>

የሰላ ትችት በማቅረቡ ብቻ  ለወራት በግፍ እስር ቤት የከረመው  ጋዜጠኛ ታምራት ተፈታ...!!!  (ተራራ ኔትዎርክ)

የሰላ ትችት በማቅረቡ ብቻ  ለወራት በግፍ እስር ቤት የከረመው  ጋዜጠኛ ታምራት ተፈታ…!!! 

ተራራ ኔትዎርክ

የተራራ ኔትዎርክ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከ118 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ መጋቢት 28, 2014 በዋስ መፈታቱን ስንገልጽ ታላቅ እፎይታ ይሰማናል።
ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከዘጠኝ ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ ወደሚወዳት አገሩ ተመልሶ ተራራ ኔትዎርክ የተሰኘ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን በማቋቋም ለግማሽ ክ/ዘመን ሲሸረሸር የቆየውን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለማሳደግ የተቻለውን ያህል ሲጥር ቆይቷል።
ጋዜጠኛ ታምራት በዚሁ ስራው ላይ ሳለ ታህሳስ 01/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከተወሰደ በኋላ በገላን ፖሊስ ጣቢያ እና በዳለቲ ማረሚያ ቤት ከሶስት ወራት በላይ በእስር መቆየቱ ይታወቃል።
ከመጋቢት 2 ቀን 2014ዓ.ም. ጀምሮ የጋዜጠኛውን የዋስ መብት ጥያቄ ሲመረምር የቆየው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት በዋለው ችሎት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቅ በወሰነው መሠረት ዛሬ መጋቢት 28, 2014 ውሳኔው ተፈጻሚ ሆኗል።
ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በእስር ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከጎናችን በመቆም በተለያዩ ሚዲያዎች የፍትሕ ጥያቄ በማንሳት በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችሁ ያለእረፍት ቅስቀሳ በማድረግ በግልፅና በተለያዩ መንገዶች ታምራት እንዲፈታ በመጠየቅ እንቅስቃሴ ስታደርጉ የነበራችሁ እንዲሁም በሃሳብ በገንዘብና በተለያዩ ማቴሪያሎች ድጋፍ ስታደርጉልን ለቆያችሁ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ ከልባችን ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።
እግዚአብሔር በመልካም ያስባችሁ
ቤተሰቦቹ!
Filed in: Amharic