>
5:21 pm - Thursday July 20, 5561

ዲሽታጊና ( አርቲስት ታሪኩ) በጂንካ ከተነሳው ብጥብጥ ጀርባ አለ መባሉ ተከትሎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ...!!!! (ኢትዮጵያን እናድን)

ዲሽታጊና ( አርቲስት ታሪኩ) በጂንካ ከተነሳው ብጥብጥ ጀርባ አለ መባሉ ተከትሎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ…!!!!
ኢትዮጵያን እናድን

ከብጥብጡ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ወጣቶች ታፍሰው ታስረዋል። የሌሎች ብሄሮች ንብረት መቃተሉ ቀጥሏል
ከጂንካ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ዲሽታ ጊና /ታሪኩ ጋንክሲ ሼክን የሚባለው ሌሎች ብሄሮች ንብረታቸውን አስረክበው ከደቡብ ኦሞ ይውጡ ከሚለው በህቡዕ የተደራጀው አጥፊ ቡድን አባል እና ዋና መሪ ተብለው በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉት ጋር ስብሰባ እየተሰበሰበ የእቅዱ አካል ነበር !! የሚገርመው እነዚህ ወጣቶች ከአመራር በሚሰጣቸው ተልኮ ሌላ ብሔር ሐገራችንን ይልቀቅ እያሉ በማህበራዊ ሚዲያ እየለቀቁ ሳምንት ሙሉ ሲያቃጥሉ ታሪኩ ተው ብሎ አላወገዘም ዝምታን መርጧል ጂንካ ሆኖ:: ውድመት እንደ ዕቅዳቸው ከደረሰ በኃላ ሁሉም በማህበራዊ ሚድያ ታሪኩ የፍቅር ሰባኪው ለምን ዝም አለ ሲሉት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የፃፈው ተመልከቱ!! በተጨማሪም ይህ አውዳሚ ሼክን ለተባለ ቡድን የአመፅ ዘፈን በጥላቻ ዘፍኗል!! የዘፈነውም ዘፈን ከዚህ በፊት የዘፈነውን ሀይስ አይሴ የሚለውን ነጠላ ዜማ ሪሚክስ አድርጎ ነው::ዘፈኑም በአሪኛ እና በአማሪኛ ትርጉሙ ፍፁም ይለያያል::
በአሪኛ ዘፈኑ አአኦ አአኤ ሀኦ ጋከት
ኪት ሀቺንቲ ነጋዬ
ሀች ሀች ሀቻችደቴ
ትርጉሙም
ለማንም አትስሙ እንቢ በሉ ሰያዟችም ሆነ ተው ሲላችሁ አትቀበሉ ሁሉም ካለበት መውደቁ መውረዱ በቅርብ አይቀርም እኛ እንኖራለን ይላል!!ቅኔው የሚወርደው ሀብት ማማ የያዘው መጤው እንደሆነ ነው ህዝብ የተቀበለው!!
 
ነገር ግን በአማርኛ በተቃራኒ ሁሉም ፍቅር ነው ብሉ ጠጡልኝ እያለ የማይገናኝ ትርጉም ዘፍኗል!! ይህን ዘፈን ማዳመጥ ትችላላችሁ ትርጉሙንም አስተርጉማችሁ አጣሩ!! 
 
በአጠቃላይ ታሪኩ ጋንክሲ ሚድያ ላይ ፍቅር ሰባኪ መሳይ ስራው ተቃራኒ ነው!!! ቅዳሜ እለት ወታደሮች እራሱ መተውታል አሳማጮች ጋር አግኝተውት!! ዛሬም ወደ ማረሚያ ስሔዱ የእሱን አአኦ እዘፈኑ እየረበሹ ነበር!! ፖሊሶች ታሪኩ ዲሽታጊናን በተመለክተ ገና እያጣሩ ነው የስልክ ልውውጥ እና የሰው ማስረጃ ከተረጋገጠት አይቀርለትም።
ከብጥብጡ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የጂንካ ልጆችን ሆን ብለው በአጃቢነት በግፍ አስረዋል ከክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አለማየሁ ባውዲ እና የቀድሞው የጂንካ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ገብሬ ይንትሶ ለአራት ዓመት ዕቅድ አቅደው የገንዘብ ፈንድ ከወያኔ እያገኙ ሼክን በሚል ቡድን የአሪ ወጣት እያደራጁ ብሔር ተኮር ጥቃት እንዲደርስ ንብረት እንዲወድም አስደርገዋል!!ሆኖም ጉዳዩን ሆን ብሎ ሳምንት ሙሉ የደበቀው የልዩ ሀይል አዛዥ የአሪ ተወላጅ የሆነው ኮ/ር እንዳለ አበራ የተባለው እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦች ለማስመለጥ እየሰራ ነው!!ሳምንት ሙሉ ከጂንካ እስከ ገጠር ቀበለያት ንብረት ተዘርፎ 151 ቤት የተቃጠለውን የዞኑ መንግስት እራሱ በሚዲያ በመዋቅር ጥያቄ ሽፋን ጥቃት መፈፀሙን የገለፀውን የሁለት ቡድን ፀብ ለማስመሰል ከተማዋን የጠበቁትን እና ቀጣይ ሚስጥር ስለሚያውቁ ማስረጃ ይሆናሉ በሚል አስሮ ከ48ሰዓት በላይ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ታስረዋል!! እነዚህ ወጣቶች ከዚህ በፊት አሁን ሼክን ነን በማለት ጥቃቱን የመሩ እና ባስተባበሩት በተጣራ ምርመራ የዞኑን አስተዳዳሪ አሪ አይደለህም ውረድ ብለው ቢሮው ድረስ ሔደው ለመግደል በሞከሩት መስክረው ምርመራ ተጣርቶ በአለማየሁ ትዕዛዝ ሳይከሰሱ መዝገቡ በእንጥልጥል ቀርቷል አሁን ሊከሰሱ ስለሚችሉ እንዳይመሰክሩ እነዚህ ወጣቶች ታስረዋል!!  ዛሬም ሸንጋማ ቀበሌ የአማራዎች ተብሎ ወፍጮ ከነ ቤቱ ተቃጥሏል::
ከደቡብ ኦሞ አሪ ወረዳ የተሰማ የብድር ድምጽ…!!!
ይሄን ቪዲዮ ስመለከት እያለቀስኩኝ ነው…(በድብቅ በሞባይል የተቀረፀ ነው…ፖሊሶች የሁሉንም ሞባይል ፈትሸው ይህች ብቻ ሳትሰባበር ቀርታለች)
ይህ የሆነው ደቡብ ኦሞ አሪ ወረዳ የተካሄደ ስብሰባ ነው…አማራው ታርዷል…ተቃጥሏል…ውጪ ተበትኗል….ከራሳቸው አፍ ስሙት።
Filed in: Amharic