>
5:21 pm - Thursday July 21, 0005

መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ....!!! (መስከረም አበራ)

መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ….!!!

.መስከረም አበራ

በህዝብ መመረጡን በቀን አስርጊዜ ለራሱ የሚነግረው ብልፅግና ፓርቲ “ጠቅላላ ጉባኤ ላደርግ ነው” እያለ ነው። ለጉባኤውም “ከፈተና ወደ ልዕልና” የሚል ስም አውጥቷል ። 
ፓርቲው ለጉባኤው የፈለገውን ስም ቢሰጥ የማይቀይረውን ገበናውን አቶ ፀጋዬ አራጌ ግልፅ አድርገው ተናግረዋል። ለጠየቁት የመርህ ጥያቄ መልሱ የእሳቸው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መሰረዝ ነው።
ፓርቲው በአቶ ፀጋ ላይ የወሰደው እርምጃ  “ፓርቲው የሊቀመንበሩ እና የምክትሉ የግል ንብረት ሆኗል፣መርህ የለም፣ስርዓት ጠፍቷል” ያሉትን ሙግት ትክክለኝነት ግልፅ የሚያደርግ ነው። መርህ ቢኖር ኖሮ አቶ ፀጋ ጥፋት አላቸው ከተባለ እንኳን ከማዕከላዊ ኮሚቴው የሚሰናበቱት በዚህ መንገድ አልነበረም።
 አቶ ፀጋ የተባረሩበት ፍጥነትና አቶ ለማ መገርሳ የተለመኑበት ልመና ርዝመት ሲታይ ደግሞ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ “ፓርቲው የኦሮሞ ነው” ያሉትን ያስረግጣል! ጄነራል ተፈራ ማሞ ለከፈሉት ውለታ የተመለሰላቸው መልስም እንዲሁ የፓርቲውን ባጭር ቀሪነት የሚያስረግጥ ነው!
የሚያስጨንቀው የምንወዳት ሃገራችን እጣ ፋንታ እንዲህ ባለ ፓርቲ እጅ መሆኑ ነው!
Filed in: Amharic