‘ብልጽግናዎች በሚቀጥለው ዓመት ይገነባል ካሉት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ጀርባ ያለው ኦነጋዊ ሴራ …!!!”
አቻምየለህ ታምሩ
*… ያደርጉታል ካልነው ያልተፈጸመ ነገር የለም፤ ገና ያልፈጸሟቸው ብዙ ኦነጋዊ ሴራዎችን ደባዎች ይቀሯቸዋል!
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ39 ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው ከ15 ጊዜ በላይ የዓድዋን ድል ክብረ በዓል በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ተገኝተው አክብረዋል። ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያምመመም በ17 ዓመታት የሥልጣን ዘመኑ የዓድዋን የድል በዓል ለ10 ጊዜ ያህል በዳግማዊ ምኒልክ በአደባባይ ተገኝቶ አክብሯል።
የፋሽስት ወያኔው አምበል መለስ ዜናዊ ግን በ21 ዓመታት የአገዛዝ ዘመኑ አንድም ቀን ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ተገኝቶ የዓድዋን የድል በዓል አክብሮ አያቅም። ግዑዙ ኃይለ ማርያም ደሳለኝም በመለስ ዜናዊ ወንበር ላይ ለአራት ዓመታት ተመስሎ የመለስን ራዕይ ሳይበረዝ ሳይከለስ ሲያስፈጽም ቢቆይም አለቆቹ ስላልፈቀዱለት ግን አንድም ቀን የዓድዋን የድል በዓል በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ተገኝቶ አክብሮ አያውቅም።
የዘንድሮው ባለተራ የኦሕዴዱ ዐቢይ አሕመድም ምንም እንኳ ገና አንድ አመቱ ቢሆንም ዓድዋን ላለማክበር የድል በዓሉ በሚዘከርበት እለት እሱ የዋለው አርባ ምንጭ ነበር።
ባለፉት 27 ዓመታት በአገዛዝነት የተሰየሙት ነውረኛ ገዢዎች የዓድዋን በዓል በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ተገኝተው ማክበር ያልፈለጉት አምርረው የሚጠሏቸውን የዳግማዊ ምኒልክን ስም ላለመጥራትና የዓድዋን ድል በዳግማዊ ምኒልክ በሐውልታቸው ስራ መዝከር ስለማይፈልጉ ነው።
ፋሽስት ወያኔ በጉልበትና እና ዓይን ባወጣ መንገድ የጀመረውን ነውረኛነት በብልሃት እና በስልት እያስኬዱት ያሉት የዘንድሮዎቹ ባለጊዜዎች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የዓድዋን መታሰቢያ በአደባባይ ተገኝተው ለማክበር ያቀዱ ይመስላል። ታዲያ ዓድዋን በአደባባይ ለማክበር ያሰቡት በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ተገኝተው አይደለም።
ታከለ ኡማ ትናንትና የዓድዋን ድል መታሰቢያ አስመልክቶ የድሉን መሐንዲስ የዳግማዊ ምኒልክን ሳይጠራ ባደረገው ንግግር ለሚቀጥለው ዓመት ለዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት እደሚሰራ አስታውቋል። ታከለ ይህን ሲናገር ታዳሚው በጭብጨባና በጩኸት አስተጋባ። እነ ታከለ ግን ለሚቀጥለው ዓመት ለዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት እደሚሰራ ሲያስታውቁ ታዳሚው ከሚቀጥለው ዓመት ጀመሮ የዓድዋ የድል በዓል መታሰቢያ በዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ስር እንደማይከበር እየነገሩት እንደሆነ አልገባውም።
ከሚቀጥለት ዓመት ጀመሮ የዓድዋ የድል በዓል መታሰቢያ እነ ታከለ በሚገነቡት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ስር ሲከበር ትናንትና በዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ስር በዓሉ ሲከበር ዞሮ ያላየው ዐቢይ አሕመድ ጭምር ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ በዓሉን ለማክበር አዲስ ወደሚገነቡት የመታሰቢያ ሐውልት የአበባ ጉንጉን ይዞ ይመጣል።
ባጭሩ እነ ታከለ በሚቀጥለው ዓመት ለዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት እደሚሰራ ሲነግሩን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የዓድዋ የድል በዓል በምኒልክ ሐውልት ስር እንደማይከበር እየነገሩን መሆኑን ብዙዎቻቸውን የተገነዘብነው አልመሰለኝም። የነዐቢይ አሕመድ አሰራር የፋሽስት ወያኔ ተቀጥላ ቢሆንም እንደ ፋሽስት ወያኔ ግን በኃይልና ዐይን ባመጣ መንገድ አይደለም።
ፋሽስት ወያኔ የዓድዋ ድል በዓል በዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ስር በድምቀት እንዳይከበር ታዳሚው የሚያውለበልበውን ሰንደቅ አላማና የሚዘፍነውን ዘፈን እስከመምረጥ፤ በወታደር እስከመበተን ደርሰው ነበር። እነ ዐቢይ ግን የዓድዋ የድል መታሰቢያ በዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ስር መከበሩን ለማስቀረት ለዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ ሐውልት ይሰራሉ። በዚህ ተራ ማጭበርበራቸው ሕዝቡን ገደሉን ሳያይ ሳሩን ብቻ እያየ ከገደል የሚገባ እንስሳ አደረጉት!