>

"ከጥር ወር ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኝ ወጣት፣ በየካቲት ወር የአድዋ በዓልን አስረብሿል ተብሎ ተከሰሰ....!!!" (ባልደራስ)

ከጥር ወር ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኝ ወጣት፣ በየካቲት ወር የአድዋ በዓልን አስረብሿል ተብሎ ተከሰሰ….!!!”
ባልደራስ

“አፈሳውና ክሶቹ የእነ አዳነች አበቤ በቀል እንጂ የህግ ጉዳይ አለመሆኑ ተመላክቷል…!!!”
/
ከጥር ወር 2014 ዓ.ም በእስር የሚገኝ ወጣት፣ የካቲት 23/2014 ዓ.ም  የተከበረውን የአድዋ በዓል አስረብሿል ተብሎ ባለፈው ሰኞ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
ፖሊስ ወጣቱን ሲከስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ፣”ባለሥልጣናትን ልክስክስ፣ ከሃዲዎች ፣ ከሥልጣን ይውረዱ ብሎ በመንግሥት ላይ አመጽ አነሳስቷል፣ የፈፀመው ወንጀል ከባድ ስለሆነ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ” ብሏል፡፡
ወጣቱ በበኩሉ ለፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ፣ “እኔ የታሰርኹት ከጥር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ነው፣ የአድዋ በዓል ሲከበር እኔ እስር በት ነበርኹኝ፣ እንዴት አድርጌ ነው በአድዋ እና በካራማራ በዓላት ላይ ተገኝቼ የምረብሸው?  የተያዝኹበትን የክስ መዝገብ ፍርድ ቤቱ አስቀርቦ ይመልከትልኝ ” ብሏል፡፡
ተከሳሹ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበውን አቤቱታ አስመልክቶ አስተያየቱን የተጠየቀው ፖሊስ፣ “እውነታውን ቪዲዮ ላይ አይቼ አጣራለሁ” በማለት በሃፍረት ስሜት ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ይህ ክስ በከተማው ውስጥ ያለው የወጣቶች አፈሳና ክስ፣ በአድዋ ክብረ በዓል ተሰደብን የሚሉት እነ አዳነች አበቤ በበቀልነት ስሜት እየተመራ ስለመሆኑ አስረጅ ሆኗል፡፡
እንደ ህጉ ከሆነ፣ ባለሥልጣናትን መሳደብም ሆነ ማዋረድ በጣም ቀላል ወንጀልና በምንም መሥፈርት ለእስር የሚዳርግ አይደለም።
Filed in: Amharic