>

የሕዝበ ውሳኔ ሕገወጥነት እና እጅግ አደገኛነት!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

የሕዝበ ውሳኔ ሕገወጥነት እና እጅግ አደገኛነት!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

አቶ አቢይ አሕመድ በብልጽግና ስብሰባ ላይ ሲናገር “ብልጽግና ‘ሕገመንግሥቱ ይቀየር!’ ከሚሉትም ወገን፣ ‘አይ ፈጽሞ እንዲነካብን አንፈልግም!’ ከሚሉትም ወገን አይደለም፡፡ ውሳኔውን ለሕዝብ እንተወዋለን ወይም ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግበት እናደርጋለን!” ሲል ሰምታቹህታል!!!
መንጋው አልገባውም እንጅ እነ አቶ አቢይ በዚህ ንግግራቸው ያረጋገጡት ነገር ሕገመንግሥት ተብየው የውንብድና ሰነዳቸው እንዲቀየር ፈጽሞ የማይፈልጉና የማይፈቅዱ መሆናቸውን ነው!!!
ነገር ግን በርካታ የዋሃንን ጉዳዩ “ለሕዝበ ውሳኔ ይቀርባል!” መባሉ አስደስቷል፡፡ የሕዝበ ውሳኔው አሸናፊ ድምፅ ግን “ሕገመንግሥቱ አይነካብን!” ወይም “አይለወጥብን!” የሚል የሚሆን መሆኑ ግን እነኝህን የዋሃንና የፖለቲካ ደናቁርት አልገባቸውም!!!
በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ከእነኝህ የዋሃንና የፖለቲካ ደናቁርት ውስጥ “የአንድነት ፖለቲካን እናቀነቅናለን!” የሚሉ ፖለቲከኛ፣ ጋዜጠኛ፣ ተንታኝ፣ ምንንትሴ ተብየዎችም መኖራቸው ነው!!!
ከዚህ ቀደም የፖለቲካ ደናቁርቱ እነ እስክንድር ነጋ ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ ሕዝበ ውሳኔ እንዲሰጥበት አገዛዙን ለመጠየቅ ፊርማ ሲያስባስቡ በነበሩበት ወቅት ለእነሱ የተናገርኩትንና ከዚያ የደንቆሮ ሥራቸው ያስቆማቸውን ሐሳብ ነው አሁንም እዚህ ላይ የምናገረው!!!
የፖለቲካ ግንዛቤያቸውን ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ በየጊዜው update የማያደርጉ ዘገምተኞች ወያኔ ከመምጣቱ በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብና አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ግንዛቤ አንድ ወይም ተመሳሳይ ይመስላቸዋል፡፡ ወያኔ/ኢሕአዴግ መርዞ ማበላሸቱን አያውቁም ወይም አይገባቸውም፡፡ በጣም የሚገርመኝ ነገር ጠባብ ብሔርተኝነትና ዘረኝነት በምናየው ደረጃ ነግሦና ችግሮቹ በዚህ ደረጃ በሀገሪቱ ተንሰራፍቶና ጠንቅ ሆኖ እያዩት እንዴት ሕዝቡ መመረዙ እንደማይገባቸው ነው!!!
በዚህ ወቅት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ንጹሑ ሰንደቅ እንዲሆንም ሆነ ሕገመንግሥት ተብየው እንዲቀየር እንዲሁም ጎሳ ተኮር ፖለቲካውና የክልል መዋቅሩ እንዲቀር የሚፈልገው አማራ ብቻ ነው!!!
በእርግጥ ደቡብ ውስጥም ጥቂት ተጨማሪ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይኖራሉ፡፡ ከአማራ ሕዝብም ቢሆን ገጠር ከከተማ ፀረ አማራው ብአዴን እንደፈለገ የሚነዳውና “ምረጥ!” የሚለውን የሚመርጥ ቀላል የማይባል የማኅበረሰብ ክፍል መኖሩ መዘንጋት የለበትም፡፡ በመሆኑም የአማራ ሕዝብም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ አይደለም በእነኝህ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ማለትም የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ንጹሑ ሰንደቅ እንዲሆን፣ ሕገመንግሥት ተብየው የውንብድና ሰነድ እንዲቀየር እንዲሁም ጎሳ ተኮር ፖለቲካውና የክልል መዋቅሩ እንዲቀር የሚፈልገው!!!
የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በዕለት ተዕለት የpolitical economy እና socio cultural መስተጋብር እንደምትታዘቡት በመርዘኛ የወያኔ/ኢሕአዴግ የጎሳ ፖለቲካ ስብከት ተመርዞና brainwashed ተደርጎ ኢትዮጵያን፣ አንድነቱንና ሰንደቁን ጥሎ “ክልልህ ነው፣ የክልልህ ሰንደቅ ነው!” የተባለውንና ነጠላነቱን እንዲጨብጥ ከዚያም አልፎ እንዲያመልክ ከተደረገ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም የጎሳ ፖለቲካ አየሩን በሞላባትና ገዥ እንዲሆን በተደረገበት ሀገር ሕዝበ ውሳኔ ማድረግ ማለት ውጤቱ አሉታዊ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም!!!
የዋሃኑን የሚያታልላቸው የአገዛዙ ባለሥልጣናት ሳይቀር የሚጠቅሱትና ምንጩ ያልታወቀ “የውሕድ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከኢትዮጵያ ሕዝብ ከ64% በላይ ነው!” የሚለው ጥናት ነው፡፡ ነገር ግን ውሕዱ ኢትዮጵያዊ ይቅርና ከሃያ ሚሊዮን በላይ የሚሆን “ክልልህ ነው!” ከሚሉት ውጭ የሚኖረው አማራ እንኳ አማራነቱን ጥሎ ወይም ቀይሮና የሚኖርበትን አካባቢ ማንነት ይዞ ለመኖር ተገዶ እየኖረ እንዳለ አያውቁም!!!
በመሆኑም የወያኔ ኩሊዎች እነ አቶ አቢይ በሕገመንግሥቱም ሆነ፣ በሰንደቁም ሆነ፣ በጎሳ ተኮር ፖለቲካውና የክልል መዋቅሩ ዙሪያ “ለሕዝብ አቅርበን ሕዝብ እንዲወስንበት እናደርጋለን!” ሲሉ ውጤቱ ምንም ማጭበርበር ሳያስፈልጋቸው የሚፈልጉት ሊሆን እንደሚችል በሚገባ ስለሚያውቁ ነው ጉዳዩን ለሕዝበ ውሳኔ ለማቅረብ የፈለጉት!!!
አቶ አቢይ በብልጽግና ስብሰባ “አማራ ሕገመንግሥቱን አይፈልገውም፣ የራሱ አድርጎ አያስበውም፣ ባልተወከልኩበት ባልተሳተፍኩበት የረቀቀና የጸደቀ ነው ይላል!” ሲል አልሰማቹህትም ወይ??? ከአማራ ውጭ ያለው ግን የአገዛዙን ሕገመንግሥት የህልውና ሰነዱ አድርጎ ነው የሚያስበው!!! ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ነው!!!
እኔ መጨረሻ ላይ ይሄ ማወናበጃ ሊመጣ እንደሚችል አውቄ ገና ድሮ ነው በአገዛዙ ብልሹና ጠንቀኛ ፖለቲካ ምክንያት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲሁም በሕገመንግሥቱና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚደረግ ሕዝበ ውሳኔ ለችግራችን መፍትሔ ሊሆኑ ከማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ከዐሥር ዓመታት በፊት 2006ዓ.ም. ላይ በዕንቁ መጽሔት እና በድረገጾች ላይ አጽንኦት ሰጥቸ ተንትኘ የጻፍኩበት!!!
