>
5:13 pm - Friday April 19, 1957

• ዐብይ አሕመድ ሆይ እንኳን ደስ ያለህ ‼  (ዘመድኩን በቀለ)

ዐብይ አሕመድ ሆይ እንኳን ደስ ያለህ ‼ 

ዘመድኩን በቀለ

 

*…. መከረኛው ህዝባችን ሆይ እነሱ ቢደብቁንም እኛ እያንገበገበን የምንወያይበት እጅግ  አሳዛኙ የህዝብ ስቃይ ተደብቆ፣ ተሸፍኖ እንዳይቀር የሚፈልጉ ሰብአዊነት መርሃቸው የሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚልኩልኝን የተረጋገጠ መረጃ ብቻ አደርሳችኋለሁ። 
“… ሰሜን ወሎ በዋግ ኀኽምራ ዞን በዝቋላ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃይ የአገው ዐማሮች በራብ መርገፍ ጀምረዋል። ይህ በምስሉ የምታዩት ህጻን ምስጋናው አይናለም ይባላል። በዝቋላ ወረዳ በዘራፊው የትህነግ ቡድን ሥር ካሉት ቅዳሚት ከሚባለው አከባቢ 06 ርዕሰ ገነት ቀበሌ ልዩ ቦታ አልቆዙ ከምትባል ጎጥ ወደ ሰቆጣ ተሰዶ የመጣ ነው።
“… ህጻናቱ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር ይማጸናሉ። የሚቀመስ ዳቦ ለማግኘት ወደ ሰማይ ይማጸናሉ። ሁለት ሦስት ህጻናት አቅፋና ያዘለች እናት እንዴት ታጥግባቸው፤? እንዴትስ ብላ ትታደጋቸው? ለራሷ የምትልሰው የምትቀምሰው የሌላት እናት እንዴትስ ወተት ታመነጭ? ህጻኑ የናቱን የጠወለገ፣ የጠነዘለ ባዶ ቁርበት ጡት ቢጎትት እንዴት ወተት ይውጣው ይላል የዓይን እማኙ ጋዜጠኛ።
“…ዐቢይ አሕመድ በየቀኑ ይደግሳል። የዐማራ ብልጽግና በየቀኑ ይደንሳል። እስክስታ ይመታል። ዐማራና ትግሬ በራብ እየተፈጀ ነው። ህጻናት እያለቁ ነው። መንግሥት የህዝብ ቅነሣ ላይ አጠንክሮ እየሠራ ነው። የስንዴ ማሳ እየጎበኘ ሙድ እየያዘም ነው። ይሄን ጉዳይ ጉዳዬ የሚለው አንድም አካል አልተገኘም። አማራ ሲያልቅ ምድሪቱን ለመውረስ መኔና ወሄ በአንድ እግሩ ቆሞ፣ በጥፍሩ ቆሞ እየጸለየ ነው።
“…ዐማራ በጦርነት ወደመ። ተማሪዎቹ እንዳይማሩ በጅምላ ጄኖሳይድ ተፈጸመባቸው። አሁን ደግሞ በራብ እየተቀጠፉ ነው። እየተጠረጉ እየጸዱ ነው። ከዐማራ ነፃ የሆነች ኢትዮጵያ ለማን እንደምትሆን አብሮ ማየት ነው። ራቡ አዲስ አበባም መግባቱ እየተነገረ ነው። የኦሮሞ ብልጽግና ካድሬና ባለሥልጣናት ቤት አንጂ ሁሉም ቤት ራብ በሩን እያንኳኳ ነው። ብልፅግና ግን ድግስ ላይ ነው። ኢሳት ስድብ ላይ ነው። ሃገር ግን በራብ እያለቀ ነው።

“…ምግብ ለተራቡ ሁሉ  !!

Filed in: Amharic