ሞኝና ወረቀት ያስያዙትን አይለቅም!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሹምየ “አንደበት!” በሚባለው ዝግጅቱ አቶ መራራ ጉዲናን እንግዳ አድርጓቸው ነበር፡፡ አቶ መራራ ከተናገሩት የሚበዛው የተሳሳተ በመሆኑ ብዙ ያስጽፍ ነበር፡፡ ከጊዜ አንጻር ግን በሁለት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፡
አቶ መራራ ጉዲና “ኦሮሞ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ተለይቶ ተበድሏል ብለው የሚያስቡት ጉዳይ ምንድን ነው?” ተብለው ሲጠየቁ “ጭሰኝነት በአማራ አልነበረም በኦሮሞና በደቡብ ግን ነበረ፣ በቋንቋችን አንዳኝም ነበረ!” ብለው ሁለቱን ነገሮች ጠቀሱ!!!
የዚህን ጽሑፍ ርእስ “ሞኝና ወረቀት ያስያዙትን አይለቅም!” ያልኩበት ምክንያትም ይሄው ነው፡፡ ማለትም ከላይ አቶ መራራ ያነሧቸው ሁለት ክሶች ኢትዮጵያን ቀውስ ውስጥ መክተት የፈለጉ ምዕራባውያኑ ያን ሞኝ ትውልድ “ፊውዳል!” የሚለውን የራሳቸውን ሀገር ችግር ወይም የፖለቲካ ደዌ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ አስመስለውና ተማሪው ሊታገለው የሚገባ አድርገው አስጨብጠውት የቀረና ያ ትውልድ አሁንም ድረስ እውነታውን ከመካድና እውነታውን ለመረዳት ካለመፈለግ የሚሰነዘሩ ሐሰተኛ ክሶች በመሆናቸው ነው!!!
እውነታው ግን የፊውዳል ሥርዓት በአውሮፓ ውስጥ እንጅ በኢትዮጵያ ውስጥ አልነበረም፡፡ እርግጥ ነው 83 ዓመት በቆየው በዘመነ መሳፍንት ጭልጥ ብለን ልንገባበት ምንም ያህል አልቀረንም ነበር፡፡ በፊውዳል ሥርዓት የየጎጥ ገዥዎች መሳፍንት እንጅ ሀገርና መንግሥት የሚባሉ ነገሮች የሉም፡፡ መሳፍንቱ በጎጣቸው ውስጥ ያለው ሕዝብና ንብረት በሙሉ መብትና ነጻነት የሚባል ነገር የሌለው ሆኖ እንደፈለጉ የሚያደርጉት፣ የሚሸጡ የሚለውጡት የግል ንብረታቸው ነው!!!
እንዲህ ዓይነት ሥርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የታየው ከግራኝ አሕመድ ወረራ ጋር በተያያዘ ማዕከላዊ መንግሥት በግራኝ ጦር ከሸዋ ተፈናቅሎ ወደሰሜን ኢትዮጵያ ተገፍቶ ከመሔዱና ከ15 ዓመት በኋላ ወረራው ከተቀለበሰ በኋላም ሸዋ የተመለሰው ማዕከላዊ መንግሥት በአቅም ማነስ ምክንያት ሊመልሰው ባልቻለው ከሸዋ በታች በነበረው የሀገሪቱ ግዛት እንዲሁም የግራኝ ወረራ የፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ከሱማሌ ቤናዲር እንዲሁም ከኬንያ በኩል ተነሥተው ወደ ሀገሪቱ መግባት በቻሉትና ሰፊውን የሀገሪቱን ክፍል የመያዝ ዕድል ባገኙት ኦሮሞዎች ለሦስት መቶ ዓመታት ለሚያህል ዘመን ዐፄ ምኒልክ ይሄንን የሀገሪቱን ክፍል መልሰው እንደገና እስኪቀላቅሉት ድረስ ከማዕከላዊ መንግሥት ቁጥጥር ርቆ በነበረው በዚህ የሀገራችን ክፍል ነበር የፊውዳል ሥርዓት የነበረው!!!