በነጻነት እና ፍትሐዊነት ስም ወይም ሽፋን ለአንድ የተዛባ ግንዛቤ እንዲይዝ ወይም እንዲያብድ ወይም እንዲደነቁር ለተደረገ ሕዝብ “ሕገመንግሥቱን፣ የጎሳ ፖለቲካውንና የጎሳ ክልል መዋቅሩን ትፈልጋለህ ወይስ አትፈልግም???” የሚል ምርጫ ማቅረብ ማለት ሕዝብን አወናብዶ የማሳሳት የወንጀል ተግባር እንጅ ፈጽሞ የሕዝብን መብት የማክበር ጉዳይ አይደለም!!!
ሲጀመር አደገኛ ወይም ጠንቀኛና እጅግ ኋላቀር መሆኑ ታውቆ ወይም ታምኖበት ከወያኔ/ኢሕአዴጓ ኢትዮጵያ በስተቀር እንኳን በምዕራቡ ዓለም ይቅርና በአፍሪካ እንኳ ጨርሶ የሌለውን የጎሳ ተኮር ፖለቲካ እና የጎሳ ክልል መዋቅር ሌሎች ሀገራት እንዳደረጉት ሁሉ በconsensus ወይም እንደማይጠቅምና ጠንቀኛ መሆኑን ተግባብተን ከፖለቲካችን ማራቅ ይኖርብናል እንጅ ወይም ደግሞ እንደ አንዳንዶቹ ሀገራት በሕግ ደንግገን የብሔረሰብና የጎሳ ማንነትን ለፖለቲካ ፍጆታ እንዳይውል ማድረግ ወይም መከልከል ይኖርብናል እንጅ ጠንቀኛ ወይም አደገኛና እጅግ ኋላቀር መሆኑን መላ ዓለም የሚያውቀውን፤ በዚህም ምክንያት ከአጠገቡ እንዳይደርስ ያደረገውን ጎሳ ተኮር ፖለቲካ እና የክልል መዋቅርን ሕዝብን አንቆ እንዲይዘው አድርገው ካደነቆሩ ወይም ከመረዙ በኋላ “ትፈልገዋለህ ወይስ አትፈግገውም?” ብሎ ለውሳኔ ማቅረብን ምን አመጣው???
ብሔረሰቦችን “አጋር!” እያሉ በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር አድርገው የኖሩትና ከልልነትን ለጥቂቶች ብቻ ፈቅደው ለብዙዎች ግን በመንፈግ ብሔረሰቦችን ሲያሰቃዩ የኖሩትና አሁንም እያሰቃዩ ያሉት የወያኔ ኩሊዎች እነ አቶ አቢይ አሕመድ ይሄንን ስትሏቸው ልክ የብሔረሰቦችንና ጎሳዎችን መብቶች የጠበቁና ያስጠበቁ፣ ለሁሉም ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ዕኩል ፖለቲካዊና ማኅበራዊ መብቶችን ሰጥተው ያረጋገጡ ይመስል ትንሽም ሳያፍሩ “የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣ ቋንቋ ባሕላቸው እንዲጠበቅና እንዲያድግ ስለምንፈልግ ነው!” ብለው ይመልሱላቹሃል!!!
ከዚያም አስከትላቹህ እነኝህን የወያኔ ኩሊዎችና ወስላቶች “ዲሞክራሲ በሰፈነበት በምዕራቡ ዓለም ብሔረሰቦች የሉም ወይ??? ተጨቁነው ነው ወይ የሚኖሩት??? ቋንቋና ባሕላቸውን መጠቀም፣ መጠበቅና ማሳደግ ተከልክለው ነው ወይ የሚኖሩት??? ካልሆነስ ወይም በምዕራቡ ዓለም ብሔረሰቦች መብታቸው ተጠብቆ የሚኖሩ ከሆነስ እኛ ታዲያ ለምን የእነሱን አዋጭ የፖለቲካ መስመር ትተን ይሄንን የያዝነውን አደገኛና ሀገር አፍራሽ ወይም በታኝ መስመርን እንድንከተል ለምን ተፈለገ ታዲያ??? ለምን እንደ የሠለጠነው የምዕራቡ ዓለም የብሔረሰብና የጎሳ ማንነትን ለፖለቲካ ፍጆታ ከማዋል አንቆጠብም??? ማለትም ለምን ጎሳ ተኮር ፖለቲካንና የክልል መዋቅርን ከሀገራችን አናስወግድምና የብሔረሰቦችን መብት የሠለጠነው ዓለም ባስጠበቀበት ከፖለቲካ ውጭ በሆነ ሲቪክ አደረጃጀት እንዲጠበቅ አናደርግም???” ብላቹህ ስትጠይቋቸው ዓይናቸው ይፈጣል እንጅ ጨርሶ መልስ የላቸውም!!!
