>

ሰበር ዜና:- የካራማራ የድል በዓልን ለማክበር በድላችን ሀውልት የተገኙት እና ለእስር የተዳረጉት የባልደራስ አባላት

ትኩረት ሰበር ዜና

 
አስቸኳይ መግለጫ —ቁጥር 3— የካቲቲ 26/2014 ዓ.ም
 
•ባልደራስ እስረኞች እህልና ውሃ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ!
 
• ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ ተነጥለው ወደ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወሰዱ!
 
·ስንታየሁ ቸኮል ቀለብ ስዩም እና አስካል ደምሌ ከእስር ተለቀቁ!
 

ዛሬ የካቲት 26/2014 ዓ.ም የካራማራ የድል በዓልን ለማክበር በድላችን ሀውልት የተገኙት እና ለእስር የተዳረጉት የባልደራስ አባላት ምግብ እና ውሃ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ጠዋት ቁርስ ያልበሉ ሲሆን፣ ከታሰሩ ጀምሮ ምግብና ውሃ ሊደርስላቸው አልቻሉም፡፡ ለምን እንደዚህ እንደሚያደርጉ የተጠየቁት ፖሊሶች፣ “ከላይ በመጣ ትዕዛዛ ነው” ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቀለብ ስዩም እና አስካል ደምሌ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፣ ቀደም ብለው እስክንድር ነጋ እና ስንታየሁ ቸኮል በመለቀቃቸው፣ 37 የነበረው የታሳሪዎቹ ብዛት ወደ 33 ወርዷል፡፡  በሌላ በኩል፣ ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ የሚባሉ የባልደራስ አባላት ከሌሎቹ እስረኞች ተነጥለው ጊዮርጊስ የሚገኘው አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዷል፡፡
ምንም አይነት የህግ ጥሰት ሳይፈጽሙ፣ ከህግ ውጭ የታሰሩት ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡-
1.      ታምራት በለጠ
2.      ጌቱ መከተ
3.      ቴዎድሮስ ስመኝ
4.      ፍላጎት ፈለቀ
5.      ፍፁም መንገሻ
6.      ኤርሚያስ ብርሃኑ
7.      ዮሐንስ እሱባለው
8.      ናትናኤል ጌታቸው ናቸው፡፡
9.      ፋሲል ማሞ
10.  ፋሲል ውሂብ
11.  ሳሙኤል ዲሚትሪ
12.  አንተነህ አማረ
13.  ሶስና ፈቃዱ
14.  ማህሌት እሸቱ
15.  ቢኒያም ታደሰ
16.  ሰለሞን አላምኔ
17.  ጌጥዬ ያለው
18.  ወግደረስ ጤናው
19.  አንተነህ ሞትባይኖር
20.  መአዛ ታደሰ
21.  አዶኒያስ ገሠሠ
22.  ፍቅረማርያም ሙላቱ
23.  ናትናኤል አቤል
24.  ነብይልዑል ይልማ
25.  ኩራ ገብሬ
26.  አቤል አለምነህ
27.  አለም ደመቀ /አሌክስ ሸገር/
28.  ስንታየሁ ለማ
29.  ብሩክ ጫኔ
30.  ተስፋዬ ከበደ
31.   ዳዊት ንጉሤ
32.   ቴዎድሮስ አንተነህ
33.   ሊዲያ አበበ
Filed in: Amharic