በዚህ ሦስት መቶ ዓመታትን ለተሻገረ ዘመን ለምሳሌ ዐፄ ምኒልክ አካባቢውን ከመለሱት በኋላ በአዋጅ እስኪያስቆሟቸው ድረስ ከትልቁ አባ ጅፋር እስከ ትንሹ ጅማ አባ ጅፋር በምሥራቅ አፍሪካ ስመ ጥር የሆነ የባሪያ ንግድ ማዕከል ነበሩ!!! ዐፄ ምኒልክ ይሄንን የሀገሪቱን ክፍል መልሰው ባይቀላቅሉትና የባሪያ ንግዱን ባያስቆሙት ኖሮ እነ አባጅፋር ኦሮሞውን ሁሉ ሸጠው ጨርሰውት ነበር!!!
ትልቁ አባጅፋር የዓረብ ነጋዴ ሲሆኑ አካባቢው ከማዕከላዊ መንግሥት እጅ መውጣቱ የፈጠረላቸውን ክፍተት በመጠቀም የባሪያ ንግድ ሰንሰለት በአካባቢው ለመዘርጋት ከዓረብ መጥተው ወደ ሀገራችን የገቡ የዓረብ ተወላጅ ናቸው፡፡ ዓረብ መሆናቸውን የጅማ አባጅፋር የልጅ ልጃቸው በጻፉት መጽሐፍ ተገልጧል!!!
ከዚህ ሌላ ከላይ እንደጠቆምኩት ጎንደር የነበረው ማዕከላዊ መንግሥት መዳከሙን ተከትሎ ከ1762ዓ.ም. እስከ 1845ዓ.ም. ድረስ ለ83 ዓመታት ሰፍኖ በነበረውና ዐፄ ቴዎድሮስ ድምጥማጡን ባጠፉት ዘመነ መሳፍንት ወቅት ወደ ፊውዳል ሥርዓት ጭልጥ ብለን ልንገባ ምንም ያህል አልቀረንም ነበር፡፡ መሳፍንቱ ከዚህ ስመ ጥር የጅማው የባሪያ ንግድ ባሮችን እየገዙ መጠቀም ጀምረው ነበር፡፡ ከዚያ በፊት በነበረው ልማድ ግን ባሪያ ተደርጎ በግዞት የሚያዘው በጦርነት የተማረከ ጠላት ነበር፡፡ መሳፍንቱ ከጅማው የባሪያ ንግድ የገዛቸውንና የሚያሻሽጧቸውን ባሮች ዐፄ ቴዎድሮስ ነጻ እንዲወጡ ማድረጋቸው ይታወቃል!!! ከእነኝህ ሁለት ተሞክሮዎች ውጭ የፊውዳል ሥርዓት በኢትዮጵያ ምድር አልነበረም፡፡ በእነዚህ ሁለት ተሞክሮዎችም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግሥታት በሌሉበት የተፈጸመ በመሆኑ ተጠያቂ ወይም ተወቃሽ አለመሆናቸው ግልጽ ነው!!!
ወደ አቶ መራራ ክስ ስመለስ ጭሰኝነት ከኦሮሞና ከሌሎችም በከፋ መልኩ በአማራ እንደነበረ መረዳት ከፈለጉ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ፍቅር እስከመቃብር በሚለው መጽሐፋቸው የአማራ ገበሬ በምን ዓይነት የመረረ የጭሰኝነት ሕይዎት ይኖር እንደነበረ ገልጸውታልና ይሄንን መጽሐፍ ቢያነቡ መልካም ነው፡፡ ልብ በሉ ጭሰኝነት መኖር ማለት የፊውዳል ሥርዓት መኖር ማለት አይደለም!!!
