>

ዕረፍቱ ለቴዎድሮስ ንጉሠ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ...!!! (ታደለ ሲሳይ)

ዕረፍቱ ለቴዎድሮስ ንጉሠ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ…!!!

ታደለ ሲሳይ

ትላንት ሊበታትኗት የቋመጡላት ኢትዮጵያ ከዐፄ ቴዎድሮስ በፊት ተበታትና ነበር። በመሣፍንት የሥልጣን ጥማት እንደ ቅርጫ ሥጋ የተበታተነችው ኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግሥት አልነበራትም። ነገር ግን የቋራው ካሣ ተነሥቶ የሥልጣን ጥመኞችን ወሽመጥ ቆርጦ የተበታተነውን የኢትዮጵያ ሥጋ ሰብስቦ የአንድነት መለከት ነፋበት። ግኡዙ ሥጋም እስትንፋስ ነሥቶ ኢትዮጵያ በአንድ መንግሥት መመራት ጀመረች።ዘመነ መሣፍንትም ታሪክ ሆነ። እነሆ ይህ ንጉሥ ትላንት የዕረፍቱ መታሰቢያ ነበረ።
በቴዎድሮስ የጠፉት መሳፍንት ዛሬ በየቦታው ብቅ ብቅ ብለው የየራሳቸውን ግዛት አጥረዋል። ጦራቸውንም አሠልጥነዋል። ኢትዮጵያ ከማእከላዊ መንግሥትነት ወደ መሣፍንት ዘመን ተመልሳለች። ይህንን የሥልጣን ጥመኛ ሁሉ አንበርክኮ አንድነቷን የሚመልስ ግዛቷን የሚያጸና ጀግና ያስፈልጋታል። በቴዎድሮስ አማካኝነት የተበታተነችውን ኢትዮጵያን አንድ ያደረገ አምላክ በጎጠኞች የተከፋፈለችን ኢትዮጵያ አንድ ለማድረግ ጀግና እንደሚያስነሣ እምነታችን ጽኑ ነው።
Filed in: Amharic