>
5:18 pm - Wednesday June 15, 5166

በጅምላ ሲጨፈጭፉ “ኦነግ ሸኔ”፤  መከላከል ሲገጥማቸው ደግሞ “የኦሮሞ ልዩ ኃይል”. . . !!! (አቻምየለህ ታምሩ)

በጅምላ ሲጨፈጭፉ “ኦነግ ሸኔ”፤  መከላከል ሲገጥማቸው ደግሞ “የኦሮሞ ልዩ ኃይል”. . . !!!
አቻምየለህ ታምሩ

 

*…. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት “ለስራ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የምንጃር ፅንፈኞች አግኝተዋቸው ገደሉብኝ” ሲል የጥልቅ ሃዘን መግለጫ ያወጣላቸው  የቡድን መሳሪያ ታጣቂዎቹ  “ሰራተኞች” ምንጃር ምን አይነት ስራ ነው የሚሰሩት?????? ወይስ ዕመት ኦሮሚያ አማራ ክልልንም ማስተዳደር ጀመረች????!!!
ፋሽስት ወያኔዎች ወራሪ አንበጣ ሠራዊታቸው በወረራቸው በወሎ፣ በጎንደር፣ በሸዋና በአፋር ግፉዓንን በጅምላ ሲጨፈጭፍ የትግራይ ሠራዊት ድል እንደቀናው በሰበር ዜና ያበስራሉ፤ ወራሪ አንበጣ ሠራዊታቸው በተወራሪው ሕዝብ ዘንድ ጠንካራ መከላከል ሲያገጥመው ግን “ሰላማዊ  ተጋሪዎች ተገደሉ” እያሉ ኒማ ኢልባጌርን ሳይቀር በሲ.ኤን.ኤን. የፈጠራ ዶክመንተሪ ያሰራሉ።
 ከነ ትንሽነቱ የፋሽስት ወያኔ የመንፈስ ልጅና ታናሽ ወንድም የሆነው የኦሮሙማ ናዚያዊ የአፓርታይድ አገዛዝ ደግሞ የመከላከያ ሠራዊቱን ትጥቅ እያስታጠቀ የሚያሰማራው የኦነግ ንጹሐንን ጨራሽ ሠራዊት የአማራ ተወላጆችን እየለየ በጅምላ ሲያርድና ሲጨፈጭፍ “ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጸሙ፤ ጥቃቱ ግን በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ አይደለም” የሚል መግለጫ ያወጣል፤ ተወራሪው ሕዝብ ከናዚ ኦነግ የጅምላ ፍጅትና ጭፍጨፋ ራሱን ሲከላከል ደግሞ “የኦሮሞ ልዩ ኃይል አባላት ተገደሉ” ብሎ መግለጫ ያወጣል፤ በሚቆጣጠራቸው ልሳኖቹ፣ በየማኅበራዊና መደበኛ ሜዲያዊቹ ካድሬዎቹን አሰማርቶ “በኦሮሞ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈጸመ” እያለ ሙሾ ያስወርዳል።
ባጭሩ መጣ የሚባለው ለውጥ ወራሪ አንበጣ ሠራዊታቸው ንጹሐንን በጅምላ ሲፈጅ  “የትግራይ ሠራዊት”፤ መከላከል ሲገጥማቸው ደግሞ  “ተጋሩ ሲቪሎች” እንደተገደሉ የሚያውጁ ፋሽስቶች፤  በጅምላ ሲፈጁ “”ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች” ግፋ ካለም “ሸኔ”፣ መከላከል ሲገጥማቸው ደግሞ “የኦሮሞ ልዩ ኃይልና ኦሮሞ” እንደተገደለ መግለጫ እያወጡ የግፉአንን ጩኸት የሚቀሙ የራባቸውና ሁሉ ብርቁ የሆኑ አረመኔዎች በመንግሥትነት የተሰየሙበት የወሮበሎች መፈራረቅ ነው።
Filed in: Amharic