>

ሌላኛው የዘር ማጥፋት...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ሌላኛው የዘር ማጥፋት…!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

*…. የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የዘር ማጥፋት የፈጸሙት እሊህ ሁለቱ ናቸው። በሰይፍ በስለት ከሚጠፋው ትውልድ በላይ በትምህርት ጄኖሳይድ እየተፈጸመበት ያለው ትውልድ ይብሳል። ይበልጣል። 
 
*… 10ኛ ክፍል ላይ 9 የትምህትር ዓይነት A ያመጣ ተማሪ ነው 12ኛ ክፍል ላይ 120 አምጥተሃል ተብሎ የነበረው
ሲፈተሽ 589 ሆኗል።ልጁ ከዚህም በላይ ያመጣል  እያሉ ነው መምህራንና የሚያውቁት ቤተሰቦቹ።

 

 
በአሳፋሪ ሁኔታ የ12 ክፍል የማትሪክ ውጤት እና የመግቢያ ነጥብ ሌላኛው የጄኖሳይድ መሳሪያ ሆኖ የሺዎችን ተስፋ ሲያጨልም፤ ውጥናቸው ሲያመክን ታይቷል ፤ በመሳሪያ በገጀራ በእሳት… አልጠፋ ያለን ህዝብ ተስፋውን በማጨለም ለስደትና ለከፋ ውድቀትና ውርደት የማመቻቸቱ የሴራ አካሄድ ምን ያህል ርቀት  ያስጉዛል? የምናየው ይሆናል።
 አብርሃ ወአፅብሃ መሰናዶ ት/ቤት (መርጡለ ማርያም) 162 አምጥተሃል የተባለው አማኑኤል ፀሐይ በቅሬታ ሲታይ 647 በማምጣቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።
አዴት መሰናዶ 150 አምጥተሃል የተባለው ተማሪ ውጤት እንደገና ተመርምሮ 618 ሁኖ ተገኝቷል።
 ቲሊሊ አጠቃላ
ይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 140 አምጥተሃል የተባለው ተማሪ ውጤት በድጋሚ ሲመረመር 601 ሆኖ ተገኝቷል።
ደቡብ ወሎ ልጓማ ትምህርት ቤት 140 አምጥተሃል ተብሎ ውጤቱ በድጋሚ ሲታይ 601 ሆኖ ተገኝቷል።
“…የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የዘር ማጥፋት የፈጸሙት እሊህ ሁለቱ ናቸው። በሰይፍ በስለት ከሚጠፋው

ትውልድ በላይ በትምህርት ጄኖሳይድ እየተፈጸመበት ያለው ትውልድ ይብሳል። ይበልጣል።
 
ማሳያ እናምጣ።
“…ተማሪ አማኑኤል ፀሐይ ወንድም። በምስራቅ ጎጃም በመርጦ ለማርያም ተማሪ ነው። ተማሪው በተፈጥሮ ራሱ ጎበዝ ነው አሉ። ሰቃይ ይሉታል። በሁሉም ዘንድ የሚጠበቅ ተማሪ ነበር። ቀኑ ደርሶ ተፈተነ።
“…ጄኖሳ
ይደሮቹ ፈተናውን አረሙ። የዚህንም ተማሪ ውጤት አዩ። ዘሩ ሲታይ ዐማራ ነው። ሃይማኖቱ ኦርቶዶክስ። ውጤቱን 162 ሰጡት። ልጁ ደነገጠ። ቀጥሎ ታሞ ሆስፒታልም ገባ።
“… መምህራኑም፣ ቤተሰቦቹም ተጨነቁና ቅሬታቸውን ጠንከር አድርገው አቀረቡ። የአማኑኤል የፈተና ውጤትም እንደገና ሲታይ ግን ውጤቱ አጃኢብ የሚያሰኝ ሆኖ ተገኘ። ፀረ ዐማራዎቹ እነ ብርሃኑ ነጋ የዘፈዘፉበት 162  ነጥብ ሳይሆን እንዲያውም የአገሪቱ ትልቁ ውጤት ሆኖ አረፈው። 647 ነጥብ አምጥቶ ከመላው ኢትዮጵያ

አንደኛ ሆኖ ተገኘ። የሌሎቹም እንደዚሁ ነው። ዐማራን በቢለዋ ብቻ ሳይሆን በትምህርትም፣ ተምሮ ሲጨርስም በሥር እጦት አንከራተው፣ አቀውሰው፣ አሳብደው ይፈጁታል።
“…ይሄን ለማስተካከል መፍትሄው ልክ እንደ ኦሮሞው መታገል ነው። ፌስቡክ ላይ እያለቃቀስክ የምታመጣው አንዳችም ነገር የለም። መረር ማለት ብቻ ነው መፍትሄው። ድል በትግል እንጂ በጉግል አይመጣም። ይኸው ነው።
• ለትምህር ሚኒስቴር ቅሬታ ስታቀርቡ የሚመልሱላችሁን ምላሽ በኮመንት ማስቀመጫ ሰንዱቁ ላይ አስቀምጡልን። ቅሬታ አቅርባችሁ በግድ የተስተካከለላችሁ ተማሪዎች ካላችሁም ጻፉልን። ሌሎቻችሁ ግን ሰብሰብ ብላችሁ በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቅ ነው። ቆፍጠን ብላችሁ እንደ ተማሪ መብታችሁን በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ነው። አከተመ።
Filed in: Amharic