>
5:13 pm - Wednesday April 19, 8023

ርስቱ ይርዳው በፋሽስት ወያኔና በኦሮሙማ ዘመን!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ርስቱ ይርዳው በፋሽስት ወያኔና በኦሮሙማ ዘመን! 

አቻምየለህ ታምሩ

የጉራጌን ማኅበረሰብ  እስካሁን የነበረውን አቋሙን ቀይሮ የኦሮሙማ ሞግዚት መሆን እንዳለበት የመከረው፤ ከአሁን በኋላ የጉራጌ ማኅበረሰብ ኦሮሙማን ከመደገፍ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለውና የጉራጌ ማኅበረሰብ የኦሮሙማ ሞግዙት የማይሆን ከሆነ  ኦሕዴድ/ ኦነግ በቄሮ አጥሮ ከገጠሩ ማኅበረሰብ ጋር እንዳንገናኝ እንደሚያደርገው በድብቅ ተቀርጾ በወጣ ድምጹ ሲናገር የሰማነው ርስቱ ይርዳው “በብል[ጽ]ግና ዘመን የሞግዚት አስተዳደር ቀርቷል” እያለን ነው።
ርስቱ ይርዳው ጉራጌ ሞግዚት እንዲሆንለት የሚጠይቀው ኦሮሙማ በጨቦ ምድር ኦሮምኛ የሚናገር ‘ቢርመዱዳ እንጡቂና’ ወይም ‘ወገናችን ነው ይገብር’ ኦሮምኛ የማይናገር ‘ዲና በሌሣ” ወይም ‘ጠላታችን ነው ይጥፋ’ በሚል የድምሰሳ ፖሊሲ እየተመራ የጨቦን ጉራጌነት ደምስሶ ወደ ኦሮሞነት የቀየረ፣ በጨቦ ምድር የነበረውን ጉራጌኛ ደምስሶ ኦሮምኛን እንደ ዋርካ ያንሰራፋውን አውዳሚ ርዕዮት ነው።
ዛሬ በዘመነ ኦሮሙማ የሞግዙት አስተዳደር ቀርቷል እያለን ያለው ርስቱ ይርዳው ትናንትና  በፋሽስት ወያኔ ዘመን የፋሽስት ወያኔ ሞግዚት በነበረበት ወቅት ጌቶቹ የግንቦት 20 በዓላቸውን 27ኛ አመት ሲያከብሩ በእንግድነት ጋብዘውት  “የግንቦት ሀያ ድል በአገሪቱ  ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት  እንዲረጋገጥ አስችሏል” ያለው ጉድ ነው።
ገራሚው ነገር ርስቱ ይርዳው ዛሬ በኦሮሙማ ዘመን የሞግዚት አስተዳደር እንደቀረ የነበረንም፤ ከዛሬ አራት አመት በፊት በፋሽስት ወያኔ ዘመን  የግንቦት ሀያ ድል በአገሪቱ  ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት  እንዲረጋገጥ እንዳስቻለ የነገረንም በዚያው በዋልታ  ቴሌቭዥን ነው። አንዳንዴ ምናለበት የሚዋሹበትን ሜዲያ እንኳን ቢቀይሩ?
Filed in: Amharic