>

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተደበደቡ፣ ህክምና ላይ ይገኛሉ! (ባልደራስ)

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተደበደቡ፣ ህክምና ላይ ይገኛሉ!
ባልደራስ

 

 ዩኒቨርስቲው ላለፉት 7 ቀናት በውጥረት ላይ ይገኛል!
/
ትላንት መጋቢት 4/2014 ዓ.ም 6 ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ “ነፍጠኛ ዳውን ዳውን”በማለት በሚታወቁ ተማሪዎች ባስነሱት ረብሻ በርካታ ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተደብድበው በሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ትላንት አመሻሹ ላይ “ነፍጠኛ ዳውን ዳውን” የሚሉ ተማሪዎች  ላለፉት 7 ቀናት ሲያደርጉ እንደቆዩ፣ የፀጥታ አስከባሪዎች ካምፕ አቅራቢያ ተሰባስበው ሲመካከሩ ከቆዩ በኋላ፣ በተማሪዎች የመኝታ ብሎኮች /ዶርሞች/ እየዞሩ የክፍሎችን በር በመደብደብ፣ “የአማራ ተማሪዎች ውጡ” በማለት ረብሻ በመፍጠራቸው፣ አንዳንዴም ድብደባ በመፈፀማቸው፣ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ተማሪውቹ ዶርሞች ተሰማርተው ባገኙት ተማሪዎች ላይ ሁሉ በፈፀሙት ድብደባ ብዙ ጉዳት ደርሷል፡፡
ከአድዋ ክብረ በዓል ክብረ ማግስት ጀምሮ፣ በግቢው ማንነቱ ባልታወቀ ቡድን በተበተነ ወረቀት ላይ “ኦሮሞ ተሰድቧል” በሚል መነሻ፣ በአማራ ተማሪዎች ላይ ድብደባ፣ ስድብና ዛቻ ሲፈፀም መሰንበቱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሂደት፣ የግቢው ፀጥታ ኃይል  ህግ ማስከበር ካለመቻሉም በላይ፣ ድብደባ  ከሚፈጽሙ ተማሪዎች ጋር አብሮ ጥቃት እየፈፀመ ስለመሆኑ ለዩኒቨስርቲው አስተዳደር አቤቱታ ቀርቦ እስከመተማመን መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በግቢው ውስጥ እየደረሰ ባለው ጥቃት የተፈጠረው ውጥረት እጅግ በመባባሱ፣ የአማራ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ለመውጣት እስከመገደድ የደረሱ ሲሆን፣ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በበኩሉ የመማር ማስተማሩ ሂደት  እንዳይቋረጥ ችግሩን በማደባበስ ለመፍታት እየሞከረ ይገኛል፡፡
Filed in: Amharic