>

ጥያቄ...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ጥያቄ…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

 

በተለይ የኦርቶዶክስ አማኞች፤ እስኪ ስለ እግዚያብሔር ስትሉ እውነቱን እንነጋገረ፤ የህሊናም ፍርድ ስጡ፤
ከብጹ አቡነ ማትያስ እና ከሙሃዘጥበባት ዳንኤል ክብረት፤
– ባለፉት አራት አመታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ አሰቃቂ የመብት ጥሰቶችን በአደባባይ ወጥቶ ውጉዝ ከመ አርዮስ ብሎ በይፋ ያወገዘ ማነው?
– ምዕመናንና ንጹሐን ዜጎች በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በሐረር፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ፣ በትግራይ፣ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሲገደሉና ሲሳደዱ፣ አድባራት ሲቃጠሉ እንባ አውጥቶ በአደባባይ እያለቀሰ ድርጊቱን የነቀፈና በመግለጫ ያወገዘ ማነው?
– አገሪቱ በጭንቅ በተያዘችበት ወቅት ምዕመናንን ለጸሎት፣ ለጾምና ለሱባዓ የጠራ፣ ቤተክርስቲያን በተለየ ሁኔታ ስትጠቃ ድርጊቱን በይፋ አውግዞ መንግስትን የወቀሰና ሹሞችን የተጋፈጠ ማነው?
ሙሃዘጥበባት ዳንኤል በኢሳት ቀርበው ከወዳጄ ወንድማገኝ ጋሹ ጋር ያደረጉትን አስደንጋጭ ቃለ መጠይቅ ከሰማሁ በኋላ አይምሮዮ ውስጥ የተፈጠሩ ጥያቄዎች ናቸው። ውይይቱ እጅግ ፈር የሳተ ስለመሰለኝ ድንገት እኔ ተሳስቼና ያመለጠኝ ነገር ካለ በሚል ነው እነዚህን ጥያቄዎች ያነሳሁት። ከስድብ መልስ ሁሉንም ሀሳብ እቀበላለሁ። ለህሊናችሁ እና ለእግዚያብሔር ስትሉ እውነቱን መስክሩ። ከቻላችሁ ማስረጃ እያጣቀሳችሁ። የእኔን ግምገማ በሰፊው እመለስበታለሁ።
Filed in: Amharic