እርግጠኛ ነኝ አቶ መራራ የሐዲስ ዓለማየሁን ፍቅር እስከመቃብር መጽሐፍ ሳያነቡ ቀርተው ወይም ጭሰኝነት ከሌላው በከፋ መልኩ በአማራ እንደነበረ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም እንዳልነበረ አድርገው እየተናገሩ ያሉት፡፡ ነገር ግን ይሄንን ሐሰተኛ ክስ ካላሰሙ በስተቀር ፖለቲካቸውን ውኃ ስለሚበላባቸውና መቆሚያ ስለሚያጡ ነው ፈጥረው ሲያወሩ የኖሩትና አሁንም እያወሩ ያሉት!!!
እዚህ ላይ ጭሰጭነት እንዴት እንደተፈጠረ ማየቱ መልካም ይመስለኛል፡፡ እንደምታውቁት በቀድሞ ዘመን የመንግሥት ተዋጊዎች ወይም ወታደሮች ደሞዝ አልነበራቸውም፡፡ ደሞዛቸው መሬት መሰጠት ነው፡፡
ዐፄ ምኒልክ በግራኝ አሕመድ ወረራ ምክንያት ከማዕከላዊ መንግሥት እጅ ወጥቶ ወይም እርቆ የነበረውን የሀገሪቱን ክፍል ከመለሱ በኋላ ከአድዋ ጦርነት መልስ በጦርነቱ ለተዋጉትና የሀገራቸውን ነጻነት ላስከበሩ የሸዋ አርበኞች የደም ዋጋ መሬት የሰጧቸው በግራኝ አሕመድ ወረራ ምክንያት ከማዕከላዊ መንግሥት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወይም እርቆ ከነበረውና ከመለሱት የሀገሪቱ ክፍል ነው፡፡ ለጎንደር፣ ለጎጃም፣ ለወሎ፣ ለትግራይ አርበኞች ግን በዚያው በየአካባቢያቸው ነበር የደም ዋጋቸውን ወይም ሀገሪቱን ከጣሊያን የቅኝ ግዛት ወረራ ነጻ ላወጡበት ውለታቸው መሬት የሰጧቸው!!!
ዐፄ ምኒልክ በግራኝ አሕመድ ወረራ ምክንያት ከማዕከላዊ መንግሥት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወይም እርቆ በነበረው የሀገሪቱ ክፍል መሬት ከተሰጣቸው አርበኞችም ቢሆን የሚበዙት አቶ አሰፋ ጫቦ ነፍሱን ይማረውና ዘመዶቹን ምሳሌ አድርጎ በማቅረብና የዓይን ምስክር በመሆን እንዲሁም በጥናት ከደረሰበት እውነታ 90% የሚሆኑትና ነፍጠኛ በመባል የሚታወቁት መሬት የተሰጣቸው አርበኞች ኦሮሞዎች መሆናቸውን ለኢሳት በሰጠው ቃለምልልስና በመጽሐፉ ላይ አረጋግጧል!!!
ዐፄ ኃይለ ሥላሴም የአምስት ዓመቱ የጣሊያን ወረራ ድል ከተመታ በኋላ እንደዚሁ ለሸዋ አርበኞች የደም ዋጋቸውን በዚሁ አካባቢ የደም ዋጋቸውን መሬት ሰጥተዋል!!!
እናም ባለመዝመታቸውና የሀገራቸውን ነጻነት ማስከበር ባለመቻላቸው ምክንያት መሬት ማግኘት ያልቻሉ ዜጎች የእነኝህን መሬት የተሰጣቸውን አርበኞች መሬት ጉልበታቸውን አዋጥተው በማረስ ከሚያመርቱት ምርት አንድ ሦስተኛ የሚያገኙበት ወይም የሚወስዱበት ሥርዓት ነው እንግዲህ ጭሰኝነት የሚባለው!!!
እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ጭሰኞቹ “አንድ ሦስተኛው ምርት ያንሰናልና አንፈልግም አናርስም!” ካሉ መብታቸው ነው መሬቱን ጥለው መሔድ ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ ባለመሬቱ “ጥሩ አራሽ ወይም ጥሩ ገበሬ አይደሉም!” ብሎ ካመነ ጭሰኞቹን ሊያባርራቸው ወይም ሊሸኛቸው ይችላል የግድ “አሳርሳቸው!” ብሎ የሚያስገድደው ነገር አልነበረም፡፡ በፊውዳል ሥርዓት ውስጥ ግን ጭሰኞቹ “አንፈልግም!” ብለው ጥለው የመሔድ መብት የላቸውም፣ ምርት የመካፈል መብትም የላቸውም ለገዥው ባሮች ናቸው!!!
እንግዲህ ይሄንን እውነታ ነው አቶ መራራ ጉዲናና መሰሎቻቸው ለራሳቸው ርካሽ የፖለቲካ ፍጆታ በሚመች መልኩ አዛብተውና አሳክረው የአማራን ስም በማጠልሸት የሌለ ታሪክ ሲያወሩ የኖሩትና አሁንም እያወሩ ያሉት!!!
ስለ ቋንቋ ወደተናገሩት ስናልፍም እውነታው አቶ መራራ እንዳወሩት አይደለም፡፡ ዐፄ ምኒሊክ ኦሮምኛን ለማሳደግ ባላቸው ፍላጎትና ኦሮሞ በቋንቋው የመጠቀም መብት እንዳለው የሚያምኑ በመሆናቸው “መጫፈ ቁልቁሉ!” የተባለውን በኦነሲሞስ ነሲብ 1899ዓ.ም. ከፈረንሳይኛ ወደ ኦሮምኛ የተተረጎመ የኦሮምኛ መጽሐፍ ቅዱስ በገንዘባቸው ማሳተማቸው የሚታወቅ ታሪክ ነው!!!
ዐፄ ኃይለሥላሴም የኦሮምኛ ስርጭት ያለው የሐረር ሬድዮን ከፍተው እስከ ደርግ ዘመን ድረስ የሬዲዮ ጣቢያው ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበረ የሚታወቅ ጉዳይ ነው!!!
ዐፄ ምኒልክም ሆኑ ዐፄ ኃይለሥላሴ ኦሮምኛን ለማሳደግና ኦሮሞ በቋንቋው እንዲጠቀም ይሄንን ያህል የለፉ ሆነው ሳለ “በቋንቋችን አንዳኝም ነበር፣ በቋንቋችን አንማርም ነበር!” ምንንትስ ቅብርጥስ እያሉ የሌለ ነገር እያወሩ ስማቸውን ለማጠልሸት መሞከር የመጨረሻ ሕሊናቢስነትና ነውረኛነት መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው!!!
እግዚአብሔር ያሳያቹህ ሀገሪቱ ካለባት financial የአቅም ማነስና ውስንነት የተነሣ እንኳንና በኦሮምኛና በሌሎች ቋንቋዎች ይቅርና ብሔራዊ ቋንቋ በነበረው በአማርኛ እንኳ ዳኝነት የሚሰጡ የተማሩ ሰዎች ቁጥር በጣም ጥቂት በመሆናቸው ምክንያት ከሀገር ወደ ሀገር እየተዘዋወሩ ተዘዋዋሪ ችሎት ሰጥተው ይመለሱ በነበረበት ዘመን “በቋንቋችን አንዳኝም ነበር!” ብሎ ክስ ማሰማት፣ እንኳንና በኦሮሞኛና በሌሎች ቋንቋዎች ትምህርት ሊሰጥ ይቅርና ብሔራዊ ቋንቋ በነበረው አማርኛ እንኳ ለማስተማር የሚችሉ የተማሩ ሰዎች ቁጥር በጣም አነስተኛና በሀገሪቱ የነበሩ ትምህርት ቤቶችም በጣት የሚቆጠሩ ብቻ በነበሩበት ዘመን የነገሥታቱን ቅንነትና ልፋት ገደል በመክተት “በቋንቋችን አንማርም ነበር!” የሚል ክስን ማሰማትና ይሄንንም “የብሔር ጭቆና ነው!” የሚል ሥያሜ መስጠት ሕሊናቢስነትና ድንቁርና የተጫነው ነውረኝነት አይደለም ወይ???
