የትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀ የዘር ፍጅት አዋጅ በአስቸኳይ ይቁም…!!!
ሸንቁጥ አየለ
ኦህዴድ የሚዘዉረዉ የፈደራል መንግስት ወደ ትግራይ የርዳታ ምግብን እንዳይገባ ሁሉንም በር ዘግቷል:: ይሄም የትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀ የዘር ፍጅት አዋጅ ነዉ
-የትግራይ ህዝብ በህይወት የመኖር ሰበአዊ መብቱ ይረጋገጥ ዘንድ የርዳታ ምግብ የሚያገኝባቸዉ በሮች ሁሉ ክፍት ሊደረጉለት ይገባል::
-ኦህዴድ የሚዘዉረዉ የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብ የርዳታ ምግብ እንዳያገኝ ሁሉንም አቅጣጫዎች ዘግቷል::ይሄም በትግራይ ህዝብ ላይ የህልዉና አደጋ ጋርጧል:: ይሄም የትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀ የዘር ፍጅት አዋጅ ነዉ ::
-በዚሁ የኦህዴድ መንግስት የጭካኔ አዋጅ በትግራይ የሚላስ የሚቀመስ የለም::በዚህም የተነሳ ህጻናት እና አቅመ ደካማዎች በትግራይ በብዛት እየሞቱ ነዉ::
–የኦህዴድ ፈደራል መንግስት ወደ ትግራይ የርዳታ ምግብን እንዳይገባ መከልከሉን እና ሁሉንም በር መዝጋቱን በአስቸኳይ ያቆም ዘንድ ጥብቅ ምክር ሊለገሰዉ ይገባል::አለዚያ የትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት አዋጅ በመንግስት ደረጃ እንደታወጀ ይቆጠራል::የዘር ማጥፋት የሚከናወነዉ በልዩ ልዩ መልክ መሆኑ ይታወቃል::
–የእርዳታ ምግብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም የዘር ፍጅት በአንድ ነገድ ላይ ማካሂያድ ታላቅ ሰበአዊ ወንጀል ነዉ::
———————-
–ህዉሃት በፕሮፕፖጋንዳዉ እንደሚነፋዉ የአማራ ህዝብ እና የትግራይ ህዝብ ጠላት ህዝብ አይደለም::የትግራይ ህዝብና የአማራ ህዝብ ወንድማማች ህዝብ እና አንድ ህዝብ ነዉ::በመሆኑን በትግራ ህዝብ መሃል ያላችሁ ልበ ንጹሃን እንዲሁም በአማራ ህዝብ መሃል ያላችሁ ልበ ንጹሃን ፖለቲከኞች/የሀገር ሽማግሌዎች እና ልሂቃን የትግራይ ህዝብ እና የአማራን ህዝብ የማቀራረብ ስራ እንድትሰሩ ይሁን::
-አንዱ የትግራይን ህዝብ እና የአማራን ህዝብ የማቀራረቢያ መንገድ አሁን የትግራይ ህዝብ በኦህዴድ የፌደራል መንግስት የእርዳታ ምግብ እንዳያገኝ በተደረገበት ወቅት የአማራ ህዝብ በልዩ ልዩ መልክ ከትግራይ ህዝብ ጎን በመቆም የትግራይ ህዝብ ሁሉንም የሰበአዊ ርዳታ በተለይም የምግብ እርዳታ እንዲያገኝ ጫና በማድረግ ነዉ::
—–
የአለም ጤና ድርጅት 95 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶቸ ወደ ትግራይ ለማስገባት ቢዘጋጅም የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃድ አለመስጠቱ ገለፀ።
95 ሜትሪክ ቶንየህክምና ቁሳቁሶች ወደ ትግራይ ለማስገባት ብንዘጋጅም እስካሁን የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃድ አልተሰጠንም ሲል የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የአለም ጤና ድርጅት ወደ ትግራይ 2200 ሜትሪክ ቶን የጤና ቁሳቁስች በአስቸኳይ ያስፈልጋል ያለ ሲሆን እስካሁን ግን ወደ ትግራይ መግባት የቻለው የህክምና ቁሳቁስ ግን 117 ሜትሪክ ቶን ብቻ ማድረስ መቻሉን ገልፃል።
ይህም ከሚያስገልገው መጠን አንፃር ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገልፀዋል።
ሰዎች በህክምና እጦት እየሞቱ መሆናቸው የገለፁት ዶ/ር ቴድሮስ ለ46, 000 የኤች አይ ቪ ታማሚ የሆኑ ዜጎች የሚሰጥ የነበረው አገልግሎትሙሉ በሙሉ ቆሟል ብለዋል።
በተጨማሪም የቲቪ ፣ ደም ግፊት ፣ ስካር እና ካንሰር የመሳሰሉ ታማሚዎች ህክምና እያገኙ አለመሆናቸው በመግለፅ እና እየሞቱ እንደሆነም አክለው ገልፀዋል።አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !