>

በእስር ላይ የሚገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶች በምግብ እጦት እና መመረዝ ለህመም እየተዳረጉ ነው ! (ባልደራስ)

በእስር ላይ የሚገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶች በምግብ እጦት እና መመረዝ ለህመም እየተዳረጉ ነው !
ባልደራስ 

የ126ኛው የአድዋ በዓል እና የካራማራ የድል በዓል በድምቀት መከበሩን ተከትሎ  በጅምላ የታፈሱ የባልደራስና የአዲስ አበባ ወጣቶች ከተማ ዳር በሚገኘው  አባ ሳሙኤል እስር ቤት ውስጥ ለከፋ የጤና ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ።
በማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ የመጠጥ እና የንጽህና መጠበቂያ  ውሃ የሌለ ሲሆን ፤ ታሳሪዎች በግፍ ከተሰሩበት ቀን አንስቶ በትላንትናው ዕለት ብቻ፣ ለዚያ ሁሉ እስረኛ በአንድ ውሃ ማመላለሻ መኪና፣በአንድ ዙር፣ በግቢው ውስጥ ለሚገኙ እስረኞች ቀርቧል። በሌሎች ቀናት ምንም ውሃ አልቀረበላቸውም። በዚህም ምክንያት እስረኞች በመጠጥ ውሃ እጥረ፣ እንዲሁም፣ ንጽህና መጠበቂያ ውሃ ባለመኖሩ ለከፋ የጤና ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ።
ከዚህም በተጨማሪ፣ በምግብ እጦት እና መመረዝ ምክንያት  ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በግፍ የታሰሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች ህመምተኛ ሆነዋል ። ማጎሪያ እስር ቤቱ ለጠያቂዎች በሩ ክፍት የሚሆነው በሳምንት ሦስት ቀን ብቻ በመሆኑ ለእስረኞች
በቤተሰብ በኩል ምግብና መጠጥ በተቻለ አቅም እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኗል ።
ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ወጣቶች እስር ሕገወጥ ቢሆንም ፤ በሕግ ጥላ ሥር የሚገኝ እስረኛ ጤናውን የመጠበቅ እና በጠያቂዎች የመጠየቅ መብት የማክበር እና የማስከበር የመንግስት ኃላፊነት ነው።
ይህም በመሆኑ ፤ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች ለሚደርስባቸው ማናቸውም የጤና ችግር ኃላፊነቱን የሚወስደው የአሰራቸው አካል መንግስት መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
Filed in: Amharic