>

ይሄንን ነውረኝነት ለማስቆም መፍትሄው ወደ አጼ ምኒልክ አደባባይ በመትመም ምላሽ መስጠት ነው !!  (ሀብታሙ አያሌው)

ይሄንን ነውረኝነት ለማስቆም መፍትሄው ወደ አጼ ምኒልክ አደባባይ በመትመም ምላሽ መስጠት ነው !!
 ሀብታሙ አያሌው

 

*…. አዲስ አበቤ ሆይ  የኦነጉ ክንፍ የቀጀላን ውሳኔ ሰምተህ ከእምዬ ሀውልት ስር ባትገኝ ማርያምን ታሪክ ይቅር አይልህም !!
                         ************
*…. አባት አርበኞች በአጼ ምኒልክ አደባባይ ባትገኙ ታሪክ ይቅር አይላችሁም !!  የኦነጉን ተወካይ የአብይ አህመድን ሚንስትር ፈርታችሁ ከቀራችሁ የአድዋን ድል እንዳረከሳችሁት ይቆጠራል !!
                         *************
አብይ አህመድ  የባህልና ስፖርት ሚንስትትር አድርጎ የሾመው የአንዱ ኦነግ ክንፍ ሊቀመንበር  ቀጀላ መርዳሳ የዘንድሮው 126ኛው የዓድዋ በዓል በእኔ ሚንስትርነት ዘመን በዳግማዊ ዓፄ ምንሊክ አደባባይ አይከበርም በሚለው አቋም  በመፅናቱ  በዓሉ እስከ ዛሬ ይከበርበት ከነበረው ከዓፄ ምኒልክ አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ እንዲዛወር ተደርጓል።
የኦነጉ ክንፍ የቀጀላን ውሳኔ በመቃወም አንጋፋው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ቅሬታውን ቢያቀርብም ኦቦ ቀጀላ አሻፈረኝ ብሏል። በዚህም መሠረት ለዓድዋ በዓል የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ከብሔራዊ ሙዚዬም ወደ አብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የበዓሉ ማክበሪያ ከምኒልክ አደባባይ ወደ ዓድዋ ድልድይ እንዲቀየር ተደርጓል።
የኦነጉ አቶ ቀጀላ ሀገርን ወክሎ መስራትና ፓርቲን ወክሎ መስራት የተለያዩ በመሆናቸው በቀሩት ሁለት ቀናት  ይሄንን ነውረኝነቱን ትቶ በዓሉ በቦታው እንዲከበር እንዲያደርግ ሊነገረው ይገባል ‼  ከዚህ በቀር አገሩን የሚወድድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዓሉን በመደበኛ ማክበሪያው በአጼ ምኒልክ አደባባይ ለማክበር መትመም አለበት።
አባት አርበኞች በአጼ ምኒልክ አደባባይ ባትገኙ ታሪክ ይቅር አይላችሁም !!
አዲስ አበቤ ሆይ ማርያምን ታሪክ ይቅር አይልህም !!
                             ********
ያስከበረህን ታከብር ዘንድ በምኒልክ አደባባይ ተገኝተህ የአድዋን ድል አክብር !!  የአብይ አህመድ ትዕዛዝ አስፈፃሚው አቶ ቀጀላና ጓዶቹ አድዋል ድልድይ ሥር  ወይም ከላይ  ላይ የወደዱበት ያክብሩ።
የባህል ሚንስትሩ የአደኛው የኦነግ ፍንካች መሪ አቶ ቀጄላ ለሚዲያ በሰጡት ምላሽ … “መንግሥት ድልድዩ ጋር ለማክበር ወስኗል ሌላው የፈለገበት ማክበር መብቱ ነው ሲሉ መልሰዋል።”  ይሄ ጥሩ አጋጣሚ ነው መንግስትና ህዝብ ፈፅሞ የማይገናኝ ህልም ያላቸው ሆድና ጀርባ መሆናቸውን ዓለም እንዲያውቀው ለማድረግ ይረዳል። መንግሥት ድልድይ ስር ህዝብ ምኒልክ አደባባይ ያከብራሉ።   አከተመ
አዲስ አበቤ ሆይ አንተ ግን ምኒልክ አደባባይ ተገኝተህ በእቴጌ መንፈስ  በዓሉን ያላከበርህ እንደሁ ማርያምን  ታሪክ ይቅር አይልህም !!
*********
እውነት እልሃለሁ ምኒልክ ዛሬም ንጉሥ ናቸው !!  በዚህ ገፅ ላይ ስማቸውን ጠቅሼ ፎቶቷቸውን ለጥፌያለሁ…  ኢትዮጵያ ጠል ጠይም ጣሊያኖች ኮሜንት ላይ እያበዱ ሲፈርጡ ትመለከታለህ።  እምዬ ሥማቸው ጠበል ነው። የጣሊያን ውላጆች  እንደ ጋኔን ያጓራሉ እንደ አባቶቻቸው ተሸንፈው ኢትዮጵያ ትቀጥላለች።
👇🏾
አድዋ!!  💚💛❤
ምንሊክ 💚💛❤
ጣይቱ!! 💚💛❤
Filed in: Amharic