እናም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የወያኔ ኩሊዎች እነ አቶ አቢይ አሕመድ ሕዝበ ውሳኔ ሲሉህ አስቀድሞ በግድ ወይም በኃይል የጫኑብህን ጠንቀኛውንና መርዘኛውን የጎሳ ፖለቲካቸውን አሁን በአንተ ስምምነት ለዘለዓለሙ እንዳይለቅህ አድርገው ሊጭኑብህና ለዘለዓለም ስትታመስበት፣ ስትታወክበት፣ ፍዳህን ስታይበት እንድትኖር ሊያደርጉብህና ለዚህም በድምፅህ መስማማትህን አረጋግጠህ የኃጢአታቸው ተካፋይ እንድትሆን ሊያደርጉህ ነው እንጅ ለአንተ አዝነውልህ ወይም ደግሞ ተጠቃሚ የምትሆንበት ስለሆነ አይደለምና ንቃ!!!
ወያኔ/ኢሕአዴግ ይሄንን ሕዝበ ውሳኔ ሥልጣን በያዘባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት አድርጎት ቢሆን የሕዝበ ውሳኔው ውጤት የሚያሠጋ ባልሆነ ነበር፡፡ የክፋታቸው ክፋት ግን ያኔ ሕዝብ እንደማይቀበለው ስለሚያውቁ በኃይል ወይም በግድ ጭነውበትና ለሠላሳ ዓመታት ያህልም ሕዝቡን ከትምህርት ሥርዓቱ እስከ እድርና ማኅበር፣ ከሃይማኖት እስከ ፖለቲካ ያሉ አደረጃጀቶችን ተቆጣጥረው ሕዝብን ሲመርዙና ሲግቱ ከኖሩ አመለካከቱንም ክፉኛ ከለወጡ በኋላ ሕዝበ ውሳኔ የሚል ጨዋታ ማምጣት ጥፋት እንጅ ልማት አይደለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ “ሕዝበ ውሳኔ አድርግ!” ሲሉህ “የለም የለም እንደ ያደጉ ሀገራት እንደማይጠቅም አውቀን በመግባባት ከሀገራችን እናስወግደዋለን እንጅ ለማይጠቅምና ጠንቀኛ ለሆነ ኋላቀርና የደነቆረ የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብና የክልል መዋቅር ሕዝበ ውሳኔ ማድረግ አያስፈልገኝም! የማይጠቅም መሆኑ በመላው ዓለም መታወቁ በቂየ ነው!” ብለህ ትዘጋበት ዘንድ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!!
“አይ!” ካልክና “እፈልገዋለሁ!” ካልክ ግን የራስህ ጉዳይ አሳር ፍዳህን ስታይበት ኑር!!!
ለአማራ ሕዝብ ማሳሰብ የምፈልገው ዐቢይ ጉዳይ ግን የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቀኛውን የጎሳ ፖለቲካንና የክልል መዋቅሩን “እፈልገዋለሁ አይቀየርብኝ!” ብሎ በድምፁ ካረጋገጠ አንተም በስደተኛና በወራሪ ተወስዶ የቀረብህ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለው እያንዳንዷ ዐፅመ እርስትህ ወደ አንተ ወደ ባለቤቱ እንዲመለስ ቆርጠህና ጨክነህ መታገል እንዳለብህ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!! መድኃኒቱ ይሄ ነው!!! የቂልነት ዘመን ማብቃት አለበት!!!
Filed in: Amharic