>

በእስር ቤት 'የአድዋን ቲሸርት አናወልቅም!" ያሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ተከለከሉ !! (ባልደራስ)

በእስር ቤት ‘የአድዋን ቲሸርት አናወልቅም!” ያሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ተከለከሉ !!
ባልደራስ

 *… ፍርድ ቤት ለቀረቡት  የአ/አ ወጣቶች ዋስትና ተፈቀደላቸው!
 
በደረጀ ይበይን የክስ መዝገብ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡት የአዲስ አበባ ወጣቶች በ7000 ብር ዋስትና እንዲወጡ ተወስኗል!
 
በዚህ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል፣ 4ቱ ዛሬ ጠዋት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ አውቶብስ ላይ ሊመሳፈር ሲዘጋጁ፣ የለበሱትን የአድዋ ቲሸርት እንዲያወልቅ ሲጠየቁ እምቢ በማለታቸው ፍ/ቤት እንዳይቀርቡ ተከልክለዋል።
በደረጀ ይበይን የክስ መዝገብ ዛሬ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተይዞላቸው ከነበሩት የባልደራስ እና የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል አራቱ የአድዋ ክብረ በዓል ቲሸርትን አድርጋችሁ ፍርድ ቤት መቅረብ አትችሉም ተብለው ዛሬ ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ተደርገዋል፡፡ ከልካዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነው ተብሏል።
የድዋን ቲሸርት አናወልቅም ብለው ፍ/ቤት የተከለከሉት ወጣቶች ፡-
1.  ቢኒያም ታደሰ
2.   ሳሙኤል ዲሚትሪ
3.    ደረጀ ይበይን
4.  አስጨናቂ ተስፋዬ ናቸው፡፡
አንሰበርም! አንሸነፍም!
Filed in: Amharic