን ጉዳይ ጥቅጥቅ አድርጎ በመዝጋት የሩቅ ጉዳይ ከንፈር መጣጭ ሆኗል::
—-
ለማንኛዉም ፖለቲካ ካወቃችሁ ነገሩ የግራ የሆነዉ ለምትጨፍሩለት ለአለቃችሁ ለአቢይ ነዉ::
አለቃችሁ አቢይ ወይ ከምዕራብ መወገን ወይም ከሩሲያ መወገን ይኖርበታል::ምዕራባዉያን እግር ስር ወድቆ እየተማጸነ ወልቃይትን እና ራያን ለወያኔ መልሼ ከወያኔ ልታረቅ ብሎ ሲማልድ የሚዉለዉ የአቢይ መንግስት ከምዕራባዉያን በኩል ከእኛ ጋር ነህ ወይስ ከሩሲያና ቻይና ጋር ነህ የሚል ጥያቄ ይቀርብለታል::ጥያቄዉን በአፍ አክሮባት መመለስ አይቻልም::ጠላቶቻችን ሰድበህ እና ረግመህ ከአተገባቸዉ ርቀህ በተግባር አሳዬን ይባላል::
የሩሲያ ወዳጅ ነኝ ብሎ በምላሱ የሚዘላብደዉ የአቢይ መንግስት ከሩሲያም የማረጋገጫ የወዳጅነት ጥያቄ በቅርቡ በግልጽ ይቀርብለታል::ከጥያቄዎቹ አንዱ የተባበሩት መንግስታት በሚያደርገዉ ጸረ ሩሲያ ዉሳኔ የአቢይ መንግስት ዉሳኔዉን ተቃዉሞ ከሩሲያ ጋር እንዲቆም ቃላችሁን ስጡን የሚል ጥያቄ ይቀርብለታል::
አቢይ ደግሞ ሁለቱንም ማድረግ ስለሚፈራ የኩበት ላይ ዉሃ ሆኖ ተንሳፎ ይቀራል እንጂ ሩሲያንም ሆነ አሜሪካንን ወግኖ አይሰለፍም::በአንድ ሌሊት ጨረቃ ሰባት ጊዜ ምልሎ ሰባት ጊዜ በመካድ ስልጣን መጨበጥን እንደ ትልቅ ክህሎት የሚመለከተዉ የኦህዴድ/ኦነግ ሀይል የአማራን ዘር ከምድረ ገጽ ለማጥፋት አለምን በማጨበርበር እንደተሳካለት ሁሉ ሩሲያን/አሜሪካን ለመሸወድ መሞከሩ ግን አይቀርም::
ሆኖም የምዕራባዉያንም ሆነ የሩሲያ ከኛ ጋር ቁም ጥያቄ የአማራን ህዝብ የሚጨፈጭፈዉ/የሚያፈናቅለዉ ኦነግ ሸኔ ነዉ ብሎ ለማታለል እንደመሞከር ቀላል አይሆንም::
የአቢይ መንግስት በሩሲያ/ቻይና እንዲሁም በምዕራባዉያን መሃከል በተፈጠረዉ ፍጥጫ ከሚጎዱት የመጀመሪያ ሀይሎች ዋና እና ቀዳሚዉ ብቻ ሳይሆን ህልዉናዉ የሚያከትምበት ሁሉ ሊሆን ይችላል::
ያገጠጠዉ የአለም አቀፍ ጦርነት እና ግጭት ዉጤት ይሄ ነዉና የአቢይ ጭፍራዎች ብዙም አትደንሱ::ብዙም አትጯጯሁ::