“የዓድዋ ድል በዓል ምኒልክ አደባባይ ይከበራል”
– የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር
126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ እንደሚያከብር እና ሕዝቡም በተለመደዉ መንገድ በዓሉን በአደባበዩ ለመታደም እንዲገኝ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ገለጸ፡፡
በዓሉ በምኒልክ አደባባይ እንደማይከበር የሚወራዉ ወሬም ከመረጃ ክፍተት እና አለመናበብ የመጣ ነዉ ብሏል ማኅበሩ፡፡
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ለአሚኮ እንደተናገሩት የዓድዋ ድልን እና ምኒልክን መለየት አይቻልም፡፡ አጤ ምኒልክ መላ ኢትዮጵያን አስተባብረዉ የበሰለ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራር ባይሰጡ ኖሮ የዓድዋ ድል አይኖርም ነበር፤ አጤ ምኒልክ በዓድዋ ድል መሪ ተዋናይ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይኾን ለጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና የነጻነት ብስራት ስለኾኑ በዓሉ በእሳቸዉ አደባበይ ይከበራል ብለዋል፡፡
በበዓሉም በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ይቀመጣል፤ መላ ኢትዮጵያዊያንም ከአሁን በፊት እንደሚከበረዉ በአጤ ምኒልክ አደባበይ ተገኝቶ በዓሉን እንዲታደም ነዉ ጥሪያቸዉን ያስተላለፉት፡፡ (አሚኮ)