ዘመድኩን በቀለ
ዓድዋ
ወደ ዓድዋ ሲሄድ ምኒልክ ኑ ካለ፣
አይቀርም በማርያም ስለማለ፣
ታዲያ ልጁ ሲጠራው ምን አለ።
ወይ ሳልለው ብቀር ያኔ
እኔን አልሆንም ነበር እኔ
ምንሊክ ጥቁር ሰው
“…ዘንድሮ የ2014 ዓም የዓድዋ የድል በዓል በመናገሻ ከተማዋ በአዲስ አበባ በአጼ ምኒልክ አደባባይ፣ በእምዬ ምኒልክ ሃውልት ስር አይከበርም። በዓሉን ለማክበር የሚፈልግ በዓሉ ወደ አንኮበር ሸዋ ከመዘዋወሩ በፊት ለጊዜው ወደ ዓድዋ ድልድይ እንዲዞር መደረጉ ተሰምቷል። ይህ የሆነበትን ምክንያት ለማወቅ ብዬ እኔም ዛሬ ጠዋት በምናቤ ከራየን ወንዝ ማዶ ተነሥቼ ወደ አዲስ አበባ ሄጄ በዚያም ባለ ድርሻ አካላትን በሙሉ ሳነጋግር ውዬ ገና አሁን ወደ ማደሪያዬ መመለሴ ነው።
“…በዛሬው ጉዞዬ ላይ ብዙ ባለድርሻ አካላትን ለማነጋገር ችያለሁ። ብአዴኖች “ተወን እንኑርበት” በማለት ለጥያቄዬ ምላሽ መስጠት ካለመፈለጋቸው በቀር ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩን አቦ ቀጄላ መርዳሳን ለጥቂት ደቂቃዎች በሸራተን አዲስ ተገናኝተን ሻይ ቡና እያልን ጠይቄአቸው ነበር። አነን ሂንዱግዱ? ብለውኝም ነበር “ጾም ገብቷል” ብያቸው እሳቸው አነን፣ ፈርሶ፣ አሬራ፣ በድራፍት እየጠጡ ጥቂት አውርቻቸውም ነበር። ለምንድነው? የድል በዓሉን ከአደባባይ ወደ ወንዝ ዳር ወደ ድልይ ላይ ስር ማክበር የለወጣችሁት? ብዬም በጥያቄ ጀመርኳቸው።
“…ኢሂእ… ላሊ ጉርባ… አሉኝ ክቡር ሚኒስትሩ ኦቦ ቀጄላ።
ኢሂእ… ላሊ ጉርባ… እኔ እኮ እነ ዐብይና ሽመልስ ጠርተውኝ ካልጠፋ የሥልጣን ቦታ መርጠው መጀመሪያውኑ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሲያደርጉኝ ቀፎኝ ነበር። እኔ ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ነፃ ለማውጣት ኦነግ ሆኜ እየታገለልኩ ያለሁ ታጋይ አታጋይ መሆኔን እያወቁ ለምን እዚህ ቦታ አምጥተው እንዳስቀመጡኝ አልገባኝም? የምፀየፈውን የኢትዮጵያን ባንዲራ ሁሉ እኮ ነው ያስለበሱኝ። ጂኒዎች። አሁን ደግሞ ብለው ብለው ዕድሜ ልኬን እንደ ሰይጣን፣ እንደ ጨካኝ፣ እንደ ጭራቅ፣ እንደ ወራሪ፣ እንደ ጨፍጫፊ፣ እንደ ሰፋሪ ቆጥረን ለኦሮሞ ህዝብ ስንሰብከው የኖርነው ምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን እንዳስቀምጥ እኮ ነው ሊያደርጉኝ የነበረው። እኔ ያለሁበት የሥልጣን ደረጃ እንዲህ እንዳደርግ ፕሮቶኮሉ እንደሚያስገድደኝ ሳውቅማ የበለጠ በገንኩ። እኔና ድርጅቴ ኦነግ ገና ሃውልቱን አፍርሰን የሃጫሉን ሃውልት በቦታው እናቆምበታለን ብለን ስናስብ ጭራሽ የምኒልክ ሃውልት ስር አበባ ላስቀምጥ? ሃኣ? ቱ! ሞቻለኋ? ሂእ…
“…ስለዚህ ይኸውልህ? ማንነበረ ስምህ? …”ዘመዴ” ምነዴ? … ዘመዴ… ቆቱ አይደለህ እንዴ ግን? የነፍጠኛ ስም ማነው ያወጣልህ? ብቻ ምንአገባኝ። እሱን ሌላጊዜ እናወራለን። አዎ ሃውልቱን አፍርሰን፣ በዓሉንም እዚያው ደብረ ብርሃን እንዲያከብሩት አሽቀንጥረን እስክንልክላቸው ድረስ ዓድዋ ድልድይ ወንዙ ዳር እንዲያከብሩትም አዝዣለሁ። እኔም ምንም እንኳ በበዓሉ ባላምንበትም በዓሉ ወንዝ ዳር ስለሚሆን እንደ ኢሬቻ ቆጥሬ እሬቻን እያሰብኩ ልገኝ እችላለሁ። ያለበለዚያ ግን ዘመዴ ሙት አላደርገውም። ዐቢይ ግን ክፉ መሆኑን እየቆየሁ ነው የገባኝ።
“… ዱጋ ረቢ ዐብይ አሕመድ ግን ሲበዛ ተንኮለኛ ነው። ለስለስ አድርጎ አቅርቦ ከግንብ ያላትምሃል። አቅፎ ስሞም አሳልፎ ይሰጥሃል። ያነካካሃል። ለምሳሌ ዶፍቶር ብርሃኑ ነጋን እንዴት እንዳሾቀው ተመልከት። ዶፍተሩ መሆን የሚመኘውን ሥልጣን ሰጠው። ኢኮኖሚስቱን ሶዬ የትምህርት ሚኒስትርም አደረገው። ብርሃኑ የዕድሜ ልክ ትግሉ ተሳካለት። ቦረቀ፣ ዘፈነ፣ ጨፈረ። ብዙም ሳይቆይ የተማሪዎች ውጤት በኦሮሚያ ተሰርቆ ትምህርት ቤት መጥተው የማያውቁ ልጆች ሁሉ 600 ነጥብ አምጥተው አለፉ። ዐማራ፣ አዲስ አበባ፣ ደቡብና ሌሎች ክልሎች ግን ሾቁ። አሁን ሁሉም ማን ላይ እየጮኸ ነው? ብርሃኑ ነጋ ላይ። እሳት ላይ ነው የጣደው።
“…አቢቹ ጋሽ ብሬን ብቻ አይደለም የሾቀው። የዐብን ሊቀ መንበር በለጠ ሞላን፣ የሱፍ ኢብራሂምን፣ ክሪስንና፣ ጣሂሮን ሁሉ አነካክቶ ነው አፋቸውን ለጉሞ ከሚወዳቸው፣ ተስፋ ከጣለባቸው ህዝብ ገንጥሎ አፈር ከደቼ ያስጋጣቸው። ውይውይውይውይ ያ ረቢ ምን አይነት በላ ነው ግን ያወረደብን። እኔ ግን ከፈለገ ሥልጣኑ ጥንቅር ብሎ ይቀራታል እንጂ አይኔ እያየ በእኔ የሚንስትር ዘመን የዓደዋ በዓል በምኒልክ ሃውልት ስር አይከበርም። ወዮወዮ አኒበዴ አርጊቴ ጉርባ አበባ ጉንጉን ይዤ ምኒልክ ሃውልት ሥር ሳስቀምጥ። ቡፍፍፍ…
