>

"…ማኔ - ቴቄል - ፋሬስ…!!!  ታየህ - ተመዘንክ - ቀለህም ተገኘህ..!!!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

“…ማኔ – ቴቄል – ፋሬስ…!!!

 ታየህ – ተመዘንክ – ቀለህም ተገኘህ..!!!!! 

ዘመድኩን በቀለ

“…ወታደሮች በጣም ጥንቃቄ እንድታደርጉ የምለምናችሁ የምመክራችሁም ነገር… ወደ ብሔር ኮንቴነር ወርዳችሁ የምታስቡ ከሆነ tplfን መታገል… tplf ጋር መገዳደል አስፈላጊ አልነበረም ቢኮዝ tplf እሱ ስለነበረ። tplfን ጠልታችሁ የtplfን ተግባር የሚደግም ነገር ማድረግ የለባችሁም። 
“…ፈጣሪ ያሳያችሁ እንዲህ የሚለው ሰው እኮ የኦሮሞ ብልፅግና የተባለ የብሔር ድርጅት መሪና ሊቀመንበር ነው። ሃገረ መንግሥቱን የራሴ በሚላቸው ዘሮቹ የሞላ ሰው ነው። ታንኩንም ባንኩንም፣ ከንቲባውንም የዕድር ዳኛውንም ሁሉ በራሱ ዘር ያስወረረ ሰው ነው። አየር ኃይሉ የሚመራው በራሱ ዘር ነው፣ ምድር ጦሩ የሚመራው በራሱ ዘር ነው። ባንኩም ታንኩም የሚመራው በራሱ ሰው ነው። የአፓርታይድ ሥርዓት በሃገሪቱ ላይ እየተከለ መሆኑን እያየነው ያለው ሰው ነው መልሶ እኛኑ “ከዘር ፖለቲካ ውጡ የሚለው። 
“…ህወሓት የተከለችውን የዘር ማዳበሪያ የሆነ መርዛማ ሕገ መንግሥት ታቅፎ እያደረ፣ ራሱ ወታደሩን የዚህ የወያኔን ሕገ መንግሥት ለመጠበቅ ቃል እገባለሁ ብሎ እያስማለ፣ ከሕገ መንግሥቱ አንዲት ቃል አትነሣም ብሎ ከወያኔ በላይ ወያኔ ሆኖ የምናየው ሰውዬ እኮ ነው ህወሓትን አሳዳጊ እናቱን በዚህ መጠን የሚወቅሰው። “…ወደ ብሔር ኮንቴነር ወርዳችሁ የምታስቡ ከሆነ tplfን መታገል… ከtplf ጋር መገዳደል አስፈላጊ አልነበረም because tplf እሱ ስለነበረ። tplfን ጠልታችሁ የtplfን ተግባር የሚደግም ነገር ማድረግ የለባችሁም። ከሂዊ ጋር የተገዳደለው የዘር ፖለቲካን ሊያስቀር ነበር እንዴ? አይገርምላችሁም?
“…የሃገሪቱ ሁኔታ ያሳሰባቸው አንዳንድ ጀነራሎች እና የጦር መኮንኖች እንዳሉ በግሌ ሰምቻለሁ። ነገዳቸው ከዐማራና ከደቡብ ከአፋርና ከሶማሌ የሆኑ የጦር ሰዎችም የሃገሪቱ መጨረሻ እያሳሰባቸው መምጣቱን በግልፅ ማንሾካሾክ መጀመራቸውንም አውቃለሁ። በተለይ የዐማራ ነገድ አባላት የሆኑ የጦር መኮንኖች፣ ወታደሮች ዘራቸው በስግብግብ የኦሮሞ አዛዦች ምክንያት እየጠፋ፣ እያለቀ መሆኑን በመገንዘብም ለምን ማለት መጀመራቸውንም ከሚደርሱኝ መረጃዎች ለመገንዘብ ችያለሁ። አባዬን ይሄ ነው ያሳሰበው። ያስጨነቀውም።
“…በተለይ ባሳለፍነው ሳምንት በሰሜን ወሎ ከፋኖ ጋር በነበረው ግርግር የኦሮሞው የጄነራል ሰሎሞን ኢተፋን ሴራ በማክሸፉ በኩል ራሱ መከላከያ ውስጥ የነበሩ የዐማራና የደቡብ ተወላጆች ያሳዩት እምቢተኝነት፣ ከዚያም በፊት ወደ ሰሜን ሸዋ ምንጃር ተልኮ በነበረው የመከላከያ ኃይል ውስጥ የነበሩ አዛዦችና ወታደሮች ከኦሮሙማው የዐቢይ መንግሥት የተሰጣቸውን ዐማራውን ፍጁት የሚለውን መመሪያ ለምን? ብለው መጠየቃቸው አራት ኪሎ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ እንድትወድቅ እንደዳረጋት ተነግሯል። ለዚህ ነው ጩጬው ጀነራል ኮሎኔሎቹን ሰብስቦ ሊያደነዝዛቸው ሲሞክር የማሸው።
“…በስብሰባው ላይ ከነበሩ የመረጃ ምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነ “…ልጅ ዘመድኩን ሰውየው መስመር ስቷል። በጊዜ ሃይ ሊባልም ይገባል። በስብሰባው ወቅት ካሜራ ከመግባቱ በፊት ሙልጭ አድርጎ በጅምላ ሰድቦናል። ከሃዲም፣ የማንረባ፣ አጋሰስ ሆዳሞች፣ የወያኔ አቃጣሪም እንደሆን አድርጎ ሲሰድበን ነበር። ኋላ ላይ ደግሞ ካሜራ ከገባ ወዲህ ሲያሞጋግሰን ነበር ያመሸው። በጣም ብልግናው ከጫፍ ደርሷል። በዕድሜም፣ በልምድም የምንበልጠውን እኛን እንደተራ ሰው ሲሰድበን አምሽቷል። በጠላት እጅ ብንማረክ እንኳ እንዲህ አንዋረድም፣ አንሰደብምም። ስለእውነቱ ከሆነ ከፍቶናል። ዝርዝር መረጃውን አደራጅተን እንልክልሃለን ብለውኛል።
“…tplfን ጠልታችሁ የtplfን ተግባር የሚደግም ነገር ማድረግ የለባችሁም። በዘር ከረጢት ውስጥ አትግቡ አላለም ዘረኛው…!! ሁሌማ መሸወድ የለም። ነውር ነው። ሁሉም ነገር መታለለልም ጭምር ለከትም፣ ገደብም አለው። ማኔቴቄልፋሬስ…!!
“… እየተጭበረበራችሁ…!!
Filed in: Amharic