በጃንሆይ ዘመን በመላ ሀገሪቱ እየተዘዋወሩ ዳኝነት ሰጥተው ይመለሱ ከነበሩት ሀገሪቷ ከነበሯት ጥቂት የተማሩ ዳኞች መሀከል አንዱ የነበሩት እንዲያውም የጅማ አባጅፋር የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት አባቢያ አባጆቢር አባዱላ አንዱ ናቸው፡፡ ሰውየው በቅርቡ ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ ይሄንን የተዘዋዋሪ ችሎት ታሪክ ጎንደር ጎጃም ትግራይ ድረስ የተጓዙበትን ተሞክሮ በመናገር ገልጠዋል!!!
ከዚህ ውጭ ግን በዚህች ዓለም ውስጥ ድሮም ሆነ አሁን የትኛውም መንግሥት አንድ ቋንቋ መርጦ በመያዝ በዚያ ቋንቋ ከሕዝቡ ጋር ግንኙነቱን ያደርጋል እንጅ የሁሉንም በሀገሪቱ ያሉ ብሔረሰቦቹንና ጎሳዎቹን ቋንቋ እየተናገረ ከሁሉም ብሔረሰቦቹና ጎሳዎቹ ጋር ግንኙነት የሚያደርግ መንግሥት በዓለም ላይ ኖሮ አያውቅም ብቻ ሳይሆን አሁንም የለም፡፡ ግፋ ቢል ከእነኝሁ ብሔረሰቦቹና ጎሳዎቹ ጋር በአስተርጓሚ ግንኙነት በመፍጠር ሥራውን ይሠራል እንጅ!!!
እናም የትም ሀገር ተደርጎ የማያውቅንና አሁንም እየተደረገ ያልሆነን ነገር እየጠቀሱ “አላደረጉም!” እያሉ ቀደምት መንግሥታቶቻችንን ለመኮነን መሞከር የጠባብ ብሔርተኞቻችንን ድንቁርናና ቅብጠትን ብቻ ካልሆነ የሚያሳየው ጠባቦቹ እንደሚሉት ፈጽሞ ጭቆናን አይደለም የሚያሳየው!!!
እጅግ የሚያሳዝነው ነገር እነ መራራ ጉዲናና መሰሎቻቸው ከዚህ ሐሰተኛ ትርክትን መሠረት ካደረገው የባዕዳን ቅጥረኝነት የጥፋት ተልዕኳቸው መቸም ቢሆን ለመታረም የማይፈልጉ መሆናቸው ነው!!!
እንደ እውነቱ ከሆነ ግን እነዚህ የኦሮሞ ልኂቃን የግራኝ አሕመድ ወረራ የፈጠረላቸውን ዕድል ተጠቅመው መንግሥት ያጣውን ነባሩን ሕዝብ እያጠፉ ቅድመ አያቶቻቸው በወረራ የያዙትን የሀገራችን ክፍል “የእኛ ነው!” የማለትና ቋንቋቸው ከሌሎች ሀገር በቀል ቋንቋዎች ተለይቶ “ብሔራዊ ቋንቋ ካልሆነ!” የማለት የሞራል ብቃትና መብት አላቸው ወይ???
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጊዜ ሳያጠፋ ቆርጦ ከመነሣትና እነኝህን ሕሊናቢስ ጽንፈኛ የኦሮሞ ልኂቃንንና ጽንፈኛ ተከታዮቻቸውን ካለማሸነፍ ወይም ካለማጥፋት በስተቀር “ሕሊና ገዝተውና ልካቸውን አውቀው አግባብ ያልሆነ ጥያቄያቸውን በመተው ተስማምተው ይኖራሉ!” ብሎ ከጠበቀ በእነሱ ተቀረጣጥፎ መበላቱና መጥፋቱ እንደሆነ ይወቀው!!!