“…ታከለ ኡማ እኮ ዓድዋ 00 ፕሮጀክት ብሎ ሲጀምር ብዙ ሰው አልገባውም ነበር። ዓድዋ ዜሮ ዜሮ ማለት እኮ ዓድዋን ዱዋዻ ጀቹዻ በር። ዓድዋ ዜሮ ነው ማለት እኮ ነው። ዓድዋ ባዶ ነው ማለት ነው። ነፍጠኛ ይንጫጫል ተንጫጭቶ ይበርድለታል። ምን አባቱ ያመጠል? ምንም አያመጣም? ማልአባሺ… ገተቲ ወዪ…‼
“…የአዲስ አበባ ህዝብ ግን በቀጥታ ወደ ለመደው አደባባይ ነው የሚተምመው። እና ምን አስባችኋል? የጥንታዊት አርበኞችም በዚያው ነው የሚያከብሩት። እና ምን ትላላችሁ? ብዬም ጠይቄአቸው ነበር።
•…ለጊዜው አሉ ኦቦ ቀጄላ… ለጊዜው ኦነግ ሥልጣን በስውር ያዘ እንጂ በሙሉ ኃይል ሥልጣን የለንም። እናም በወታደሩም፣ በደኅንነቱም፣ በፖሊሱም ውስጥ ሰግስገን አስገባን እንጂ ወደ አክሽን ለመግባት ብዙም አልቻልንም። ቢሮክራሲው አሁንም በነፍጠኛው የተዋጠ ነው። እናም ይሄን ማስቆም አሁን የሚችለው ብልጽግና ነው። ትንሽ ቢያስፈራራ፣ መግለጫ ቢያወጣ ያው ሰዉ ፈሪ ስለሆነ የሚመጣ አይመስለኝም። ደግሞ እንደዚያ እንዳንል የካቲት 23 የኦርቶዶክስ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል ነው። ብዙ ሰው ይመጣል። ይሄ እስክንድር ነጋ ደግሞ አይቀርም። ነፍጠኛ መውጣቱ አይቀርም። እኔ ግን ምን አገባኝ። የእኛን ቄሮዎች እና የብአዴን አጋሰሶችን ይዤ እንደ ኢሬቻ በዓል ድልድዩ ላይ ወንዙ ዳር አከብራለሁ። የፈለገ ይምጣ፣ ያልፈለገ አይምጣ። ለደንታው ነው። ደግሞስ ልሂድ ብል እንጦጦ ላይ የሰፈረው የኦነግ ጦር በመነጥር ሁላ ሊያየኝ እኮ ይችላል። ደግሞም በሃጫሉ አጥንት ላይ መቀለድ ነው። አላደርገውም። ለኪለኪለኪ ኦኦ
“…እኔም ኦቦ ቀጄላን ተሰናብቼ የማታዋ አውሮጵላን ሳታመልጠኝ ልሂድ ብዬ ወደ ጀርመን ወደ ራየን ወንዝ ማዶ ተመልሻለሁ። አይገርምላችሁም ግን?
• ሃሎ አዲስ አበባ የካቲት 23 የት ናችሁ?
ዓድዋ
ወደ ዓድዋ ሲሄድ ምኒልክ ኑ ካለ፣
አይቀርም በማርያም ስለማለ፣
ታዲያ ልጁ ሲጠራው ምን አለ።
ወይ ሳልለው ብቀር ያኔ
እኔን አልሆንም ነበር እኔ
ምንሊክ ጥቁር ሰው
ጊዮርጊስ ፈረሱ ቆሞ ሳይ ድል ቀናኝ ሳልል ዋይ
አባቴ ወኔውን ተኮሰው
ምኒልክ ጥቁር ሰው
ዳኛው ያሉት አባመላ ፊት ሐብቴ ዲነግዴ
ሰልፉን በጦር አሰመረው ፊት ሆኖ በዘዴ “
ኣ ? አዲስ አበባ ! የት ነህ?
ከሜዳው ከአውድማው የተኛውን በሬ
ቆስቁሰው ነካክተው አደረጉት አውሬ